Search This Blog

Wednesday, May 1, 2024

ፍትህ የተነፈጋት ነብስ፤ ዛሬም የጋዲሳ ሂርጳሳ ቤተሰቦች ሰለፍትህ ይጣራሉ

 


በ1990ዎቹ በማዕከላዊ እስር ቤት ታስረው ተሰቃይተው ከሞቱ እስረኞች መካከል አንዱ የነበረው የፊንፊኔ ዩንቨርሲቲ ተማሪ ጋዲሳ ሂረጰሳ ዛሬም ድረስ ፍትህ እንዳጣ ቤተሰቦቹ ገለፁ።

ለውጡን ተከትሎ ማእከላዊ እስርቤት ለህዝብ እይታ ክፍት ሲደረግ ተማሪው በታሰረበት ክፍል ግድግዳ ላይ '‘ከእኔ እና ከከሳሾቼ ማነው ወንጀለኛ?'' በማለት የፅፎ ስሙን ከስር ያሰፈረበት መልእክት የብዙዎችን ልብ ነክቷል።
በኢህአዴግ ዘመን በማእከላዊ እስር ቤት ታስረው ከሞቱት እስረኞች መካከል ጋዲሳ ሂርጰሳ አንዱ ነው።
የማእከላዊ እስር ቤት ወደ ሙዚየምነት ይቀየራል ተብሎ ከአራት አመታት በፊት በተከፈተበት ወቅት በእስር ቤቱ ግድግዳ ላይ ተፅፎ የተነኘው ''ከእኔ እና ከከሳሾቼ ማነው ወንጀለኛ?'' የሚለው የጋዲሳ ፅሁፍ በአብዛኞች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።
በማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ በስቃይ ላይ የነበሩ ሰዎች በቤቱ ግድግዳ ላይ የተለያዩ መልዕክቶችን ይጽፉ እንደነበር ተገልጿል።
የማካላዊ እስር ቤት በተከፈተበት በቅት በፊንፊኔ ዩኒቨርስቲ የላቀ ውጤት በማስመዝገብ የሚታወቅ ተማሪ የነበረው ጋዲሳ በ1998 ከዚህ አለም በሞት ቢለይም ስሙ ከስር ሰፍሮ በተለጠፈ የአማርኛ ጽሁፍ በማህበራዊ ድህረ ገጽ መነጋገሪያ በመሆን ህይወቱ ያለፈበትን ሁኔታ አመላክቷል።
የጋዲሳ ታላቅ ወንድም ታየ ሂርጰሳ ጋዲሳ ተማሪዎችን ለተቃውሞ አስተባብሯል በሚል መታሰሩን ለቢቢሲ ተናግሯል።
በ1997 የኦሮሚያ ክልል መቀመጫ ከፊንፊኔ ወደ አዳማ ሲዘዋወር በፊንፊኔ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የተደረገውን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ ከተባረሩት 300 ተማሪዎች መካከል ጋዲሳ አንዱ መሆኑን ወንዲሙ ገልጿል።
ከዚያም ሳይቆይ ተማሪዎችን ለተቃውሞ አነሳስተሃል በሚል ወደ ማከላዊ እስር ቤት እንዲገባ መደረጉን ተናግሯል።
ያኔ በፊንፊኔ ዩኒቨርሲቲ የአምስተኛ ዓመት የቴክኖሎጂ ዲፓርትመንት ተማሪ እንደነበርና በዩንቨርሲቲው የላቀ ውጤት ካላቸው ተማሪዎች መካከል ግንባርቀደም እንደነበረ አክሎ ገልጿል።
ጋዲሳ በእስር ቤት ተመላልሶ ስጠይቀው እንደነበር የገለፀው ታላቅ ወንድሙ፣ የእስር ቤቱ ሁኔታ በጣም አስቸጋሪ እንደነበር ከሱ መረዳቱን ተናግሯል።
በኋላም በድብቅ ጨለማ ክፍል ውስጥ እንዲሰቃይ በማድረግ፣ መላ ሰውነቱ ሽባ ሆኖ እና ለተለያዩ ሌሎች በሺታዎች ተጋልጦ ህክምና ሳያገኝ በመቆየት በመጨረሻም በሽታው ስጠናበት ሆስፒታል ተወስዶ ህይወቱ ማለፉን ተናግሯል።
ጋዲሳ ከሰኔ 1996 ጀምሮ ህይወቱ እስካለፈበት 1998 ድረስ በማእካላዊ እና አለም በቃ ተብሎ በሚጠራ እስር ቤቶች መቆየቱን የገለፀው ወንዲሙ፣ ህይወቱ ስታልፍ አጠገቡ እንደነበር ተናግሯል።
በእስር ቤቱ በደረሰበት ጉዳት መላ ሰውነቱ የማይንቀሳቀስ እንደነበር በመግለፅ በጊዜው የህክምና ማስረጃ ጠይቀን የሳንባ ምች ነው ብለው እንደከለከሉት ገልጿል።
የጋዲሳ ታላቅ ወንድም አቶ ታየ ሂርጰሳ ጋዲሳ ከማእከላዊ ስወጣ ለፍርድ ቤት አቤቱታ አቅርበው እንደነበር ገልፆ ነገርግን በህመም ህይወቱ አልፏል በማለት መዝገቡን መዝጋታቸውን ተናግሯል።
ክሳቸው ያላግባብ መዘጋቱን የሚናገረው ታዬ፣ ያኔ ማዕከላዊና ቃሊቲ እስር ቤቶችን ስያስተዳድሩ የነበሩ ሰዎች በህግ መጠየቅ አለባቸው ብሏል።
በወቅቱ የቀረቡት ማስረጃዎች ተጣርተው ወንጀለኞች በህይወት አሉ እና በሰው ህይወት ላይ ወንጀል የፈፀመው አካል በህግ መጠየቅ አለበት' ሲል የጋዲሳ ወንዲም ታየ ተናግሯል።
የጋዲሳ ወላጅ እናት ወይዘሮ ጃለሊ ድሮ በበኩላቸው በእስር ቤት በደረሰበት ጉዳት ህይወቱ አልፏል ነገር ግን ወንጀሉን የፈፀሙት ሰዎች እስካሁን ለህግ አልቀረቡም ብለዋል።
ለሀገር ይሆናል ብለን ስንጠብቅ ለአፈር አደረጉብኝ በማለት በሀዘን ተናግረዋል።
በኢህአዴግ መራሹ መንግስት ዘመን ሽዎች ታስረው የከፋ ስቃይ እንዳሳለፉ፣ አያሌዎች ደብዛቸው እንደጠፋና የብዙ ቤተሰቦች ህይወት በዚህ እንደተመሰቃቀለ ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት።

#ፍትህ #ፍትህ #ፍትህ

No comments:

Post a Comment