Search This Blog

Monday, April 7, 2014

ኖርዌይ ኢህአዴግ ያሰረባትን ዜጋዋን ጉዳይ እየተከታተለች ነው ማዕከላዊ እስርቤት ከፍተኛ ስቃይ ይደርስባቸዋል በሚል ተሰግቷል

ኖርዌይ ኢህአዴግ ያሰረባትን ዜጋዋን ጉዳይ እየተከታተለች ነው
ማዕከላዊ እስርቤት ከፍተኛ ስቃይ ይደርስባቸዋል በሚል ተሰግቷል
http://www.goolgule.com/norway-following-up-okellos-arrest/

የኢህአዴግን ካዝና የምትሞላዋ ኖርዌይ በማዕከላዊ እስር ቤት የሚገኙትን ዜጋዋን አስመልክቶ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እየሰራች መሆንዋ ታወቀ። በማዕከላዊ እስር ቤት የታሰሩት ዜጋዋ ድብደባና ቶርቸር እንዳይካሄድባቸው በቅርብ ክትትል እያደረገች መሆንዋን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ክፍሎች ለጎልጉል አስታውቀዋል።

ኢህአዴግን ከልጅነቱ ጀምራ ስትደጉም የኖረቸውና አሁን ደግሞ “በልማታዊ መንግሥትነት” መድባ ድጋፏን የምትዘረጋለት ኖርዌይ ዜጋዋን አስመልክቶ አስፈላጊውን ሁሉ የማድረግ ግዴታ እንዳለባት ይታወቃል። በዚሁ መሰረት የኖርዌይ ትልቁ ጋዜጣ ቀደም ሲል ጎልጉል ምንጮቹን ጠቅሶ ይፋ ያደረገውን ዜና የሚያረጋግጥ ዜና አሰራጭቷል።

ደቡብ ሱዳን የጸጥታ ሃይሎች አሳልፈው ለኢህአዴግ የሰጧቸው የቀድሞ የጋምቤላ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦኬሎ አኳይ የኖርዌይ ዜግነት እንዳለቸው በማረጋገጥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን በቅርበት እንደሚከታተለው፣ አዲስ አበባ የሚገኘው የኖርዌይ ኤምባሲም ስራውን እየሰራ እንደሆነ አፍተን ፖስት አመልክቷል።

አፍተን ፖስት “የሰብአዊ መብት ተከራካሪ” ሲል በዜናው መክፈቻ የጠቀሳቸውን አቶ ኦኬሎ አኳይን አስመልክቶ የውጪጉዳይ ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን አማካሪ ስቫይን ሚኬልሰንን ጠቅሶ “አቶ ኦኬሎ የደቡብ ሱዳን የደህንነት ሃይሎች በደቡብ ሱዳንና በዩጋንዳ ድንበር መካከል ይዘዋቸዋል። አንደተያዙም ወደ ጁባ ሳይወሰዱ ተላልፈው ተሰጥተዋል” በማለት የጉዳዩን አካሄድ አመላክቷል።

የኢህአዴግን የገቢ ምንጭ የሆነችው ኖርዌይ በጉዳዩ አቋም በመያዝ ያስታወቀችው ስለመኖሩ ዜናውን የዘገበው አፍተን ፖስት ያለው ነገር የለም። ይሁን አንጂ ድርጊቱን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ኖርዌይ እንደምትቃወመው አልሸሸገም። አቶ አኳይ ለምን ወደ ስፍራው እንደተጓዙ በውል የተገለጸ ነገር እንደሌለ ዜናው ጠቁሟል። “በተመሳሳይ” በማለት ከዜናው ግርጌ ኢህአዴግ ለዴሞክራሲና ለሰብአዊ መብት ክብር እንደሌለው፣ በነጻ ፕሬስና በተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ እያደር የከረረ ርምጃ በመውሰዱ ክፉኛ የሚዘለፍበት ጉዳይ እንደሆነ አጣቅሷል።

