Search This Blog

Friday, February 28, 2014

U.S. Department of State: 2013 Human Rights Reports of Ethiopia

February 28, 2014

Country Reports on Human Rights Practices for 2013

EXECUTIVE SUMMARY
Ethiopia is a federal republic. The ruling Ethiopian Peoples’ Revolutionary Democratic Front (EPRDF), a coalition of four ethnically based parties, controls the government. In September 2012, following the death of former Prime Minister Meles Zenawi, parliament elected Hailemariam Desalegn as prime minister. In national parliamentary elections in 2010, the EPRDF and affiliated parties won 545 of 547 seats to remain in power for a fourth consecutive five-year term. Although the relatively few international officials allowed to observe the elections concluded that technical aspects of the vote were handled competently, some also noted that an environment conducive to free and fair elections was not in place prior to the election. Authorities generally maintained control over the security forces, although Somali Region Special Police and local militias sometimes acted independently. Security forces committed human rights abuses.U.S Department of State
The most significant human rights problems included: restrictions on freedom of expression and association, including through arrests; detention; politically motivated trials; harassment; and intimidation of opposition members and journalists, as well as continued restrictions on print media. On August 8, during Eid al-Fitr celebrations, security forces temporarily detained more than one thousand persons in Addis Ababa. The government continued restrictions on activities of civil society and nongovernmental organizations (NGOs) imposed by the Charities and Societies Proclamation (the CSO law).
Other human rights problems included arbitrary killings; allegations of torture, beating, abuse, and mistreatment of detainees by security forces; reports of harsh and, at times, life-threatening prison conditions; arbitrary arrest and detention; detention without charge and lengthy pretrial detention; a weak, overburdened judiciary subject to political influence; infringement on citizens’ privacy rights, including illegal searches; allegations of abuses in the implementation of the government’s “villagization” program; restrictions on academic freedom; restrictions on freedom of assembly, association, and movement; alleged interference in religious affairs; limits on citizens’ ability to change their government; police, administrative, and judicial corruption; violence and societal discrimination against women and abuse of children; female genital mutilation/cutting (FGM/C); trafficking in persons; societal discrimination against persons with disabilities; clashes between ethnic minorities; discrimination against persons based on their sexual orientation and against persons with HIV/AIDS; limits on worker rights; forced labor; and child labor, including forced child labor.

ሀይለመድህን አበራ፦ የታፈነ ብሶተኛ ወይንስ የሚያደርገውን የማያውቅ የአእምሮ በሽተኛ?

መንግስትና የመንግስት ደጋፊዎች ነን ባዮች ማምታታቱን ትተው አንዱን መምረጥ አለባቸው

የሰሞኑ ትኩስ ዜና በሆነው የረዳት አብራሪ ሀይለመድህን አበራ የሚያበረውን አውሮፕላን ጠልፎ ስዊዘርላንድ ማሳረፉን በተመለከተ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ነው:: በተለይ የኢትዮጵያው አገዛዝ እና እሱን አውቀውም ይሁን ሳያውቁ ለመደገፍ የሚፈልጉ ሰዎች የሚስጡዋቸው መላምቶች የሚያስገርሙና እርስ በርሳቸው የሚጋጩ ናቸው:: ከነዚህ አስተያየቶች መካከል ሁለቱን ልጥቀስ:: በአንድ  በኩል ሀይለመድህን የአእምሮ ችግር አለበት ሲሉ በሌላ በኩል ደግሞ የሀገሪቱንም ሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ስም ያጎደፈ በማለት ለመውቀስ ይዳዳቸዋል::Ethiopian Airlines pilot Hailemeden Abera Tegegn
እንግዲህ እኔ እስከሚገባኝ ድረስ እነዚህ ሁለቱ ግምቶችና ወቀሳዎች በአንድ ግዜ እና በአንድ ላይ እውነት ሊሆኑ አይችሉም:: አንዱ እወነት ከሆነ ሌላው ሀሰት ይሆናል:: ይህም ማለት ሀይለመድህን የአእምሮ በሽተኛ ከሆነ የኢትዮጵያንም ሆነ የአየር መንገዱን መልካም ገፅታ በማቆሸሽ ሊወቀስ አይችልም:: ምክንያቱም አንድ ሰው የአእምሮ ህመም አለበት ከተባለ በአእምሮ ህመም ውስጥ ሆኖ ለሚፈፅመው ድርጊት ሀላፊነት ሊወስድ አይጠበቅም:: አመዛዝኖና አስቦ ያደረገው ስላልሆነ:: ድርጊቱ በሰውየው እንደተፈፀመ ተደርጎ አይታሰብም:: ምክንያቱም ከግለሰቡ ቁጥጥር ውጪ በሆነ ሀይል ተፅእኖ ስር ሆኖ ያደረገው የተከናወነ በመሆኑ:: በዚህም የተነሳ መልካም ነገር ቢሰራም ሊመሰገንና ሊሸለም እንደማይችል ሁሉ ክፉ ነገር ቢያደርግም ሊወቀስ እና ሊፈረድበት አይገባም:: ይህ ካልሆነ ግን የአእምሮ በሽተኛ የሚለውን ማንሳቱ ብዙም ትርጉም ሊኖረው አይችልም:: ስለዚህ መንግስትና የመንግስት ደጋፊዎች ነን ባዮች ማምታታቱን ትተው አንዱን መምረጥ አለባቸው::

የህወሓቶች ገመና ሲጋለጥ( የካድሬው ወንጀል በማይጨው ሆስፒታል) Abraha Desta

ብርሃኑ ሃይለስላሴ ይባላል። አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ እያለ ጥናቱን ትቶ በካድሬነት ተግባር የተሰማራ እንደነበር አውቃለሁ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የምንማር የትግራይ ልጆችን እየሰለለ ነበር የሚውለው። 

ተመረቀና በህወሓት አባልነቱ መሰረት የትምህርት ዉጤቱ ግምት ዉስጥ ሳይገባ፣ ሳይወዳደር (ሌሎች ብቁ ሰዎች እያሉ) በእምባ አለጀ ወረዳ የጤና ጥበቃ ሐላፊ ተደርጎ በፓርቲ በመሾሙ ዓዲሽሁ ከተማ ገባ። በዓዲሽሁ ከተማ ብዙ ሴቶችን ደፈረ። ህዝብ ጮሆ። ሰሚ የለም። ምክንያቱም ሐላፊ ነው።

ሴቶችን በመድፈር ወንጀል ከመክሰስ ይልቅ ሌሎች ሰራተኞች ያላገኙት የማስተርስ ትምህርት ዕድል ተሰጠው። ሴቶች ስለደፈረ ተሸለመ ማለት ነው። በጦላይ ለስልጠና ተልኮ እዛም ሌላ ሴት ደፈረ። የተደፈረች ሴት የሕግ ከለላ አጥታ ከሱ ጋር እንድትታረቅና ክስ ላትመሰርት ተገደደች።



ከስልጠና በኋላ ህወሓቶች የማይጨው ለምለም ካርል ሆስፒታል CEO አድርገው ሾሙት። እነሱ ምን ይሳናቸዋል!? በማይጨው ከአንድ ዓመት ባልበለጠ ግዜ ዉስጥ አስራ አራት ሴቶችን ደፈረ፤ ስልጣኑን ተገን በማድረግ። ሴቶች አቤት ይላሉ። ግን ሰሚ የለም። በማይጨው ሰው በመኪና ገጨ። ራሱ ሰው ገጭቶ ሽፌሩ እንደገጨ ለማስመሰልና ከቅጣት ለመዳን ከሽፌሩ ጋር ተዋዋለ። ክስ ተመስርቶበት፣ በፖሊስ ተይዞ በስድስት ሺ ብር ዋስ ተለቀቀ።

ይህን ሁሉ ግፍ ሲፈፅም የማይጨው ኗሪዎችና የሆስፒታሉ ሰራተኞች ቅሬታ አሰሙ። ረበሹ። ተሰበሰቡ። የሆስፒታሉ ሰራተኞች ተሰብሰበው ከፓርቲ አባልነቱ እንዲወገድ ጠየቁ (ምክንያቱም የገዢው ፓርቲ አባል በመሆኑ ስልጣኑ ተገን አድርጎ ነው ግፍ እየፈፀመ ያለው ከሚል እሳቤ)። ከስራ (ከሐላፊነቱ) ታግዶ በፖሊስ እንዲያዝ ወሰኑ። ቢሮው ታሽጎ ሁለቴ ቁልፍ ሰብሮ መግባቱ ተረጋገጠ። ማንም አልጠየቀውም።

አቶ ብርሃኑ ሃይለስላሴ በሰራተኞቹ ስብሰባ ቀርቦ ሁሉም የተጠቀሱት ወንጀሎች መፈፀሙ አምኖ ይቅርታ ጠየቀ። በተበዳዮቹና ሰራተኞቹ ግፊት በፖሊስ እንዲታሰር ተደረገ። ህዝቡ ተረጋጋ። እኛም "ኮርማው ታሰረ!" ብለን በፌስቡክ ፃፍን። ህወሓቶች ለምን አስራ ስምንት ሴት እስኪደፍር ድረስ ዝም አሉት? ሕግ ለካድሬዎችስ አይሰራም ወይ? ብለን ጠየቅን። የህወሓቶች አድሎአዊ አሰራር ወቀስን። መታሰሩ ግን ጥሩ መሆኑ ጠቆምን።

አቶ ብርሃኑ በፖሊስ ከታሰረ ከሁለት ቀናት በኋላ መለቀቁ ሰማሁ። መለቀቁን አስመልክቼ በፌስቡክ ፃፍኩ። መለቀቁ ግን በሌላ አካል አልተረጋገጠም ነበር።

Thursday, February 27, 2014

በባህር ዳር ከተማ የታየው ህዝባዊ ተቃውሞ በሌሎች የሀገራችን ክፍሎችም ተጠናክሮ ይቀጥላል!

(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ!!!

ከጊዜ ወደ ጊዜ አምባገነናዊ የአፈና መዋቅሩን በማጠናከር ለመድብለ ፓርቲ የፖለቲካ ሥርዓት በር መዝጋቱን አጠናክሮ ለብቻው አውራ ፓርቲ ለመሆን እየታተረ ያለው የኢህአዴግ መንግሥት ደርግ በውድቀቱ ዋዜማ ወደ ተላበሰው ባህሪ እየተሸጋገረ እንደሆነ ተስተውሏል፡፡
የዚሁን ድርጅታዊ ባህሪ ውርስ በዋነኛነት ከሚያስፈጽሙት የግምባሩ አባል ድርጅቶች አንዱ የሆነው ብአዴን ኢህአዴግ በአማራው ህዝብ ላይ እየፈፀመው ያለው የንቀት እና የማጥላላት ዘመቻም አብይ ተደርገው ሊወሰዱ ከሚችሉ የግንባሩ አፍራሽ ተግባራት በዋነኝነት ሊጠቀስ የሚችል ነው፡፡
የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የብአዴን ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን የክልሉን ህዝብ የናቀ እና ያዋረደ አስነዋሪ ንግግር ካደረጉ በኋላ ከጥፋታቸው ከመታረም ይልቅ በክልሉ ቴሌቭዥን ያንኑ አምባገነናዊ ባህሪያቸውን እንደያዙ የግሌ ብቻ ሳይሆን የድርጅቴ አቋም ነው ሲሉ መመለሳቸውም መላውን የሀገሪቷን ህዝብ ያስቆጣ ተግባር ነው፡፡

ብሶት በርክቷል!

