ስም፡– ዮናታን ተስፋዬ ረጋሳ
ዕድሜ፡- 31
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከተማ
ዕድሜ፡- 31
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከተማ
አሁን በእስር የምገኝበት ቦታ፡– ዝዋይ የፌደራል ማ/ቤት (የስድስት አመት ከስድስት ወር የእስር ቅጣት ፍርደኛ አድርገውኛል)
ለእስር የተዳረግሁበት ምክንያት፡- በግል የፌስ ቡክ አካውንቴ ሽብርተኝነትን የሚያበረታታ ጽሁፍ ጽፈሃል የሚል ነው፡፡
በይፋ የተመሰረተብኝ የክስ አይነት፡– መጀመሪያ የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጁን አንቀጽ 4 መተላለፍ የሚል ነበር፡፡ በኋላ ግን በብይን ወቅት አንቀጹ ተቀይሮ የአዋጁን አንቀጽ 6 መተላለፍ የሚል ሆኗል፡፡ በዚህ አንቀጽ ጥፋተኛ ተብዬ የ6 አመት ከ6 ወር ቅጣት ተወስኖብኛል፡፡
በእስር በምገኝበት ወቅት የሚከተሉት የመብት ጥሰቶች ተፈጽመውብኛል፡፡
ሀ. በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ለአራት ወራት በቆየሁባቸው ጊዜያት
1. ሳይቤሪያ በሚባለበሚባለለማለማ ስፍራ ታስሬያለሁ፡፡
2. ቤተሰብና የሐይማኖት አባትን ጨምሮ ጠያቂ ተከልክያለሁ፡፡
3. በግል የጻፍኋቸው የፌስ ቡክ ጽሁፎቼ ላይ ለማስረጃነት እንድፈርም ተደርጌያለሁ፡፡
ሀ. በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ለአራት ወራት በቆየሁባቸው ጊዜያት
1. ሳይቤሪያ በሚባለበሚባለለማለማ ስፍራ ታስሬያለሁ፡፡
2. ቤተሰብና የሐይማኖት አባትን ጨምሮ ጠያቂ ተከልክያለሁ፡፡
3. በግል የጻፍኋቸው የፌስ ቡክ ጽሁፎቼ ላይ ለማስረጃነት እንድፈርም ተደርጌያለሁ፡፡
ለ. በቂሊንጦ እስር ቤት በቆየሁባቸው ጊዜያት
1. ከሌሎች እስረኞች ተነጥየ እንድታሰር ተደርጌያለሁ፡፡
2. ለሦስት ቀናት ቀንና ሌሊት እጅና እግሬን በሰንሰለት ታስሬ ነበር፡፡
3. ድብደባ ተፈጽሞብኛል፡፡
4. ዛቻና ማስፈራሪያ ደርሶብኛል፡፡
5. የጠያቂ ገደብ ተጥሎብኛል፡፡
6. የመጠየቂያ ሰዓት ገደብ ተደርጎብኛል፡፡
7.ጠበቃየን እንዳላናግር ተከልክዬ ነበር፡፡
1. ከሌሎች እስረኞች ተነጥየ እንድታሰር ተደርጌያለሁ፡፡
2. ለሦስት ቀናት ቀንና ሌሊት እጅና እግሬን በሰንሰለት ታስሬ ነበር፡፡
3. ድብደባ ተፈጽሞብኛል፡፡
4. ዛቻና ማስፈራሪያ ደርሶብኛል፡፡
5. የጠያቂ ገደብ ተጥሎብኛል፡፡
6. የመጠየቂያ ሰዓት ገደብ ተደርጎብኛል፡፡
7.ጠበቃየን እንዳላናግር ተከልክዬ ነበር፡፡
በመጨረሻም፣ ስለእኔ ትንሽ ለማለት ያህል፣ ከ1ኛ ደረጃ እስከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ የተማርሁት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ነው፡፡ ትውልዴና እድገቴም አዲስ አበባ ነው፡፡ ለቤተሰቦቼ የመጀመሪያ ልጅ ነኝ፡፡ በተማርሁት የውጭ ቋንቋና ሥነ-ጽሁፍ ትምህርት ዘርፍ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋን አስተምሬያለሁ፡፡
ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ደረጃዎች ሰላማዊ የፖለቲካ ስራ ስሰራ ቆይቻለሁ፡፡ በግልም ሀሳቤን ከመግለጽ ወደኋላ ያልሁበት ጊዜ የለም ማለት እችላለሁ፡፡ ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ ሰማያዊ ፓርቲን ተቀላቅያለሁ፡፡ በፓርቲው ውስጥ ከተራ አባል እስከ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊነት ተሳትፎ አለኝ፡፡ በ2007 ሀገራዊ ምርጫም ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እጩ ተወዳዳሪ ነበርሁ፡፡ሰላማዊ ትግልና በህጋዊ አሰራር የማምን ሰው ነኝ፡፡ በእውነቱ ህገ-መንግስታዊ ሀሳብን በነጻነት መግለጽ መብቴን ተጠቅሜ በመፃፌ ረጅም እስር እና ፍርድ
ቤት መንላታ ሳያንስ በእስር ወቅት ከላይ የጠቀስኩት ከፍተኛ የመብት ጥሰት ደርሶብኛል፡፡
No comments:
Post a Comment