ጎልጉል መጋቢት 19 ቀን 2006 ዓም (March 28, 2014) ቀን ዜናውን ይፋ በማውጣት ቅድሚያ ወስዶ ሲዘገብ አቶ ኦኬሎ ከደቡብ ሱዳን ከሆቴል ውስጥ ታፍነው መወሰዳቸውን ጠቁመን ነበር። አሁን አዲስ በመጣው መረጃ በዩጋንዳና በደቡብ ሱዳን ድንበር ላይ ተያዙ መባሉ ምን አልባትም ኢህአዴግ ሊመሰርትባቸው ላሰበው ክስ አመቺ ሁኔታ ለመፍጠር ታስቦ እንደሚሆን ጥርጣሬ አለ። የዜናው ምንጭ አቶ ኦኬሎ ከጁባ በሄሊኮፕትር መወሰዳቸውን እንደሚያውቁ ገልጸዋል።

በመለስ ዜናዊ ውሳኔና ትዕዛዝ በአኙዋክ ተወላጆች ላይ በጅምላ የተከናወነውን ጭፍጨፋ አስመልከቶ ተቃውሞ በማሰማት፣ አድርጉ ተብለው የታዘዙትን ባለመቀበል አገር ጥለው የኮበለሉት አቶ ኦኬሎ ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ያገባናል በሚሉ “አክቲቪስቶች”፣ የፖለቲካ ድርጅቶችና፣ ማህበራት ዘንድ ዋንኛ ርዕስ ያለመሆናቸው ምክንያት አስገራሚ እንደሆነባቸው የሚጠቁሙ ዲያስፖራዎች ጥቂት አይደሉም። ከዚያም አልፎ አሁንም የመታሰራቸው እና እርሳቸውን ለማስፈታት በሚደረገው ሁኔታ ላይ የተፈጠረው ዝምታ አጠያያቂ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

አቶ ኦኬሎ ማዕከላዊ እስር ቤት እንደሚገኙና፣ በዚያም በከፍተኛ ደረጃ ቶርቸር ይደረጋሉ በሚል ስጋት ሁኔታውን ለሚመለከታቸው በማሳወቅ በኩል አንዳንድ ወገኖች እንቅስቃሴ መጀመራቸው ታውቋል። ኢህአዴግ እስካሁን ፍርድ ቤት ያላቀረባቸው አቶ ኦኬሎ “አሁን ስለሚገኙበት የጤና ሁኔታ የኖርዌይ ኤምባሲ የጉብኝት ሪፖርትና ይጠበቃል” ሲሉ እኚሁ ክፍሎች አመላክተዋል።