በአሁኑ ጊዜ በየቦታው የተጠራቀሙ ብሶቶች ይሰማሉ፡፡ ከመንግሥታዊ ተቋማት የተዝረከረከ አገልግሎት አሰጣጥ ጀምሮ እስከ ዋናው የአገሪቱ የፖለቲካ ሥነ ምኅዳር ድረስ ብሶት በርክቷል፡፡

የኑሮ ውድነቱ አዕምሮውን የሚያናውጠው ሕዝብ፣ የመልካም አስተዳደር እጦትና የሰብዓዊ መብት መጓደል እያንገሸገሸው ነው፡፡ ሕዝቡ መንግሥት ምን እስኪሆን ድረስ ነው የሚጠብቀው እያለ በየቦታው ያጉረመርማል፡፡ ይኼ አሉባልታ ሳይሆን እውነት ነው፡፡ በተጨባጭ የሚታይ፡፡ 



እንዲህ ዓይነቱ የብሶት አቤቱታ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ለተሰገሰጉ ራስ ወዳዶችና ስግብግቦች ላይዋጥላቸው ይችላል፡፡ ነገር ግን እውነቱ ይኼ ነው፡፡ በተደጋጋሚ ሕዝቡ የመልካም አስተዳደር ችግር ሲገጥመው፣ ‹‹ይኼ የኪራይ ሰብሳቢዎችና ፀረ ሕዝቦች ሟርት ነው›› እየተባለ ሲድበሰበስ ይሰማል፡፡ ችግሩ አፍጥጦ ወጥቶ መላወሻ ሲታጣ ግን፣ ‹‹የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ ተግተን እንሠራለን›› የሚል ማስተዛዘኛ አይሉት ማደናገሪያ ይቀርባል፡፡ አሁን በተጨባጭ እየታየ ያለው መልካም አስተዳደር የሚባለው ጽንሰ ሐሳብ መቀለጃ መሆኑ ብቻ ነው፡፡ 

ሕዝቡ የፍትሕ ያለህ እያለ በየደረሰበት ሲያነባ ላይ ላዩን ችግሩ መኖሩን እያመኑ መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ ችግሩን ማባባስ የተመረጠ ይመስላል፡፡ በፍትሕ እጦት የሚንገላታው ዜጋ መንግሥት ከዛሬ ነገ መፍትሔ ያፈላልግልኛል ብሎ ሲጠብቅ ውጤቱ በዜሮ ተባዝቶ እየቀረበለት ነው፡፡ በፍትሕ ሥርዓቱ ውስጥ የተሰገሰጉ ግለሰቦችና ቡድኖች ሕዝቡን ከማስለቀስ አልፈው ተስፋ እያስቆረጡት ነው፡፡ 

በሰብዓዊ መብት ጥሰት ምክንያት አቤቱታ ሲቀርብ ፈጽሞ አይፈጸምም በሚባልበት አገር ውስጥ በርካታ እሮሮዎች እየተደመጡ ናቸው፡፡ ሐሳብን በነፃነት ከመግለጽ ጀምሮ የተለያዩ የመብት ጥያቄዎችን የሚያቀርቡ ዜጎች በጠላትነት ይፈረጃሉ፡፡ ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን ለማስከበር ላይ ታች ሲሉ በሕገወጥ መንገድ ይሰቃያሉ፡፡ መብትን በሰላማዊ መንገድ መጠየቅ ከነውር በላይ እየታየ ዜጎችን ወደ ሕገወጥነት የሚመራ አሻጥር ይከናወናል፡፡ በመንግሥት መዋቅሮች ውስጥ የተሰገሰጉ እነዚህ ኃይሎች ዜጋ በአገሩ እንዳይኮራና ስደት ውስጥ እንዲዘፈቅ እያደረጉ ናቸው፡፡ 

Wednesday, February 26, 2014

በአባይ ግድብ ጉዳይ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር እየተነጋገርኩ ነው አለች

አራት ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ዶላር ይፈጃል የተባለዉ ግድብን እንገነባለን በማለት የኢትዮጵያ መንግስት በቦንድ ስም ገንዘብ ለመሰብሰብ ያደረገዉ ሙከራ እምብዛም አለመሳካቱ ይታወቃል። የኢትዮጵያ መንግስት የግንባታዉ ፕሮጀክት ሰላሳ አራት ከመቶ ተጠናቋል ቢልም ግብጽ ባሰማችዉ ተቃዉሞ የግድቡ ግንባታ መስተጓጎሉን የመገናኛ ብዙሗን ዘግበዋል።Rile river facts and information in Amharic
የኢትዮጵያ ዉሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሆኑት አቶ አለማየሁ ተገኑ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “ኢትዮጵያ ችግሩን ለመቅረፍ ከሱዳን ጋር ዉይይት ጀምራለች” ሲሉ ገለጸዋል። ግብጽን ወደ ዉይይቱ ሒደት ለማምጣት እየተጣረ መሆኑን የገለጹት ሚኒስቴር ሒደቱ ምን እንደሚመስል ግን ያመላከቱት ነገር የለም።
ሱዳንና ግብጽ ከግድቡ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ኢትዮጵያ ብትገልጽም፤ ሁለቱ አገራት ግን ለጉዳዩ አዎንታዊ ምላሽ ሲሰጡ አልተስተዋልም። ግብጽ ሰማኒያ ከመቶ የሚሆነዉ የዉሃ ሐብቷ ከአባይ እንደሚመጣ ይታወቃል፤ የአባይን ጉዳይ እንደ ህልዉና ስለምትመለከትዉ የህዝብ ድጋፍ የሌለዉ የመላኒየሙ ግድብ እንደምን ዉጤታማ ይሆናል የሚለዉ ጉዳይም አጠያያቂ እየሆነ ነዉ።
ግድቡን ለመገንባት እስከ ሐያ ሺ የሚደርሱ ኢትዮጵያዉያን መፈናቀላቸው የታወቀ ሲሆን 70 ሚሊዮን ኩቢክ ሜትር ዉሃን ያከማቻል ተብሎ የተነገረት ግድብ ከፈነዳ ከፍተኛ የዉሃ መጥለቅለቅ ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት አለ።

ምነው ሚኒስትር ዘነቡ ?


ትናንት ማታ የሴቶች፣ ሕጻናትና የወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትሯ ወ/ሮ ዘነቡ በትዊተር ገጻቸው ላይ ግብረ ሰዶምን በተመለከተ የጻፉትን ነገር ከምመለከት ወይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ባይኖር ወይ እርሳቸው ሚኒስትር ባይሆኑ እመርጥ ነበር፡፡ የሴቶችና የወጣቶች፣ የሕጻናት ሚኒስትር ሆነው ግብረ ሰዶምን በመደገፍና የዑጋንዳን አዲሱን ሕግ በመቃወም መጻፋቸው ‹‹ይህቺ ሀገር ወዴት እየሄደች ነው›› ብዬ እንድጠይቅ አድርጎኛል፡፡ ከተወሰኑ ጊዜያት በፊት በአዲስ አበባ የተሾሙ የአሜሪካ አምባሳደር በኢትዮጵያ የግብረ ሰዶማውያን መብት እንዲጠበቅ እሠራለሁ ያሉትን አስታውሼ እኒህ ዲፕሎማት እውነትም ሠርተዋል ማለት ነው አልኩ፡፡

ከተወሰኑ ዓመታት በፊት የኤች አይ ቪ ኤድስ ጉባኤ በአዲስ አበባ ሲደረግ የእምነት ተቋማት መሪዎች ግብረ ሰዶምን በመቃወም መግለጫ ለመስጠት ተዘጋጅተው ወዲያው ነበር የተሠረዘው፡፡ ግብረ ሰዶማውያንን ተዋቸው ተብለው መግለጫቸው መሠረዙ፣ እነርሱም ያንን በዝምታ ማለፋቸው በሀገራችን ከተከናወኑ አሳዛኝ ተግባራት አንዱ ሆኖ እንዲመዘገብ አድርጎታል፡፡
ዑጋንዳ ሕጉን ያወጣችው የግብረ ሰዶማውያንን ተግባር ለመከታተል፣ ለመቆጣጠርና ሕጋዊ ርምጃ ለመውሰድ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕግም ግብረ ሰዶም ወንጀል መሆኑን ከዑጋንዳ ቀድሞ የደነገገ ነው፡፡ ምነው ሚኒስትራችን የግብረ ሰዶም ደጋፊ ሆነው ብቅ አሉ፡፡ ይህ ሕግኮ እርሳቸውንም የሚመለከት ነው፡፡ ግብረ ሰዶም በሀገሪቱ በድብቅ እየተድፋፋ ሕጻናትና ወጣቶችን እየቀጠፈ፣ ማኅበረሰባዊና ሃይማኖታዊ እሴቶቻችንን እያፈረሰ ነው፡፡ ሰውን ከተፈጠረበት ዓላማና ግብር ውጭ የሚያደርግ ነው ግብረ ሰዶም፡፡ እንስሳት እንኳን የማይፈጽሙትን የሚያስደርግ ነው ግብረ ሰዶም፡፡
ምዕራባውያን በራሳቸው ምክንያት የተነሣ የዚህ ሐሳብ ደጋፊም አቀንቃኝም ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እነርሱ የደገፉትን ሁሉ የመደገፍ ግዴታ ግን የለብንም፡፡ የእነርሱ ማኅበረሰባዊ ሥሪትና የእኛ ሥሪት ፈጽሞ አይገናኝም፡፡ በርግጥ ይህንን መሰል ርካሽ ነገሮችን መደገፍና ማቀንቀን ዓለም ዐቀፍ ተቀባይነትን ለማግኘት አቋራጭ መንገድ መሆኑ ይታወቃል፡፡ እኛ ግን ሚኒስትራችን የምንፈልጋቸው ለአሜሪካ ጉዳዮች አይደለም፤ ለኢትዮጵያ ጉዳዮች እንጂ፡፡
እርስዎ የተሾሙላቸው ሕጻናት፣ ሴቶችና ወጣቶች ሥራ፣ ንጹሕ ውኃ፣ የመኖሪያ ቤት፣ የጤና ተቋማት፣ ሰብአዊና ፖለቲካዊ መብቶች ቸግሯቸው እንጂ ግብረ ሰዶምነት አልቸገራቸውም፡፡ ግብረ ሰዶምነት የእነርሱ ማጥቂያ መሣሪያ እንጂ ክብርት ሚኒስትሯ የሚቀኙለትና የሚሟገቱለት አይደለም፡፡
ለሕጻናት፣ ለወጣቶችና ለሴቶች ያልተሠራ ብዙ አጀንዳ ባላት ሀገር፣ በዐቅም እጥረት በጤና ተቋማቱ የማይወልዱ እናቶች፣ በየጉራንጉሩ የሚወለዱ ሕጻናት፣ በየጫት ቤቱ ሥራ ፈትተው የሚባዝኑ ወጣቶች ያሏት ሀገር ግብረ ሰዶምን ጉዳዬ ብላ ማቀንቀኗ በዜጋ ላይ የሚፈጸም ስላቅ ነው የሚሆነው፡፡
እኔ ይህ መልእክት አሁንም የእርሳቸው ባይሆን እመርጣለሁ፡፡ ማብራሪያ እንደሚሰጡበትም ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ሚኒስትሯስ ምን ይላሉ?

