Search This Blog

Monday, October 19, 2026

Red Sea politics - ቀይ ባህር , ኢትዮጵያ ምን እያደረገች ነው?

 
በቀይ ባህር እና በባቤል አልመንደብ የሚከሰቱት የቅርብ ጊዜ ክስተቶች አንድ ግልጽ መልዕክት እየሰጡን ነው፦ ባህር በር ለኢትዮጵያ የንግድ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የብሔራዊ ደህንነትና ጉዳይ ነው።

በየመን ያለው ጦርነት እየተባባሰ ሲሄድ፣ ሁቲዎች ሞካን፣ ማዩን/ፔሪምን እና የሃኒሽ ደሴቶችን በመቆጣጠር በባቤል አልመንደብ ላይ ያላቸውን ተጽዕኖ አሳድገዋል። ይህ የዓለም ንግድ እና የኃይል ምንጮች የሚያልፉበትን አንድ እጅግ ወሳኝ የባህር መተላለፊያ በከፍተኛ። የጸጥታ አደጋ ውስጥ አስገብቶታል። በአንድ ቀን 30 ያህል መርከቦች በሚያልፉበት ሰርጥ ዛሬ ወደ 15 መርከቦች ወርዷል። ከየመን ወደ ጅቡቲ የሚሻገሩ ስደተኞች ቁጥር በፍጥነት ጨምሯል።
ይህ ለኢትዮጵያ ምን ማለት ነው?
1. የቀይ ባህር ጉዳይ ከእንግዲህ ሊዘገይ የማይገባ ጉዳይ ነው
ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር በጂኦግራፊ የተለየች ብትሆንም፣ ከቀይ ባህር የሚነሱ የንግድ፣ የኃይል፣ የደህንነትና የጂኦፖለቲካ ለውጦች በቀጥታ ይነኳታል። የወደብ ተደራሽነት የሀገር ራስን የመቻል ዋልታ ነው።
2. ባቤል አልመንደብ ከኢትዮጵያ የሚርቅ ጂኦፖለቲካዊ ቦታ አይደለም
በአንድ በኩል የየመን የባህር ዳርቻ በሁቲዎች ቁጥጥር ሲገባ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በአፍሪካ ዳርቻ ጅቡቲ፣ ኤርትራ እና ሶማሊያ የሚገኙት ወደቦች እና የውትድርና ማዕከላት የክልሉ የኃይል ሚዛን አካል ሆነዋል። በዚህ ሁኔታ ኢትዮጵያ የቅርብ ተመልካች መቆየት አይቻላትም። ቀይ ባህር ውስጥ የሚፈጠረው የፀጥታ ስጋት ከቀይ ባህር ተወሳኝ የጎረቤት አገራት (ኤርትራና ጂቡቲ) በላይ ተጽዕኖ የሚያሳደረው ኢትዮጵያ ላይ ነው።
3. የአሁኑ ቀውስ ለኢትዮጵያ አደጋ ብቻ ሳይሆን የስትራቴጂ እድልም ነው
የቀይ ባህር ቀውስ ለኛ የተግባር ትምህርት ነው። ባህር አጠገብ ተቀምጠህ የባህር በር ከሌለህ ያንተ ደህንነነት የሚወሰነው ለኢሎች ነው። ከእንግዲህ የኢትዮጵያ ጥያቄ “የባህር በር” ሳይሆን፣ “በህር ላይ ተግባራዊ መገኘት (functional maritime presence)” የሚል መሆን አለበት።
4. “በባህር ላይ መገኘት” ሲባል ት
• የረጅም ጊዜ የወደብ ተደራሽነት፣
• የራሷ የሎጂስቲክስ እና የንግድ ቁጥጥር፣
• የባህር ላይ ደህንነት አቅም፣
• የባህር ሃይል መገኛ፣
• እና የማይቀለበስ የስምምነት ዋስትና
ያለው functional maritime presence ነው።
5. ከአሁኑ ቀውስ የምንማረው ዋና ትምህርት
ዛሬ በቀይ ባህር የሚካሄደው ትግል የወደብ ትግል ብቻ አይደለም። የመተላለፊያ ነጥቦችን (chokepoints) የመቆጣጠር ትግል ነው።
ሁቲዎች በባቤል አልመንደብ የሚያገኙት ተጽዕኖ እንዴት አንድ የባህር መተላለፊያ የኢኮኖሚና የጂኦፖለቲካ መሳሪያ ሊሆን እንደሚችል በተግባር እያሳየ ነው። ኢትዮጵያም ይህንን ትምህርት በጥንቃቄ መውሰድ አለባት። ቀይ ባህር እግራችን ካላረፈ ድምፃችን ተሰሚነት አይኖረውም።
6. ስለዚህ የኢትዮጵያ ስትራቴጂ ምን መሆን አለበት?
“Access to the sea” ከሚለው አስተሳሰብ ወደ “presence in the sea” መሸጋገር ነው። እንዴት በሚለው ላይ ጥናቶች ይቀረቡ፤ ውይይቶች ይደረጉ።
የዛሬው የቀይ ባህር ቀውስ ኢትዮጵያን እንድታስብ የሚያስገድድ ነው። የባቤል አልመንደብ አሁን እያሳየን ያለው የባህር ጂኦፖለቲክስ ለሌላ ጊዜ የሚተው ጉዳይ እንዳልሆነ ነው።
የተፈጥሮ እስር ቤት ተፈጥሯዊ እጣ ፈንታ አይደለም። የጂኦግራፊ ገደብ ሊኖር ይችላል፤ ያ ገደብ ግን በጥሩ ስትራቴጂ ሊሰበር ይችላል።

No comments:

Post a Comment