Search This Blog

Sunday, February 9, 2014

አረናዎችን ለመግደል ህወሓት እያሴረ ነዉ ተባለ


ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለመዋሃድ ንግግር እያደረገ ያለው የአረና ፓርቲ፣ ከሕወሃት ጋር ከፍተኛ የሰላማዊ ትግል ትንቅንቅ ላይ እንደሆነ በስፋት እየተነገረ ነዉ። በቅርቡ በአዲግራት ሊደረግ ታስቦ በነበረዉ ሕዝባዊ ስብስባ ከሌላ አኡራጃዎች የመጡ የሕወሃት ካድሬዎችና ዱርዬዉን ድንጋይ እየወረወሪ ሲበጠብጡ፣ የአመራር አባላትን ሲደበድቡ እንደነበረ የሚታወስ ነዉ። ህወሃት እነዚህ ዱርዮዎችን አሰማርቶ የሽብር ተግባራትን በመፈጸሙ ምክንያት፣ ስብሰባዉን ማድረግ ካለመቻሉ የተነሳ፣ የአዲግራት ሕዝብ አማራጮችን እንዳይሰማ ተደርጓል።
በተመሳሳይ ሁኔታ በሁመራ ሕወሃት በሕግ ተፈቅዶ የተጠራን የአረና ስብሰባ በኋይል ለማጨናገድ ችሏል። አረናዎች ሳይታክቱ በየከተሞቹ የሚያደርጉት ሰላማዊ እንቅስቃሴዎች ፣ በሌላ ብኩል ደግሞ ህወሃት እያሳያቸው ያለው ፍጹም ጸረ-ሰለማ እና ጸረ- ዲሞርካሲ ተግብራት አብዛኛዉን የህወሃት ደጋፊ የነበሩትን ሁሉ እያስገረመና እያስቆጣ ሲሆን፣ በርካታ ሕወሃቶች ወደ አረና እየተጎረፉ እንደሆነ ምንጮች ይጠቁማሉ። ከዚህም የተነሳ ሕወሃት የአረናን ግለት መግታት ስላልቻሉ የአመራር አባላቱን የመግደል ሴራ አያሴሩ መሆናቸውን የሚገልጹ ዘገባዎች እየተነበቡ ናቸው።

No comments:

Post a Comment