ሚኒስትሯ ወ/ሮ ዘነቡ ለታድያስ አዲስ ዛሬ በ9 ሰዓት በሰጡት መግለጫ ‹‹ከልብ ነው ያዘንኩት፤ የእኔም አቋም አይደለም፤ የመንግሥትም አቋም አይደለም፤ ያየሁትም በትናንትናው ዕለት ነው፤ በሆነውም ነገር በጣም ነው ያዘንኩት፤ በተፈጠረው ነገር ሰብእናዬ ተጎድቷል፡፡ እስከ መጨረሻ ማጣራት ያለብኝን አጣራለሁ፡፡ ይህ በሀገሪቱ ሕግ ላይ የተቀመጠ ወንጀል ነው፡፡ ከእኔ ሰብእናም ጋር አይሄድም›› ብለዋል፡፡ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሽመልስም ‹‹አካውንታቸው ባልታወቁ ሰዎች ተጠልፏል›› ብለዋል፡፡

Ethiopians in Dallas Raise $ 31,000 to Assist Saudi Victims

Under the leadership of The Mutual Assistance Association for the Ethiopian Community (MAAEC), we Ethiopians living in the Dallas Fort Worth area have come together to assist our brothers and sisters who are victims of the violent crackdown and deportation in Saudi Arabia. As a result, $31,000 has so far been raised for the cause. Ato Birhan Mekonnen, chairman of the MAAEC, handed over the check ($31,000) to the representatives of United States Association for International Migration (USAIM) in a ceremony conducted on Tuesday, Feb 25, 2014 at the latter’s office, in Washington DC. The remaining uncollected fund will be delivered in due time. USAIM is an organization engaged on providing the much-needed humanitarian assistance for the vulnerable Ethiopians returning from Saudi Arabia.Ethiopians Saudi Arabia victims
Following the news of the inhuman and horrible Saudi crack down on Ethiopians living in the kingdom couple of months ago, the Ethiopian community in Dallas Fort Worth joined hands with the world wide campaign to stand for the human rights of our Ethiopian sisters and brothers. MAAEC had issued a press release condemning the act, organized a historic protest demonstration at the Federal building in Dallas, and conducted a candle vigil night to memorize in memory of those died in the violence. Once again we reaffirm our solidarity with our brothers and sisters and pledge to continue to do all we can to help them in the future.

Tuesday, February 25, 2014

የስዊስ አቃቢ ህግ የረዳት ሃይለመድህን አበራን ሰብአዊ መብቶች ያከብራል ሲሉ ቃል አቀባዩዋ ተናገሩ

-የሰዊስ አቃቢ ህግ ቃል አቀባይ ሚስ ያኔት ባልመር በረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ዙሪያ ከኢሳት ለቀረበላቸው ጥያቄ የምርመራ ሂደቱ ያልተጠናቀቀ በመሆኑ ዝርዝር መረጃዎችን ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸው ገልጸው፣ የሰብአዊ መብቱን በመጠበቅ በኩል ለተነሳው ጥያቄ ግን ስዊዘርላንድ የሰብአዊ መብቶችን በጠበቅ በኩል ታዋቂ አገር መሆኑዋን በመግለጽ የሃይለመድህንን የሰብአዊ መብቶች እንደሚያከብሩ ገልጸዋል።
ሃይለመድህን ጠበቃ ተቀጥሮለት ጉዳዩን በመከታተል ላይ ነው። የሃይለመድህንን የፍርድ ቤት ጉዳይ መከታተል ይቻል እንደሆን የተጠየቁት ቃል ሚስ በርነር፣ በአሁኑ ሰአት ስለፍርድ ቤት ሂደት ለማውራት ባይቻልም በስዊዘርላንድ አብዛኛውን ጊዜ ፍርድ ቤቶች በግልጽ ችሎት ጉዳዮችን እንደሚያዩ ተናግረዋል።
የሚቀጥለው የፍርድ ቤት ቀጠሮ ቀን ይታወቅ እንደሆን ሲጠየቁም ” እዛ ደረጃ ላይ ገና አልተደረሰም” በማለት መልሰዋል። የምርምራው ሂደት መቼ እንደሚጠናቀቅ ሲጠየቁም፣ የስዊስ የፍትህ አሰራር መረጃዎችን በሚስጢር መያዝን ስለሚያዝ፣ ምንም አይነት መግለጫ መስጠት እንደማይቻል አክለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ስዊዘርላንድ ለረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ጥገኝነት እንደትሰጥ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ የፊታችን አርብ ፌብሩዋሪ 28 በበርን እንደሚካሄድ በስዊዘርላንድ የ ዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ የስውዘርላንድ የድጋፍ ኮሚቴ ገልጿል።

በአርማጭሆ የአንድነት ፓርቲ አባላት ከስራ ተባረሩ

-የፓርቲው አባላት በመንግስት ስራ ውስጥ ድርሻ አይኖራችሁም ተብለው መባረራቸውን የተባረሩ የፓርቲው አባላት ለኢሳት ገልጸዋል። አብዛኞቹ ለሱዳን እየተሰጠ ያለውን መሬት በተመለከተ ተቃውሞ በማሰማታቸው መባረራቸውን ገልጸዋል።
የምእራብ አርማጭሆ የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ የሆነው አቶ አንጋው ተገኝ፣ በድንበር ጉዳይ ጥያቄ በማንሳታቸው መባረራቸውን ገልጸዋል
ከተባረሩት የፓርቲው አባላት መካከል አወቀ ብርሃኑ፣ አባይ ዘውዱ ፣ አንጋው ተገኝ፣ አብርሃም ልጃለም እና አለልኝ አቡሃይ ይገኙበታል።

Rally for Ethiopian Airlines Co-Pilot in Washington DC. Switzerland Embassy

Monday, February 24, 2014

“የባህርዳር ህዝብ አንግቦ የተነሳው በአገሪቱ እየጨመረ የመጣውን የለውጥ ጥያቄ ነው” ሲሉ ነዋሪዎች ገለጹ

የ28 አመቱ ሙላት የመሸንቲ ነዋሪ ነው፤ በተቃውሞ ሰልፉ ላይ የተገኘሁት በአገዛዙ ተማርሬ ነው ይላል። ለምን ተማረርክ በማለት ዘጋቢያችን ላቀረበችለት ጥያቄ፣ “ምን የማያስመርር ነገር አለ፣ ሁሉም ነገር እየተበላሸ እንጅ እየተሻሻለ ሲሄድ አታይም፣ ይህም አልበቃ ብሎ ይዘልፉናል” በማለት በሰልፉ ላይ የተገኘበትን ምክንያት ገልጿል።
የባህርዳር ነዋሪዎች አንድነትና መኢአድ በጋራ በጠሩት ሰልፍ ላይ በነቂስ ወጥተዋል። “ህዝብን እያዋረዱ መግዛት አይቻልም፣ብአዴን ኢህአዴግ የአማራን ህዝብ የመግዛት የሞራል ልእልና የለውም፣ ህዝብ ከእርስት ማፈናቀል ይቁም፣ ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል፣ ነጻነት የሌላት አገር ጨለማ ናት፣ ገበሬው በገዛ መሬቱ ስደተኛ አይሆንም” የሚሉና ሌሎችም መፈክሮች ተስምተዋል።
“ዛሬ ታላቅ ደስታ ተስምቶኛል፣ የአመታት ህመሜ ተፈውሷል” ሲል የተናገረው የቀበሌ 7ቱ ነዋሪ ማሙሽ፣ ሰልፍ እንደሚደረግ ከሰማበት ጊዜ ጀምሮ ሲቀሰቅስ መቆየቱን ተናግሯል።
አቶ አለምነው መኮንን የአማራን ህዝብ መዝለፋቸውን ተከትሎ የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የባህርዳር ነዋሪዎች በኢትዮጵያ ባንዲራ፣ አንዳንዶችም ጥንታዊት ኢትዮጵያን በሚወክሉ የጀግንነት ማጌጫዎች ተውበው በአደባባይ ተይተዋል።
ይሄ ህዝብ ማስፈራሪያዎችን ሁሉ ጥሶ፣ የቀን አበል ሳይሰጠው ለነጻነቱ በፍላጎቱ የወጣ ህዝብ ነው ያለው መኮንን፣ ገዢው ፓርቲ ይህንን ሰልፍ ለማውገዝ ሌላ ሰልፍ ሊያዘጋጅ እንደሚችል ይናገራል።
“ወጣቱ ፣ ሽማግሌው ሴቱ ወንዱ ተነስቷል” የሚለው ሌላው ነዋሪ፣ ህዝቡ ለነጻነቱ ሲጠይቅ መዋሉን ገልጿል።
“ከሰለፉ ማግስት ባህርዳር እንዴት ናት?’ በማለት ሲጠየቅም፣ ” ህዝቡ ደስ ብሎት በእየቤቱ እየተወያየ ነው” ብሎአል ። ሌላው አስተያየት ሰጪ ደግሞ በሰልፉ ላይ የታየውን ዲሲፒሊን አድንቋል።
የአቶ አለምነው መኮንን ጉዳይ የተቃውሞ ሰልፉን ለማድረግ እንደ መነሻ ሆነ እንጅ ዋናው ጥያቄ የዲሞክራሲ፣ የነጻነት እና የኢኮኖሚ መሆኑን ገልጿል። ”ኢህአዴግ እንደተናካሽ ውሻ በድንጋጤ ያገኘውን ሁሉ ለመንከስ ቢሞክርም፣ ትግሉ ግን ወደ ሁዋላ የሚቀለበስ አይመስለኝም ሲል አስተያየቱን አክሏል።