ከቤተሰባቸው ተነጥለው በስደት ከሚኖሩበት ኖርዌይ ወደ ደቡብ ሱዳን ያመሩት የቀድሞው የጋምቤላ ርዕሰ መስተዳድር ደቡብ ሱዳን በህወሃት ሙሉ ቁጥጥርና ፈቃድ የምትንቀሳቀስ አገር መሆኗን እያወቁ ወደዚያ ማቅናታቸውን “ታላቅ ጥፋት” መባሉን መዘገባችን ይታወሳል። ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አሁንም አልተሳካም። ባምቤላ የአኙዋኮች ጭፍጨፋ ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ የነበሩት አቶ ኦሞት ኦባንግ በቅርቡ መኮብለላቸውና በብዙዎች ዘንድ አውሮጳ እንዳሉ ቢነገርም በትክክል ያሉበት አገር በይፋ አለመታወቁን መዘገባችን አይዘነጋም።
******************
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
የኢህአዴግን ካዝና የምትሞላዋ ኖርዌይ በማዕከላዊ እስር ቤት የሚገኙትን ዜጋዋን አስመልክቶ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እየሰራች መሆንዋ ታወቀ። በማዕከላዊ እስር ቤት የታሰሩት ዜጋዋ ድብደባና ቶርቸር እንዳይካሄድባቸው በቅርብ ክትትል እያደረገች መሆንዋን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ክፍሎች ለጎልጉል አስታውቀዋል።
ኢህአዴግን ከልጅነቱ ጀምራ ስትደጉም የኖረቸውና አሁን ደግሞ “በልማታዊ መንግሥትነት” መድባ ድጋፏን የምትዘረጋለት ኖርዌይ ዜጋዋን አስመልክቶ አስፈላጊውን ሁሉ የማድረግ ግዴታ እንዳለባት ይታወቃል። በዚሁ መሰረት የኖርዌይ ትልቁ ጋዜጣ ቀደም ሲል ጎልጉል ምንጮቹን ጠቅሶ ይፋ ያደረገውን ዜና የሚያረጋግጥ ዜና አሰራጭቷል።
ደቡብ ሱዳን የጸጥታ ሃይሎች አሳልፈው ለኢህአዴግ የሰጧቸው የቀድሞ የጋምቤላ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦኬሎ አኳይ የኖርዌይ ዜግነት እንዳለቸው በማረጋገጥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን በቅርበት እንደሚከታተለው፣ አዲስ አበባ የሚገኘው የኖርዌይ ኤምባሲም ስራውን እየሰራ እንደሆነ አፍተን ፖስት አመልክቷል።
አፍተን ፖስት “የሰብአዊ መብት ተከራካሪ” ሲል በዜናው መክፈቻ የጠቀሳቸውን አቶ ኦኬሎ አኳይን አስመልክቶ የውጪጉዳይ ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን አማካሪ ስቫይን ሚኬልሰንን ጠቅሶ “አቶ ኦኬሎ የደቡብ ሱዳን የደህንነት ሃይሎች በደቡብ ሱዳንና በዩጋንዳ ድንበር መካከል ይዘዋቸዋል። አንደተያዙም ወደ ጁባ ሳይወሰዱ ተላልፈው ተሰጥተዋል” በማለት የጉዳዩን አካሄድ አመላክቷል።
የኢህአዴግን የገቢ ምንጭ የሆነችው ኖርዌይ በጉዳዩ አቋም በመያዝ ያስታወቀችው ስለመኖሩ ዜናውን የዘገበው አፍተን ፖስት ያለው ነገር የለም። ይሁን አንጂ ድርጊቱን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ኖርዌይ እንደምትቃወመው አልሸሸገም። አቶ አኳይ ለምን ወደ ስፍራው እንደተጓዙ በውል የተገለጸ ነገር እንደሌለ ዜናው ጠቁሟል። “በተመሳሳይ” በማለት ከዜናው ግርጌ ኢህአዴግ ለዴሞክራሲና ለሰብአዊ መብት ክብር እንደሌለው፣ በነጻ ፕሬስና በተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ እያደር የከረረ ርምጃ በመውሰዱ ክፉኛ የሚዘለፍበት ጉዳይ እንደሆነ አጣቅሷል።

Sunday, April 6, 2014

የወያኔ የበላይነት እስከመቼ ?? ... መሸዋወድ እስከየት?

We need freedom and democracy !!! Ashenafi
የቀድሞውን ወታደራዊ ስርኣት ለመጣል የአሁኑን የሽምቅ ሽብራዊ መንግስት ለማንገስ በበረሃትግል የተሳተፉት የኢሕኣዴግ ድርጅቶች በሃገሪቱ የትግል ታሪክ ውስጥ ጉልህ ድርሻ አላቸው::በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ስራትን ለማስፈን እጅ ለእጅ ተያይዘን በጋራ ታግለን ህዝባዊ ነጻነትን እናረጋግጣለን በማለት ጫካ የተደባለቁት ድርጅቶች የትግራይን ህዝብ ነጻ በማውጣት ታላቋን ትግራይን እፈጥራለሁ ያለውን ሕወሓት የትግሉ ስኬት ሲከሽፍበት ኢሕዴንን እና ኦሆዴድን በመንተራስ ተረማምዶ ለስልጣን ከበቃ 22 ድፍን አመታትን አስቆተረ::