የኦሮሚያ ክልል ከስልጣን የለቀቁትን ፕሬዚዳንቱን ለማሳከም ከፍተኛ ገንዘብ ማውጣቱ ታወቀ

ያለፉትን ሶስት የሥልጣን አመታት በህክምና ያሳለፉትና ከሳምንት በፊት በገዛ ፈቃዳቸው ከሃላፊነታቸው የተሰናበቱት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አለማየሁ አቶምሳን ለማሳከም ክልሉ ከአንድ ሚሊየን አሜሪካን ዶላር በላይ ወጪ ማድረጉ ተሰማ፡፡
በጰጉሜ ወር 2002 ዓ.ም ኦህዴድ ባካሄደው ጉባዔ ባልተጠበቀ መንገድ አቶ አባዱላ ገመዳን ተክተው ወደስልጣን የመጡት አቶ አለማየሁ በስራ ገበታቸው ላይ ብዙም ሳይሰነበቱ በመታመማቸው ያለፉትን ሶስት ዓመታት በህክምና ምልልስ ለማሳለፍ ተገደዋል፡፡
አቶ አለማየሁ አቶምሳ፤ የአቶ አባዱላ ገመዳ አመራር የተዘፈቀበትን ስር የሰደደ ሙስና ለመታገል በተሾሙ ማግስት በትኩስ ጉልበት ተነሳሽነት አሳይተው እንደነበር የጠቆሙት የኢሳት የኦሮምያ ምንጮች፣ በሁዋላ ግን ከምግብ መመረዝ ጋር በተያያዘ ለከፍተኛ ህመም በመዳረጋቸው ስራ ለመስራት አለመቻላቸውን ገልጸዋል።
በአቶ አባዱላ የክልል አመራር ዘመን የአዲስአበባ አጎራባች የሆኑ የኦሮሚያ ከተሞች ከፍተኛ የመሬት ወረራ ወይም ሙስና የተፈጸመ ሲሆን አቶ አባዱላ ይህን ለማስቆም ምንም ጥረት አለማድረጋቸው ብቻም ሳይሆን እሳቸውም ተዋናይ ሆነው መገኘታቸው በመተካካት ስም በኦህዴድ ውስጥ ያላቸው ሚና እንዲቀንስ ምክንያት መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡
አቶ አለማየሁ የክልል ፕሬዚደንት በመሆናቸው በመንግስት ወጪ መታከማቸው ተገቢና ሕግ የሚደግፈው ቢሆንም፣ ለእሳቸው ሕክምና ባለፉት 3 ዓመታት የወጣው ወጪ በኢህአዴግ በትረ ስልጣን ዘመን ለማንም ወጥቶ እንደማያውቅ ታውቋል።
አቶ አለማየሁ ተከታታይ ሕክምናቸውን በታይላንድ ያካሄዱ ሲሆን በከፍተኛ ስፔሻሊስት ሀኪሞች የሚደረግላቸው ክትትል ለአንድ ጊዜ ከ200 እስከ 400 ሺ ብር የሚገመት ወጪ ያስወጣል።
ለአቶ አለማየሁ የወጣው አንድ ሚሊየን ዶላር የሚገመት ወጪ በኦሮሚያ ክልል ለሚገኙ ደሃ ህዝቦች ከአንድ በላይ የጤና ጣቢያዎች ወይም ት/ቤቶችን መገንባት የሚችል መሆኑን በመግለጽ በዚህ መልኩ የሕዝብ ገንዘብ መውጣቱ ትልቅ የሐብት ብክነት ተደርጎ ተቆጥሯል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ፕሬዚዳንቱን ለመተካት የኦሮምያ ባለስልጣናት ሽኩቻ ውስጥ መግባታቸውን ምንጮች አክለው ገልጸዋል። ፕሬዚዳንቱ በምክር ቤቱ የተሾሙና ተጠሪነታቸውም ለምክር ቤቱ ቢሆንም ፣ ምክር ቤቱ ሳያውቀው እንዲወርዱ ተደርጓል። እስካሁንም ድረስ የምክር ቤቱ አባላት ማን እንደሚሾም የሚያውቁት ነገር የለም።

Saturday, February 22, 2014

የመከላከያ ተቋም ተግባር አገርን መጠበቅ ነዉ ወይስ አገርን መዝረፍ?

የአዉሮፓ ቅኝ ገዢዎች አፍሪካን ሲቀራመቱ ባህር ተሻግረዉ በመጡ የነጭ ባዕዳን ኃይሎች መገዛትን መርጦ የአዉሮፓን ወራሪዎች በሰላም በሩን ከፍቶ ወደ አገሩ ያስገባ እንድም የአፍሪካ አገር አልነበረም፤ የኋላ ኋላ ተሸንፈዉ በቅኝ አገዛዝ ቀንበር ስር ቢወድቁም ሁሉም የአፍሪካ አገሮች እንደ አቅማቸዉ ከወራሪ ኃይሎች ጋር ተፋልመዋል። በአንድ ወቅት የቅርብ ጎረቤቶቻችንን ጨምሮ ብዙዎቹ የአፍሪካ አገሮች በወራሪ ኃይሎች ተሸንፈዉ የቅኝ ገዢዎች ቀንበር ጀርባቸዉ ላይ ሲጫን አገራችን ኢትዮጵያ ብቻዋን የአለም ጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተምሳሌት ሆና የኖረችዉ ጣሊያኖች፤ እንንግሊዞችና ፈረንሳዮች ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ለይተዉ ስለወደዷት ወይም ስላከበሯት አይደለም። ይልቁንም ነፃነታችንና የግዛት አንድነታችን ተከብሮ የኖረዉ ኢትዮጵያ እናት አገሩ በጠላት ስትደፈር ከሚያይ ምትክ የሌላት ህይወቱ ብታልፍ ደስ የሚለዉ የኩሩና የጀግና ህዝብ አገር በመሆኗ ነዉ። የሚገርመዉ ይህ ኩሩና ጀግና ህዝብ ጣሊያንን የመሰለ በዘመናዊ መሳሪያ የታጀበ ኃይል ዉርደቱን ተከናንቦ ወደመጣበት እንዲመለስ ሲያስገድድ እንደ ዛሬዉ የተደራጀ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት አልነበረዉም። ዛሬ አራት ኪሎና ስድስት ኪሎ ላይ የተተከሉት ሁለቱ ታሪካዊ ሀዉልቶቻችን የሚነግሩንም ይሀንኑ የኢትዮጵያ ህዝብ በዘመናዊ መልክ የተደራጀ ሠራዊት ሳይኖረዉ የጎበዝ አለቃ እየመረጠ በጣሊያን ፋሺስቶች ላይ የተጎናጸፈዉን አኩሪ ድል ነዉ።
ኢትዮጵያ ዉስጥ ዘመናዊና የተደራጀ መከላከያ ሠራዊት ጥንስስ የተጣለዉ በዳግማዊ ሚኒልክ ዘመነ መንግስት ሲሆን እሱም ቢሆን ከአድዋ ድል በኋላ ቆይቶ የመጣ ክስተት ነዉ። በአፄ ኃ/ሥላሤና በደርግ ዘመነ መንግስት ኢትዮጵያ ለአንድ ፓርቲና ይህ ፓርቲ እወክለዋለሁ ለሚለዉ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ሙያዊ ብቃት የነበረዉ፤ሙያዉን የሚያከብርና ለአገሩና ለወገኑ ታማኝ የሆነ የመከላከያ ሠራዊት ነበራት። የወያኔ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ መጠለፍ እና ወያኔ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በረዳት አብራሪ ሃይለመድህን አበራ መጠለፉን ተከትሎ የአየር መንገዱ ተጠቃሚዎች ቁጥር ይቀንሳል ተብሎ ይገመታል። ይህን የተረዱት የወያኔ ሹማምንት መክረው ዘክረው የደረሱበት ስልት ቢኖር የረዳት አብራሪውን ቤተሰቦች በማስፈራራትና በማግባባት ረዳት አብራሪው አእምሮው የታወከ “እብድ” እንደሆነ እንዲናገሩ ማድረግ ነው።
የረዳት አብራሪው እህት “ወንድምሽ ጭቅላቱን ያመው ነበር ብለሽ ከተናገርሽ በንጻ ይለቀቃል” የሚል ምክር በተላኩ የደህንነት ሰዎች እንዲደርሳት የተደረግ ሲሆን ሌሎችም የቤተሰቡ አባላት እሷ የተናገረችውን እንዲደግፉ ወያኔ ጫና እያደረገባቸው ነው።
በዚሁ መሰረት ጫና ተደርጎባችው ይሁን የብአዴን አባል በምሆናቸው ምክንያት ዶ/ር እንዳላማው የተባሉ የረዳት አብራሪው ወንድም ቪኦኤ ላይ ቀርበው ምንም እንኳን ወንድማቸው የአእምሮ ሁከትም ሆነ ጭንቀት እንዳለበት እሳቸው ባያውቁም እህቱ ያለችውን ግን ሙሉ ለሙሉ እውነት ነው ብለው ደግፈዋል። (ወይንም እንዲደግፉ ተደርገዋል)።
እንደተለመደው በቪኦኤ በኩል “ረዳት ፓይለቱ አእምሮው የታወከ፣ እብድ ነው” የሚለውን ዜና የሰራው ጋዜጠኛ ሄኖክ ሰማእግዜር መሆኑ የዘገባው መልዕት በወያኔዎች እንደተጠነሰሰ ይበልጥ የሚያረጋግጥ ነው።
ይህ በዚህ እንዳለ በጀርመን ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ረዳት አብራሪ ሀይለመድህን እንደ ወንጀለኛ እንዳይታይና ጥገኝነትም እንዲሰጠው በሚል የድጋፍ ሰላማዊ ሰልፍ ሊያደርጉ መዘጋጀታቸውን አሳውቀዋል።
Ethiopian Airlines flight hijacked by it's pilot

Friday, February 21, 2014

Ethiopian Airlines Hijacker Co-Pilot to Stand Trial

Swiss officials have revealed that the Ethiopian Airlines co-pilot, Hailemedhin Abera, who hijacked his own flight on Monday, will be charged for taking hostages.

A Swiss court has reportedly appointed a defence counsel for Abera and ordered that he is held in custody until his trial begins. However, his trial date is yet to be announced.
Reports have emerged that the 5-year employee of Ethiopian Airlines hijacked the flight heading from Addis Ababa to Rome by locking the pilot, who was visiting the washroom, from the cockpit.
Reports further indicate that Abera threatened to crash the plane if the pilot did not stop demanding entrance into the cockpit by knocking on its locked door.
Although earlier reports claim the 200+ passengers and crew of the Boeing 767 flight were largely unaware of the situation in the cockpit, new reports indicate otherwise.
According to reported accounts of passengers, oxygen masks were let down at some point and a distressed male voiced warned “sit down, sit down or I’ll take your oxygen.”
Reports further indicate that the flight attendants continued to hand out refreshments and reassure the disturbed passengers of their safety. All the passengers and crew members were reportedly safe.
On Wednesday, Alemu Asmamaw, an uncle of Abera, revealed to reporters that the the loss of a close relative of the airman had made him emotionally distressed.
His family has expressed shock at the news of his terror act, noting that he was a loyal employee of Ethiopia’s national airliner. However, they have also revealed that he had been withdrawn in the past year and reportedly revealed to them that he suspected he was being monitored.
The Boeing 767 plane Abera hijacked has been released to Ethiopian Airlines on Wednesday and everything has returned to normal at the Geneva airport he landed.
Swiss officials say an investigation is ongoing into the incident to create better understanding of the curcumstances surrounding the hijacking.
While pro-government supporters say authorities have been exonerated from direct complicity in the airman’s weird move, other pundits are calling for a revision of security protocols in aircrafts to prevent them from being taken over with such ease.

የብአዴን ድንጋጤና የእሁዱ የተቃውሞ ሰልፍ

-በአማራ ክልል የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የብአዴን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አለምነው መኮንን በአማራ ህዝብ ላይ የሰነዘሩትን ዘለፋ ተከትሎ የተነሳውን ተቃውሞ ለማብረድ የብአዴን የወጣቶች ሊግ ለአባለቱ  የስልጠና እና የግምግማ ስራ በባህር ዳር ፤ ደሴ እና ጎንደር እያከናወነ ነው።
የካቲት 16  አንድነትና መኢአድ በጋራ የጠሩትን ሰልፍ ተከትሎ በባህር ዳር ከተማ ባሉ ዘጠኝ ክፍለ ከተሞች 12 የገጠር ቀበሌዎች ብአዴን አባላቱ እና አባል ያልሆኑ  ወጣቶችን በግዳጅ በማስጠራት ባቀረበው የውይይት ሃሳብ እና መመሪያ በማህበራዊ ድረ ገፆች በሚተላለፉ ሃሰተኛ መረጃዎች ማንም ተወናብዶ ሰልፉን መቀላቀል እንደሌለበት አሳስቧል።
የጥፋት ሃይሎች የሚያስወሩት ሴራ ነው የሚለው ብአዴን፣ ሰልፉን ለማጨናገፍ ና ማህበረሰቡ በሰልፉ ላይ እንዳይገኝ ወጣቶች አስፈላጊውን ስራ መስራት እንዳለባቸው መክሯል።
የባህር ዳር ከተማ ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት ሃላፊ ወጣት ጌታቸው ብርሃኑ ባቀረበው ጽሁፍ የተሳሳቱ መረጃዎችን በማምጣት ህዝብ እና መንግስትን የማለያየት ስራ እየሰሩ በማለት ለወጣቶች ተናግሯል፡፡
የብአዴን ጽ/ቤ ሃላፊ የሆኑት አቶ እሱባለው መሰለ በበኩላቸው “የማህበራዊ ድህረ ገጾችን አትመልከቱ ችግር አለባቸው የሚያስተምሩት  ጥላቻ እና አመጽን ነው” በማለት ምክራቸውን ለግሰዋል።
“በማህበራዊ ድረ ገፆች በሚተላለፉ ሃሰተኛ መረጃዎች አንታለልም” የሚል መሪ ቃል ይዞ እየተከናወነ  ያለው ይህ ስልጠና ፣ ኢሳትንና ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን ማእከል አድርጎ የሚካሄድ ነው።
አንዳንድ ተሰብሳቢዎች ” በድምጽ የሰማነውን ጉዳይ አይን ባወጣ ውሸት እንዴት ይክዱናል” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የአቶ አለምነውን ንግግር ሳያስተባብሉ ” የብአዴን የወጣት ሊግ እና ታች ያሉ አመራሮች ወጣቱን ለማሳሳት መመኮራቸው ብዙ ተሰብሳቢዎችን አስደምሟል።”
አንዳንድ ወጣቶች ” መረጃውን ለምን ማህበራዊ ሚዲያ እና ኢሳት አቀረበው ብሎ ከመጥላት ለምን አቶ አለምነው ከ22 ሚልየን  በላይ የሚሆነውን ህዝብ ተሳደበ ብሎ” ውይይት አይከፈትም ነበር ሲሉ ተደምጠዋል።  ብአዴን ከህዝብ ይልቅ ግለሰብ ይበልጥብኛል በማለት ጉዳዩን እየሸፋፈነው ነው በማለት አንዳንድ አባሎቹ ለዘጋቢያችን ነግረዋታል።  የጎንደር መሬት ለሱዳን ተቆርሶ መሰጠቱን በተመለከተም ኢህአዴግ ተቃዋሚዎችን በመሳደብ  ስታራቴጅ ችግሩን ለማድበስበስ እየሞከረ መሆኑን ወታጦች መናገራቸውን ሪፖርተራችን ከባህርዳር ዘግባለች።
አቶ አለምነው የአማራው ህዝበ የትምክህት ለሃጩን ማራገፍ አለበት በማለት መናገራቸው ይታወቃል
አንድነትና መኢአድ እሁድ ለሚካሄደው ተቃውሞ በባህርዳር ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ሲሆኑ፣ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ ተቃውሞውን እንዲገልጽም ጠይቀዋል።

Thursday, February 20, 2014

መከላከያ የህዝብ ወይስ የህወሓት?

ህወሓት ደርግን ማሸነፍ ማለት የኢትዮጵያ ህዝብን ማሸነፍ ማለት ነው ብሎ ስለሚያስብ ተግባሩ ሁሉ የንቀት፣ የማንቋሸሽና የማዋራድ ስራ እየፈፀመ ይገኛል። ሌላውን ትተን ጥቂት የሻዕቢያ ተላላኪ የሆኑትን የህወሓት መሪዎች የግንጠላ አጀንዳቸውን ይዘው በረሃ የሸፈቱበት ቀን ልክ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም የትግራይ ህዝብ “ደደቢት ሂዳችሁ ታገሉሉኝ” ብሎ ወክሎ የላካቸው ይመስል “እኛ ታግለን ነፃ ስላወጣንህ እንደፈለግን እናደርጋሃለን” በማለት ዓይን አዉጣ በሆነ መንገድ ሰሞኑን “የካቲት 11 የትግራይ ህዝብ ዳግም ልደት ነው” እየተባለ በመከላኪያ ሰራዊት ታጅቦ በመከበር ላይ ስለሚገኘው የህወሓት አስቂኝ፣ አስገራሚና አሳዛኝ ድራማ የሚከተሉትን ጥቂት ነጥቦችን በአጭሩ እንመልከት።Ethiopian troops belongs to the ruling party TPLF/EPRDF
የህወሓት ድራማ ቁጥር 1.
የህወሓት መሪዎች እናስተዳድራለን የሚሉት 90 ሚሊዮን የኢ/ያ ህዝብ ነው እየገዙ ያሉት። ከፍተኛ ባለስልጣናቱን ጨምሮ ካድሬዎቻቸው፣ አባላቶቻቸውና ደጋፊዎቻቸው በቀጥታም ሆነ በስውር እየጋጡ ያሉት የኢትዮጵያ ህዝብ ሀብት ነው። የገጠሩን ትተን በሀሪትዋ ዋና ዋና ከተሞች ቁልፍ ቦታዎችን በመያዝ 90 ከመቶ የትግራይ ባለሀብቶች የቢዝነስ እንቅስቃሴያቸውን የሚያካሂዱትና ባለቤት የሆኑት በሌሎች ክልሎች ነው። በአጠቃላይ የሀገሪትዋ ሀብት በተለያየ መልኩ የተቆጣጠሩት የህወሓት መሪዎች፣ ካድሬዎችና አጃቢዎቻቸው ናቸው። በመሆኑም በመሬት ላይ ያለው ህዝቡ የሚያውቀው ሐቅ ይህ ሆኖ ሳለ እነሱ የሚሉን ግን “የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ነን” ነው። ልብ በሉ!! ስልጣን ላይ ያሉት እነሱ። ሀገሪቱን የተቆጣጠሩት እነሱ። ሀገሪትዋን እየዘረፉ ያሉት እነሱ። ነገር ግን ነፃ እናወጣለን የሚሉት ህዝብ አንድ ክልል ነው። ታዲያ!! ቆም ብሎ ላሰበውና ላስተዋለው ሰው ይህ መንግስት ከኛ አብራክ የወጣ ኢትዮጵያዊ መንግስት ነው ለማለት ያስችላልን?።

Wednesday, February 19, 2014

ሰበር ዜና አንድነትና መኢአድ የጠሩት የተቃውሞ ሰልፍ ብአዴንን አሳስቦታል “ስራ አጥ” ያላቸውን ወጣቶችን ዛሬ ሲያሳፍስ ውሏል

 የባጃጅ አሽከርካሪዎችም ሰልፉን እንዳይቀሰቅሱና እንዳይሳተፉ ማስጠንቀቂያ ደርሷቸዋል

አንድነት ፓርቲ ከመኢአድ ጋር በመሆን የጠራውና በመጪው ዕሁድ የካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ም ብአዴንን በመቃውሞ በሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ብአዴንን እንዳሳሰበውና በባህር ዳር ከተማ “ስራ አጥ” ያላቸውን ወጣቶችን ዛሬ ሲያሳፍስ መዋሉን ለክልሉ መንግስት ቅርበት ያላቸው የፍኖተ ነፃነት ምንጮች አጋለጡ፡፡
የፍኖተ ነፃነት ምንቾች እንዳጋለጡት በብአዴን ከፍተኛ ሹማምንት ትዕዛዝ በባህርዳር ከተማ ያሉ “ስራ አጥ” ወጣቶች ዛሬ ሲታፈሱ ውለዋል፡፡ አፈሳው በመንገድ ላይ ንግድ የተሰማሩና ኑሯቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ዜጎችንንም የጨመረ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን የብአዴን ካድሬዎች የባህር ዳር ከተማ የባጃጅ አሽከርካሪዎችንም በመሰብሰብ ሰልፉን እንዳይቀሰቅሱና  በተቃውሞ ሰልፉ ላይም እንዳይሳተፉ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋቸዋል፡፡
የባህር ዳር የባጃጅ አሽከርካሪዎች አንድነት ፓርቲ በሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ በባህርዳር ባደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ በራሳቸው ተነሳሽነት ቅስቀሳ ሲያሰርጉ እንደነበር ይታወሳል።

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ስልጣን ለቀቁ

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ስልጣን ለቀቁ

       የኦህዴድ ሊቀመንበርና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አለማየሁ አቶምሳ የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ፣ ምከር ቤቱ እንዳሰናበታቸው የመንግስት የመገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል። አቶ አለማየሁ መታመማቸው ከተዘገበ የቆየ ቢሆንም እስካሁን ከስልጣን ሳይወርዱ ቆይተው አሁን ለምን ለማንሳት እንደተፈለገ ግልጽ አይደለም።
በአፋር በቅርቡ በሚካሄደው የምክር ቤት ስበሰባ ላይ ፕ/ት አሊ ሴሮ ከስልጣን ሊነሱ እንደሚችል ለኢሳት የደረሱ መረጃዎች አመልክተዋል። ምንም እንኳ ኢሳት ከመንግስት በኩል መረጃውን በማግኘት ለማረጋገጥ ባይችልም፣ ህወሀት በአሊ ሴሮ ምትክ ሌሎች ሰዎችን ለመሾም ማቀዱን የሚያሳዩ ፍንጮች ደርሰውታል።