በ22 አመት የስልጣን ቆይታው የኢሕዴንን እና የኦሆዴድን የትግል አስታውጾ ላማኮላሸት እና ከታሪክ ሂደት መስመር ለማሳት የተጠቀመባቸው ዘዴዎች እና ወታደራዊውን እና የደህንነቱን ተቋም በአንድ ብሄር በማጠር አባል ድርጅቶቹ እና አባላቱ መላወሻ እንዲያጡ ሲሰራ በአደባባይ ታይቷል::ከአቶ ታምራት ላይኔ የፖለቲካ ጠለፋ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ቁጥራቸው ይህ ነው የማይባሉ የኢሕዴን ታጋዮች እና ካድሬዎች በተለያዩ የወንጀል ልጣፎች ከያሉበት ተጠልፈው ወደ ሞት እስር እና ስደት ተግዘዋል:: የኦህዼድ አባላትንም እንዲሁ በመጥለፍ በፖለቲካዊ የኦነግ ታርጋ በማሰር በመግደል እና በተለያዩ ጥቅማጥቅሞች በማሸት አንደበታቸውን አሽጎታል:: ይህ የሕወሓት ስራ ማንም የሚያውቀው እና ጸሃይ የሞቀው ሃቅ ነው:: ቢተነተን የማያልቀው የሕወሓት የውስጥ እና የውጭ ሽብር የሚጋለጥበት ቀን መድረሱት የብኣዴን እና የኦህዴድ አባላት ተግተው በመስራት ላይ መሆናቸውን ሌሎችንም ካድሬዎች እንዲንቀሳቀሱ አድርጓል::
የብኣዴን እና የኦህዴድ አመራሮች እና ካድሬዎቻቸው ራሳቸውን ከሕወሓት የበላይነት የማላቀቅ ግዴታ አለባቸው::የሕወሓት የበላይነት ከምን የመጣ ነው? ትግል ከሆነ ሁሉን እኩል ድርሻ ያለውን ትግል በጋር ታግለው ነው ወታደራዊውን ስርኣት ያስወገዱት ለሕወሓት ብቻ ማን ይህን እድል ሰጠው? ሕወሓት ብቻውን አልታገለም ብኣዴንም የራሱ ድርሻ ኦሕዴድም የራሱ ድርሻ አለው:; የአማራውና የኦሮሞው ህዝብ ኢሕዴን/ብኣዴንን አይተው ኦሕዴድን አይተው እንጂ ለሕወሓት ሲሉ የእትዮጵያን መሬት በመምራት አልተባበሩም ስለዚህ የብኣዴን እና የኦሕዴድ አመራሮች እና ካድሬዎች ሊገነዘቡት የሚገባው ጉዳይ ትግሉ ሕወሓት ብቻ የመራው ያደራጀው ያሸነፈው አለመሆን እና የድርጅቶቹም ድርሻ እኩል መሆኑን ነው::
በመከላከያው እና በደህንነቱ ዘርፍ ከፍተኛውን ቦታ በመቆጣጠር ሌላውን የእንጀራ ልጅ ያደረጉት ሕወሓቶች የበረሃውን ዳገት እና ቁልቁለት እነሱ ብቻ የተወጡት አድርገው በማቅረብ የቀሪውን ታጋይ ደም እና ድካም ጥላሸት እየቀቡት ነው::የሕወሓት የበላይነት እንዲያበቃ በመከላከያው እና በደህንነት ተቋማት ውስጥ ያሉ የብኣዴን እና የኦሕዴድ ታጋዮች የራሳቸውን አስታውጾ ሊያበረክቱ ይገባል::የፖለቲካ ባርነት እንዲቆም ትግሉን የማቀጣጠል ሃላፊነት አለባቸው::

Saturday, April 5, 2014

Landgrab turns Oromo from Farming to a Household Guard

From land owner to zebegna--how the planned plot to expand Addis Ababa beyond its current limit is transforming Oromo farmers. According to this survey ( credit to Tesfaye Shiferaw Sida), before the expansionist land grab, 94.5% of the population were farmers, afterwards 62% became household guards for the settlers while the rest are unemployed or work as daily laborers. This outrageous plan must be stopped by any means necessary! 


to a household guard landgarab 
Above: From Red (farmer) to Green(guard) 