Saturday, February 15, 2014

የመኖሪያ ፈቃድ – ከራስ ወዳድነት ያልራቀው የስደተኞች የመጨረሻ ግብ

በሳዑዲ ለተፈናቀሉና ለተጎዱ ዜጎች የእንድረስ ምክክር በኦስሎ

oslo 9
ከራሳቸው አልፎ ባህር ውስጥ ቢደፉት የማይጎድል ሃብት አላቸው። ከሃብታቸው ብዛት የተነሳ ተጨማሪ የነዳጅ ክምችት አግኝተው ጉድጓድ ለመቆፈር ተቃውሞ በመነሳቱ ሪፈረደም አካሂደዋል። ከነዳጅ ይልቅ ውሃ ውስጥ ያለው ህይወት አንደሚብስባቸው በማስታወቅ ድምጽ የሰጡ በመብዛታቸው ነዳጁ ባለበት እንዲቆይ ተወስኗል። ይህ ዜና በተሰማበት ሰሞን ያልተገረመ አልነበረም። ሃብት ካለ ምን ችግር አለ? አንግዲህ እንደዚህ “ብር ይብቃን፤ አሳና የባህር ውስጥ ፍጡራን እንቁራሪትን ጨምሮ ይበልጡብናል” የተባለባት አገር ኖርዌይ ናት።
በተቃራኒው ደግሞ ብር ካየ የሚገባበትን ጉድጓድ፣ የሚፈጽመውን ጥፋት የማይለካው ኢህአዴግ የሚመራት ኢትዮጵያ ያፈራቻቸው ስደተኞች ኖርዌይን ተጠልለዋል። ከአራት ሺህ በላይ ወገኖች ኖርዌይ በጡረታ መልክ እየቆረሰችላቸው ወይም ስራ እየሰሩ ህይወታቸውን ይመራሉ። በኖርዌይ መወልወያና መጥረጊያ ይዘው ቀን የሚገፉ “ራፐሮች”፣ አዛውንቶችን የሚንከባከቡ ሞግዚቶች፣ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና የስራ እርከን የሚሰሩ ባለሙያዎች አንዲሁም በስደተኞች ካምፕ ተጠልለው የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ወገኖች በየዘርፉ በብዙ መልክ ተመድበው ይኖራሉ።
አብዛኞቹ የመኖሪያ ፈቃድ ባለቤቶች ከፖለቲካ ድርጅቶችና ከሲቪክ ማህበራት በተሰጣቸው የአገልግሎት የድጋፍ ደብዳቤና ክትትል ቢሆንም መልስ ካገኙ በኋላ ወገናቸውን መልሶ ከመርዳት የውሃ ሽታ ሆነው እንደሚቀሩ ይነገራል። “በኢትዮጵያ አምላክ ያዙኝ ልቀቁኝ” በማለት የትግል ችቦ ለኳሽ፣ አቀጣጣይ፣ መሪና አስተናባሪ መስለው የሚፈልጉትን እስኪያገኙ በርተው ስለሚጠፉ በድፍረት የሚነሳ obang 2ጉዳይ ባይሆንም አቶ ኦባንግ ሜቶ አምርረው የተናገሩበት ጉዳይ ነበር። እዚህ ላይ ሊሰመርበት የሚገባው ትልቅ ጉዳይ የመኖሪያ ፈቃድ በነበራቸውም ሆነ ባልነበራቸው ወቅት ወገኖቻቸውን፣ አገራቸውን እንዲሁም ቃል ኪዳናቸውን ሳይዘነጉ ባሉበት የዓላማ አለት ላይ ሆነው ስራቸውን የሚሰሩ ምርጦችም የመኖራቸው እውነት ይሆናል።

Thursday, February 13, 2014

በርካታ ወጣቶች ወደ ማዕከላዊ እስር ቤት እየተጋዙ ነው

ኢህአዴግ አሸባሪ ካላቸው ግንቦት ሰባት እና ሌሎች ፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ በርካታ የአዲስ አበባና አማራ ክልል ወጣቶች ወደ ማዕከላዊ እስር ቤት እየተጋዙ መሆኑን የአይን እማኞች ተናገሩ፡፡
ኢህአዴግ በጀመረው አዲስ አሰሳ በሀገሪቱ አንድንድ ቦታዎች ኢንተርኔትን ጨምሮ ስልክ እንዳይሰራ የተደረገ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎችም የመከላከያ ሀይል ተበትኗል፡፡ የዚህን ዜና ዝርዝር  በሌላ ጊዜ ይዘን እንቀርባለን። በሌላ ዜና ደግሞ ብአዴን ከፍተኛ የሞራል ውድቀት የደረሰበት መሆኑን ምንጮች ገለጹ።
የብአዴን የጽፈት ቤት ሃላፊ እና የአማራ ክልል ም/ል ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ አለመነው መኮንን የሚመሩት ህዝብ  ጸያፍ ስድብ መሳደባቸውን ተከትሎ ብአዴን የሞራል ውድቀት እንደደረሰበት ከክልሉ የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
የክልሉ ህዝብ ያሳየው ቁጣና በብአዴን የንግድ ድርጅቶች ላይ የጣለው ማእቀብ ያሰጋቸው አቶ በረከት ስምኦን ወደ ባህርዳር በማቅናት ፣ የደረሰውን ኪሳራ ለመቋቋም ያስችላሉ የሚሉዋቸውን አማራጮች ሁሉ ለመጠቀም ከሌሎች አመራሮች ጋር እየመከሩ ናቸው።
የብአዴን አመራሮች ባደረጉት የመጀመሪያ ግምገማ “የአማራ ህዝብ ፊት ለፊት የምንናገረውና ከጀርባ የምንናገረው ነገር የተለያየ ነው” ብሎ እንዲያስብና እምነቱን እንዳይጥልብን አድርጓል” ብለዋል። ብአዴን በመጪው ምርጫ ላይ በክልሉ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ኪሳራ ሊደርስበት እንደሚችልም በግምገማው ወቅት ተነስቷል።
የክልሉ ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአማራ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፣ በኢሳት የቀረበው የአቶ አለምነው ድምጽ አይደለም ብለው ማስተባበል ሳይችሉ ቀርተዋል። ፕሬዚዳንቱ በባህርዳር ስብሰባ መካሄዱንና ድምጹም በጊዜው የተቀረጸ መሆኑን በተዘዋዋሪ መንገድ ያመኑ ሲሆን፣ መክትላቸው የተናገሩትን በቀጥታ ከማስተባበል ይልቅ አቶ አላምነው ለአማራው ህዝብ ስላላቸው ፍቅር መግለጽን መርጠዋል።

ተዋርዶ መገዛት ይብቃን!

የወያኔ ሹማምንትና አደርባይ ሎሌዎቻቸው አንገቱን አስደፍተው የሚገዙትንና የሚዘርፉትን ህዝብ ይበልጥ ስብእናውን አዋርደው ሊገዙት ለምን እንደሚፈልጉ የማይገባን ጥቂቶች አይደለንም። እነዚህን ግፈኞች ቀረብ ብሎ ላያቸው ግን ይህ ድርጊታቸው እንቆቅልሽ አይደለም።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ህዝብ አይሰማንም ብለው በር ዘግተው ከሚያካሂዷቸው ጉባኤዎች እያፈተለኩ የሚወጡ የቪዲዮና የድምጽ መረጃዎች የነዚህን ግፈኞች ስነ ህሊና ግልጽ አድርገው ያሳያሉ።

ከወራት በፊት የሶማሊያ ክልል ፕሬዝዳንት የሀገር ሽማግሌ ሰብስቦ የወያኔ አላማ ከእሱ ጎሳ ጋር ተባብሮ ሌላውን ብሄረሰብ የበታች አድርጎ መግዛት መሆኑን ሲናገር የሚያሳይ ቪዲዮ ተመልክተን ነበር። የክልሉን ህዝብ የሚጨፈጭፈው ለዚህ ሲባል መሆኑን ለማሳመን ነበር በሩን ዘግቶ የተናገረው።
ሰሞኑን ደግሞ አንድ የአማራ ክልል የወያኔ ሹምና ሎሌ አንደ እንደሶማሌ ሹም ካድሬዎቹን ሰብስቦ በአማራው ህዝብ ላይ ተሳለቀ፤ ለ እግራቸው ጫማ የላቸውም በሚላቸው የአማራው ተወላጅ ላይ ለሰሚ በሚሰቀጥጥ ቋንቋ ያወርደው የነበረ ስድብ የሚነግረን ተጨማሪ ነገር ተመሳሳይ የወያኔን ምንነትን ነው።

Wednesday, February 12, 2014

በ500 ብር ደሞዝ የሚተዳደረው የህወሃት ታጋይ ከ10 ሚሊዮን ብር ያላነሰ ሃብት ማካበቱ ተገለጠ

የደህንነት ሃላፊ ከነበሩት ከአቶ ወልደስላሴ ወልደ ሚካኤል  ጋር በግብረ-አበርነት የተከሰሱት የህወሃት ታጋዮች ከደሞዛቸው ጋር ፈጽሞ የማይመጣጠን ሃብት አግበሰው መገኘታቸው ታውቋል።
በተለያዩ አለመግባባቶች የተነሳ እየተመሰረቱ ያሉ ክሶች የህወሃት ተጋዮች በህገወጥ መንገድ የሰበሰቡትን የሃብት መጠን ለማወቅ እየረዳ መሆኑን የገለጸው ዘጋቢያችን ከአቶ ወልደስላሴ ጋር በግብረ አበርነት የተከሰሱት የህወሃት ታጋዩ የአቶ ወልደስላሴ ወንድም አቶ ዘርአይ ወልደስላሴ የመከላከያ ሚኒስቴርን ሲለቁ በመጨረሻ ይከፈላቸው የነበረው ወርሃዊ ደሞዝ 532 ብር ብቻ እንደነበር አመልክቷል ፡፡  ይሁንና፣ ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ባደረገው ማጣራት ግለሰቡ በተለያዩ ባንኮች በስማቸው 5 ሚሊዮን ብር ከማስቀመጣቸውም በተጨማሪ፣ አዲስ አበባ ቤቴል ሆስፒታል አካባቢ በ74 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ግንባታ እያካሄዱ ፣ በአፋር ክልል ደግሞ ከ1 ሚሊዮን 400 መቶ ሽ ብር በላይ በሆነ ወጪ የእርሻ ኢንቨስትምንት እያከናወኑ መሆናቸው እንዲሁም  በስማቸው 2 ሚሊዮን 700 ሺ ብር ግምት ያላቸው 2 ሎደር መኪኖች መገኘታቸውን ገልጽዋል።
የአቶ ወልደስላሴ እህት የሆኑት ወ/ሮ ትርሃስ ደግሞ የ8ኛ ክፍል ተማሪና ምንም ስራ ያልበራቸው ሲሆን፣ በወንድሞቻቸው ድጋፍ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገዛ አንድ ስካቫተር፣መኪና እንዲሁም   በአዲስ አበባ በየካና ቦሌ ክፍለ ከተሞች፣ በለገጣፎ፣ መቀሌና አክሱም 3 ሺ 266 ካሬ ሜትር ቦታዎች በስማቸው መገኘቱ ተመልክታል ፣እንዲሁም  በተለያዩ ባንኮችም 8 ሚሊዮን ብር ተቀማጭ ማድረጋቸውን  አንድ ተጨማሪ ዘመናዊ መኪና በስማቸው ተመዝግቦ መገኘቱን ጸረ ሙስና ኮሚሽን በምርመራ አረጋግጧል።
ዋናው ባለስልጣን አቶ ወልደስላሴ ደግሞ ስራ ሲጀምሩ ደሞዛቸው 1600 ብር የነበረ እና በእድገት እስከ 6000 ሺ ብር ሲከፈላቸው የቆየ ቢሆንም ያካባቱት ሀብት ግን ፈጽሞ ከደሞዛቸው ጋር የማይመጣጠን ነው ተብሏል። ባለ 4 ፎቅ ህንጻ ባለቤት የሆኑት አቶ ወልደስላሴ በ1 አመት ከ2 ወራት ቤቱን አከራይተው 790 ሺ ብር ገቢ አግኝተዋል።
አቃቢ ህግ ያቀረበውን ክስ የእስረኞች ጠበቆች፣ አዲስ የተጨመረ ክስ ነው በማለት አቤቱታ አቅርበዋል።
አቶ ወልደስላሴ ከወ/ሮ አዜብ ጋር በነበራቸው መቀራረብ ከፍተኛ ሃብት ማፍራታቸውን ፤ አቶ መለስ ዜናዊ ከሞቱ በሁዋላ ግን የእርሳቸው ዋነኛ ተቀናቃኝ የሆኑት የደህንነቱ ዋና አዛዥ አቶ ጌታቸው አሰፋ ግለሰቡን በሙስና ከሰው እንዳሳሰሩዋቸው አንዳንድ የመገናኛ ብዙሀን ገልጸው ሲዘግቡ ቆይተዋል።
ህወሃቶች እርስ በርስ በሚያደርጉት ሽኩቻ እየተካሰሱ ፍርድ ቤት መቅረባቸው የካበቱትን ሃብት ለማወቅ እየረዳ ነው የሚለው ዘጋቢያችን፣ በጸረ ሙስና ኮሚሽን ያልተመረመረና በፍርድ ቤት ቀርቦ ያልታወቀ ከዚህም የባሰ የሙስና ታሪክ እንደሚኖር መገመት ይቻላል ሲል አስተያየቱን አስፍሯል።

አቶ አለምነው መኮንን መኖሪያ ቤት በድንጋይ ተደበደበ,,

1507855_406582846154533_728831923_n
የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የብአዴን ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን መኖሪያ ቤት በድንጋይ መደብደቡን የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ጠቆሙ፡፡ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች እንጠቆሙት ባሳለፍነው ሳምንት የካቲት 1 እና የካቲት 2 ቀን 2006 ዓ.ም(ቅዳሜና እሁድ) ለሊት በተደጋጋሚ ማንነታቸው ባልታወቀ ግለሰቦች መኖሪያ ቤታቸው በድንጋይ መደብደቡን ተከትሎ ቤታቸው ቀንና ለሊት በፖሊስ እየተጠበቀ ይገኛል፡፡
አቶ አለምነው መኮንን የአማራን ህዝብ የሚያዋርድና የሚዘልፍ ንግግር ሲያደርጉ የተቀዳ ድምፅ ለህዝብ ይፋ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ በብአዴን ውስጥ የንትርክ ምክንያት መሆናቸው አይዘነጋም፡፡

ሰው ለሆኑ ሰዎች በሙሉ! (በጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፤ ከዝዋይ ማረሚያ ቤት)

የነገሮች ሁሉ መድረሻ እስር ቤቶች እየሆኑ መጥተዋል፡፡

‹‹ይህንን ስለመሳሰሉ ጉዳዮች መወያየት ክልክል ነው፡፡›› በማለት በተንጎላጀጀ ድምፅ ጠባቂው ተናገረ፡፡ ቀጠል አደረገናም ‹‹መነጋገር የምትችሉት ስለቤተሰብ ጉዳዮች ብቻ ነው›› በማለት ተናገረ፡፡ ይህን ከላይ ያለውን ሐሳብ የሚመለከት ማንኛውም አንባቢ፣ ጉዳይ የተፈፀመው እዚህችው እማማ ኢትዮጵያ ሰማይ ስር ባሉ አጃኢበኛ እስር ቤቶች፣ ቤተሰብ መጠየቂያው እንደሆነ መጣራቱ አይቀርም፡፡
ይሁንና በመግቢያው ላይ ያለው ጽሑፍ ተቀንጭቦ የተወሰደ ‹እናት› ከተሰኘውና እ.ኤ.አ. በ1906 ከታተመው የስመ ጥሩው ሩስያዊ ደራሲ ማክሲም ጎርኪይ ታሪካዊ ልቦለድ ገፅ 102 ላይ ነው፡፡ የዛሬ 108 ዓመት አካባቢ ማለት ነው፡፡ አቤት ርቀቱ!… ይህ ርቀት ግን ለእኛ ምንም ማለት ያልሆነ ይመስላል፤ ለምን? ቢሉ ዛሬም ይህንንና ይህን የመሳሰለውን አስፍተን እየሠራን እንገኛለን፡፡ እንዲያውም በአንዳንድ ሁኔታዎች እየተጓዝን ያለነው የቁልቁለት ሩጫ በእጅጉ አሳሳቢ ሆኖ ይገኛል፡፡

በደብረዘይት አየር ኃይል አባል የነበረው ምክትል መቶ አለቃ ዳንኤል የሽዋስ ሥርዓቱን በመቃወም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊትን ተቀላቀለ

አምባገነኑ የወያኔ ቡድን የታጠቀ ኃይሉን መከታ በማድረግ ንጹሃን ዜጎችን ያለ አግባብ እየጨፈጨፈ የስልጣን ዕድሜውን ለማስቀጠል የሚያደረገውን እንቅስቃሴና በሰራዊቱ ውስጥ የነገሰውን የአንድ ቡድን የበላይነት በመቃወም የደብረዘይት አየር ኃይል አባል የነበረውና L-39 ስኳድሮን ተዋጊ ጀት አብራሪ የነበረው ም/መ/አለቃ ዳንኤል የሽዋስ አገዛዙ የሚያደርስበትን ጭቆናና እንግልት ይበቃል በማለት  ወደ ኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር  ተቀላቅሏል።Ethiopian People Patriots Front - EPPF
በደብረዘይት አየር ኃይል አባልና L-39 ስኳድሮን ተዋጊ ጀት አብራሪ የነበረው ም/መ/አ ዳንኤል የሽዋስ ተቃዋሚዎችን ትደግፋለህ ከእነሱም ጋር የጠበቀ ግኑኝነት አለህ በሚል ምክንያት ተጠርጥሮ ያለምንም ወንጀል ለአምስት ወር ያህል ታስሮ እንደነበርና ከእስር እንደተለቀቀም በወያኔ የደህንነት አባሎች አማካኝነት በአይነ ቁራኛ ክትትል ይደረግበት እንደነበርም አስታውቋል።
በም/መ/አ ዳንኤል የሽዋስ የወያኔው የደህንነት አባሎች ጥላቻና ጥርጥር ምክንያት እንደገና ከተቃዋሚ ኃይሎች ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን ደርሰንበታል በማለት ወደ እስር ቤት እንዳስገቡትና ለ23 ቀናት በደብረዘይት እስር ቤት ከቆየ በኋላ ከእስር ቤት አምልጦ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊትን መቀላቀሉን ገልጿል።
በሌላ ዜና በሁመራ አካባቢ የሚኖሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ደጋፊዎች ናችሁ በማለት ታስረው የነበሩ 10 ሰዎች ላይ ከ6 ዓመት እስከ 25 ዓመት በመፍረድ ወደ መቀሌና ሽሬ እስር ቤት እንደወሰዱዋቸው ታውቁዋል።
በመቀሌ እስር ቤት በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ደጋፊነትና በተለያየ የአሸባሪነት ሰበብ እየፈጠረ የሚያስረው የወያኔው አገዛዝ በመቀሌ እስር ቤት ብቻ 36,900 እስረኛ የሚገኝ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 4500 የሚሆኑት ሴቶች እንደሆኑ ታውቋል።
በዚሁ እስር ቤት ሰዎችን በሌሊት እየቀሰቀሱ በመውሰድ ደብድበው የሚመልሱ ሲሆን፣ አንዳንዶች ደግሞ በዚያው እንደወጡ እንደሚቀሩ ከአካባቢው የተገኘ መረጃ ያመለክታል።
የወያኔ ካድሬዎችም በዚሁ በመቀሌ እስር ቤት ውስጥ በሚገኙ ሴቶች ላይ የወሲብ ጥቃት እንደሚፈጽሙባቸው የታወቀ ሲሆን፣ በዚህም ምክንያት ሁለት ሴቶች መፀነሳቸውና አስፈላጊውን እንክብካቤ ባለማግኘታቸው ሕይወታቸው እንዳለፈ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በዳንሻ አካባቢ በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ስም በሕዝቡ ላይ እያደረሰ ያለው እንግልት ተጠናክሮ ቀጥሏል።
የወያኔው ገዥ ቡድን በዚሁ አካባቢ እየደረሰበት ባለው ወታደራዊ ጥቃት ሳቢያ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር እንደ ምሽግ የሚጠቀመው እናንተን ነው በማለት የአካባቢውን ህብረተሰብ ያሰቃይ እንደነበር ይታወሳል።
በአሁኑ ወቅት ብዛት ያላቸው የዳንሻና የአካባቢው ነዋሪዎችን እያሰረ ሲሆን፣ የሚሰጠው ምክንያት ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ያስታጠቃችሁን መሣሪያ አምጡ፣ ከእነሱ ጋርም ቀጥተኛ ግኑኝነት እንዳላችሁም ደርሰንበታል በሚል ወደ እስር ቤት እያጎራቸው ይገኛል።

Tuesday, February 11, 2014

በየትም አገር የአሸባሪነት ህግ አለን የሚሉ ዜጎቻቸውን አያጠምዱበትም!!!


አሜሪካ ውስጥ ያፈንዳ የገደለ ይተኮሰ የፈጀ .... አሜሪካዊ ዜጋ አሸባሪ ተብሎ ሲከሰስ ሲዘለፍ አላየንም ይልቅ እብድ ንክ ምናምን በሚል ከእስር ቤት ወደ 

ፍርድ ቤት እና ምርመራ ይሄዳል:: አሜሪካንም እኮ የአሸባሪዎች ህግ አላት:: ሆኖም ዜጎቿን አታጠምድበትም:: ከሌላ አገር ዜጋ ጋር አያይዛ ቲለጥፈዋለች 

... የአሜሪካ ዜግነት እንኳን ቢኖረው ኦሪጂኑን ነው የምትጠራው እንጅ አሜሪካዊ አሸባሪ ብላ አደባባይ ዜጎቿን በንዝህላልነት አታስርም አትገልም 

አታንገላታም:: ሌሎችም አገራት እንዲሁ ...በአሸባሪነት ህግ ዜጋን አያጠምዱም :: የአሸባሪነት ህግ ከምንጩ በአሸባሪነት አሜሪካን የመዘገበቻቸውን አሸባሪ ድርጅቶች (ሕወሓትን ይጨምራል) ለመዳኘት የወጣ ነው::



እዚህ ጋ ግን ሲመጡ እኛ አገር የህጉ ትርጉም ለየት ብሎ እያየነው ነው::በዚህ ህግ ይዳኛሉ የተባሉት እነ አልቃይዳ እና የታጠቁ መሰሎቹ ሳይሆኑ የተዳኙበት የራሳችን ዜጎች የሆኑ ኢትዮጵያውያን ያውም ያልታጠቁ ብእር እና ወረቀት ያነገቡ የህዝብን ነጻነት እና መብት ያስተማሩ ወዘተ... ናቸው:: በአለም አቀፍ ደረጃ አሸባሪነትን ለመቆጣጠር የተባለው ዜጎችን ማጥመድ መሆኑ አሳሳቢነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ በሃገራችን አሸባሪነ የተባሉት ግን የማናውቃቸው ሰዎች ሳይሆኑ መንግስትን በይፋ የተቃወሙ ለውጥ የጠየቁ የፖለቲካ መሪዎች ጋዜጠኞች እንዲሁም ሃይማኖታዊ ነጻነታቸውን የጠየቁ የሃይማኖት ምሁራን ናቸው::እንዲሁም የሰብኣዊ መብታቸው ተጥሶ ከህጉ ውጪ በላያቸው ላይ ከባድ እና አደገኛ የሆነ ፕሮፓጋንዳ እየተካሄደባቸው ሳይመሰከርባቸው እና ማስረጃ ሳይቀርብባቸው ወንጀለኛ ተደርገው እንዲታዩ ተደርጓል::

ይህ የሽብር ህግ በተለያየ ጊዜ እንዲስተካከል እና እንዲለወጥ እንዲሻሻል ዜጎችን ማጥመድ እንዲያቆም .. የተለያዩ ቡድኖች አገሮች እና ኢትዮጵያውያን የገዛ የወያኔ ስርኣት አባላት ሳይቀሩ እየተናገሩ ነው :: ግን የወያኔው ጁንታ ይህንን ለስልጣን ማስረዘሚያ እና ለተቃዋሚዎች ማፈኛ እየተጠቀመበት ነው::በአለም አቀፍ ደረጃ አሸባሪ እንደሆነ የሚታወቀው ሕወሓት ምእራባውያን እየነቁ እንዳይነቁ አድርጎ እያጭበረበራቸው በሚያገኘው የብድር እና የእርዳታ ገንዘብ ዜጎችን ለማፈን እና ለመግደል እየተጠቀመበት ነው::ይህ የሽብር ህግ የማያፍናቸው አፋኞቹን የአገሪቱ ባለስልጣናት እና በተቃዋሚ ውስጥ የተሰገሰጉ ባላንጣዎችን የሚያሳፍኑ ብቻ ነው::

ይህንን ህግ በተመለከት መፍትሄ ከማምጣት ይልቅ በየጊዜው ለማፈኛነት መጠቀምን የመረጠው የወያኔ ጁንታ ከትግራይ እስከ ሞያሌ ከጋምቤላ እስከ መልካጀብዱ እና ጎደ በሃገሪቱ በተለያዩ ማእዘናት ዜጎችን በማሳደድ ሰርተው እንዳይኖሩ እንዲፈናቀሉ የፖለቲካ እምነታቸውን እንዳያራምዱ እንዳይጽፉ እንዳያነቡ በማድረግ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ሽብርን እየነዛ አሸባሪ እያረገ በማሰር ከአገር ተሰደው እንዲወጡ በማድረግ እና በመግደል ጭምር ወንጀል እየፈጸመ ስለሚገኝ ህዝቦች በጋራ ታግለን ስርኣቱን መቃብር ልንከተው ይገባል::

Monday, February 10, 2014

የአቶ አሥራት ጣሴ እስር የኢህአዴግ የጉልበት ፖለቲካ ማሳያ ነው!

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ የተሠጠ መግለጫ
UDJ SEAL
ፓርቲያችን አንድነት በተደጋጋሚ ከገዥው ፓርቲ ህግን ከለላ በማድረግ እና የመንግስትን ሥልጣን በመጠቀም የሚደርስበትን ከፍተኛ አፈና ተቋቁሞ የኢትዮጵያን ህዝብ ሉዓላዊ የስልጣን የበላይነት ለማረጋገጥ ትግሉን አጠናክሮ መቀጠሉ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡
በተለይም ፓርቲያችን በመላው የሀገራችን ክፍል የዘረጋውን መዋቅር በህዝባዊ አቅም ወደ ተሻለ ደረጃ በማሸጋገር በአምስት ዓመት ስትራተጂክ ዕቅዱ መሰረት እያከናወነ ያለው ህዝባዊ ንቅናቄ እና በተሳካ ሁኔታ ጠቅላላ ጉባዔ አካሂዶ ዴሞክራሲያዊ የአመራር ሽግግር ማድረጉ በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ ትልቅ ተስፋ ያሳደረ ቢሆንም ገዥውን ፓርቲ በአንጻሩ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደከተተው ይስተዋላል፡፡
ኢህአዴግ ቀደም ሲል የፓርቲያችንን እንቅስቃሴ በመከታተል ከከፍተኛ አመራሮች መካከል አቶ አንዱዓለም አራጌ፤ ናትናዔል መኮንን እና ሌሎች በርካታ አባላትን የተለያየ ምክንያት ፈጥሮ እየወነጀለ ለእስር መዳረጉ የሚታወቅ ነው፡፡ ይህም በድንገት የተደረገ ሳይሆን የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር እና የኢህአዴግ ሊቀመንበር አቶ መለስ ዜናዊ በግልጽ በፓርላማ ተገኝተው ‹‹አንድነት ፓርቲ እግር ሲያወጣ እግሩን እንቆርጣለን›› ባሉት መሰረት የፈጸሙት ነበር፡፡
አሁንም የራዕያቸው አስቀጣይ ነን የሚሉ የገዥው ኃይሎች ፈለጋቸውን ተከትለው የአውራ ፓርቲ (የአንድ ፓርቲ ስርዓት) ለመገንባት አንድነትን በጉልበት ፖለቲካ ማጥፋት እንደ ብቸኛ መንገድ ወስደው እየተረባረቡ ይገኛሉ፡፡ በመላው የሀገራችን ክፍል በርካታ አባሎቻችን ከስራ ተፈናቅለዋል፤ በግፍ ከሀገራቸው እንዲሰደዱ ተደርገዋል፤ ታስረዋል፤ ተደብድበዋል፡፡ ይህም በየጊዜው በፓርቲያችን ልሳን በመረጃ ተደግፎ ለህዝብ ይፋ የተደረገ ሲሆን፤ በአጠቃላይ በፓርቲያችን አመራር እና አባላት ላይ የተፈጸመውን የሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰት ባመላከትንበት ሪፖርትም ተካተቶ ለህዝብ ይፋ ተደርጓል፡፡
በተለይም የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት በሚል የተካሄደውን ህዝባዊ ንቅናቄ ተከትሎ ፓርቲያችን በተንቀሳቀሰባቸው አሥራ አንድ የሀገራችን ከተሞች ጉልህ ሚና የተጫወቱ እና በህዝብ ተቀባይነት ያላቸውን አባላት ምክንያት እየፈጠሩ እና የፍትህ ስርዓቱን የፖለቲካ መሳሪያ እያደረጉ ለእስር እና ለእንግልት መዳረጉን አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡
ኢህአዴግ ገና በጊዜ የጀመረው የ2007 ዓ.ም የምርጫ ዘመቻ የተለመደውን የጉልበት ፖለቲካ የተከተለ ሲሆን በቅርቡ በምዕራብ ሸዋ ዞን ለንሴቦ ወረዳ አቶ አለማየሁ ለሬቦ የተባሉ የሲተዳማ ዞን የአንድነት ስራ አስፈጻሚ በአዲስ አበባ ተገኝተው የፓርቲ ጉባኤ ተሳትፈው ሲመለሱ በቁጥጥር ስር ውለው ለ22 ቀናት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በእስር ቤት ከተሰቃዩ በኋላ መንግስትን ሰድበዋል የሚል ክስ ተመስርቶባቸው በዋስ ተለቀዋል፡፡ ይህንን ተከትሎ በየካቲት 30 ቀን የፓርቲያችን ከፍተኛ አመራር (የብሄራዊ ምክር ቤት አባል) የሆኑት አቶ አስራት ጣሴ ፍርድ ቤትን ዘልፈዋል ተብለው ለእስር የተዳረጉ ሲሆን ሌሎች አራት ከፍተኛ የፓርቲ አመራሮች ሊታሰሩ ሴራ እየተሸረበባቸው መሆኑን ምንጮች ለፓርቲያችን እያረጋገጡ ይገኛሉ፡፡
የፍትህ ስርዓቱን ዋነኛ የፖለቲካ መሳሪያ ያደረገው የኢህአዴግ መንግስት አቶ አስራት ጣሴን ለማሰር እንደ ምክንያት የተጠቀመው በአዲስ ጉዳይ መጽሄት 197 ቅፅ 7 ያወጡትን ጽሑፍ ሲሆን አጠቃላይ መልዕክቱም በኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ የሌለ መሆኑን፤ ህጎች አፋኝ መሆናቸውን፤ ኢ.ቲቪ የሰራቸው አኬልዳማ፤ ጀሃዳዊ ሃረካትና ሌሎች ለፖለቲካ ጥቃት ማድረሻ የተቀነባበሩ ድራማዎች ህገ ወጥ መሆናቸውን የሚገልጽ ነው፡፡ ይህ የፍትህ ጥያቄ ደግሞ አቶ አስራት ጣሴ ገና በጠዋት ለትግል የወጡበት፤ ከመሰሎቻቸው ጋር ሆነው አንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍት ፓርቲ እንዲመሰረት በርካታ መስዋዕትነት የከፈሉበት የፖለቲካ አላማቸው እና የፓርቲ አቋም መሆኑ ይታወቃል፡፡
‹‹የኢህአዴግ መንግስት ከሚመራቸው ፍርድ ቤቶች ፍትህ ይገኛል ብለን ሳይሆን ለታሪክ እንዲመዘገብ ወደ ፍርድ ቤት እንሄዳለን›› ሲሉም የግል ሃሳባቸው ብቻ ሳይሆን በብዙ አንቀጽ የተጠቀሰ የፓርቲያቸው አቋም ስለመሆኑም ማሳያ ነው፡፡ ከዚህም በላይ ኪሊማንጃሮ የተባለው ድርጅት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር በመንግስት ተቋማት ላይ ያደረገው ጥናት እንደሚያሳየው በህዝብ ከማይታመኑ ተቋማት መካከል ፍርድ ቤቶች በአንደኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡ ናቸው፡፡
ከነዚህ በህዝብ ከማይታመኑ ተቋማት ፍትህ አይገኝም ብሎ ማመን እና እምነትን መንገርም ሆነ መጻፍ ህገ መንግስታዊ መብት መሆኑ እየታወቀ በአካል ባልተገኙበት ችሎት በአካል ተገኝቶ ችሎትን ያወከ ወይም የዘለፈ በሚቀጣበት ፍታብሔር አንቀጽ 480 ቀርበው እንዲያስረዱ ከተጠሩ በኋላ ለእስር ተዳርገዋል፡፡ ይሁን እንጂ የተጠሩበት የፍታብሔር አንቀጽ የሚያዘው ጥፋታኛ ሆነው የተገኙ ቢሆን እንኳ በአነስተኛ የገንዘብ መቀጮ የሚቀጣ እንጂ ለእስር የሚያበቃ አልነበረም፡፡
ኢህአዴግ ይህንን እያደረገ ያለው ቀናቶች ወደ 2007 ዓ.ም ምርጫ እየገሰገሱ እና ፓርቲያችንም በህዝባዊ አቅሙ እየጎለበተ በመምጣቱ ካለቃቸው እንደተማሩት እግር ያወጣ ፓርቲያችንን እግር በመቁረጥ፤ አመራሩን ህግን ከለላ አድርገው ለእስር በመዳረግ፤ እንዳይጽፍ፤ እንዳይነገር እና በፍርሃት ቆፈን ተይዞ አንገቱን እንዲደፋ በማድረግ በምርጫ ሜዳው ከጀሌዎቻቸው ጋር ሩጠው አሸንፈናል ብሎ ለማወጅ የሚደረግ አስነዋሪ ዘመቻ ነው፡፡
ነገር ግን እንዲህ ያለው አምባገነናዊ ተግባር ትግላችንን የበለጠ አጠናክረን በመግፋት ሰላማዊ ትግሉ የሚጠይቀንን መስዋዕትነት ለመክፈል የሚያበረታን እንጂ ወደኋላ የማይመልሰን መሆኑን ዛሬም እንደ ትላንቱ ለመላው ህዝባችን እናረጋግጣለን፡፡
የፍትህ ስርዓቱም ከአንድ ፓርቲ ወገንተኝነት እንዲወጣ እና በግፍ የታሰሩ አመራሮቻችንንም በነጻ እንዲያሰናብት እንጠይቃለን !!!!
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!