የኦሮሞ ህዝብ ትግል ከጭቁን የአማራ ህዝብ ጋር ሳይሆን ከገዢው መደብና ከቀድሞው ሥርዓት ነፋቂዎች ጋራ ነው

“ኢትዮጵያ ውስጥ የመገንጠል ጥያቄ ማንሳት ይቻላልን?” ለሚለው የአምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው ጽሁፍ መልስ


በአርዕስቱ ለመጥቀስ እንደሞከርኩኝ የኦሮሞ ህዝብ ትግል ከትውልድ ለትውልድ ሲተላለፍ የመጣው ከገዥዎችና ከረዳቶቻቸው የውጪ ኃይላት ጋር ነው። ይህ ህዝብ በነፍጥ አንጋቾች ቅኝ (አቅኝዎች) ሥር ከቀደቀበት ጊዜ አንስቶ አስከ ዛሬ ድረስ ትግሉን ያቁዋረጣበት ጊዜ የለም። ይህም የሆነበት ወቅት ብናስብ ሴሜቲኮች (ሓበሾች) ወደ ምስራቅ አፍሪካ ከመጡበት ጊዜ አንስቶ ነው። እነዚህ ህዝብ ወደ ምስራቅ አፍሪካ የመጡት በተለያየ ጊዜ ሲሆን፣ ሰበባቸውም የተላያየ ነው። ከመጡም በኃላ በኩሾች ንጉሥ (አባ ገዳ) “ኩሳ” በተባለ የሥልጣን ወይም የንግሥና ስም ስር በመተዳደር ነው። ቀስበቀ እየበረከቱ ሲሄዱ በተንኮልና በኃይል የነበረውን የኩሽ ህዝቦችን መስተዳድር ደምስሳው ሥልጣኑን ተቆጣጠሩ። የዛጉዌዎች ሥርወመንግስት መሃል ገብ እንጂ እስካሁን በሥልጣኑ ሲፈራረቁበት ቆዩ።
እስኪ አቶ አምሳሉ ገ/ኪዳን የጠቀሱልን “ታሪክ” እንመልከት።
“… ከጥንት ከመሠረት ጀምሮ የሚታወቁ ሀገራት አሉ እንደ ዓለም ታሪክና መንፈሳዊው ተረክ ስናይ ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ ከተመሠረቱ ህልው ከሆኑ ሦስት ሀገራት አንዷ ናት፡፡ በዚህ ዙሪያ የተለያዩ ተረኮች አሉ፡፡
አንደኛው ኢትዮጵያን የመሠረታት የአዳም ልጅ አሪ ወይም አራም ዓለም በተፈጠረ በ 970ዓመት ነው፡፡ የመጀመሪያ ንጉሷም እሱ ነው እስከ የጥፋት ወኃ ድረስ 21ነገሥታት ነግሠው ለ 1286 ዓመታት ኢትዮጵያን ገዝተዋል የሚል ተረክ ለብቻው አለ፡፡ ከጥፋት ውኃ በኋላም ኖኅ ዓለምን ለሦስቱ ልጆቹ ሲያከፋፍል አፍሪካ ለካም ደርሳው ነበርና ኢትዮጵያ ውስጥ ከነገሡት የነገደ ካም ነገሥታት የመጀመሪያው ካም ነው ብለው ከካም የሚጀምሩ አሉ፡፡ አይ አይደለም ከካም ሦስተኛ ትውልድ 2545 ዓመት ቅ.ል.ክ ከሰብታህ ነው የሚጀምረው ብለው ከሰብታህ የሚጀምሩም አሉ፡፡ በዚያም ሆነ በዚህ ሀገሪቱ ጥንታዊትና በሀገር ደረጃ በቀዳሚነት ከተጠሩ ሀገራት አንዷ ናት፡፡ በጥንት የዓለም ታሪክ መጻሕፍትም ሆነ በመንፈሳዊ መጻሕፍት ዛሬ አፍሪካ ብለን የምንጠራውን እንዳለ ኢትዮጵያ ነበር የሚሉት፡፡ በጥንቱ የአውሮፓዊያን የዓለም ካርታ ላይ አትላንቲክ ውቅያኖስን “የኢትዮጵያ ውቅያኖስ” ሲል ይጠራዋል፡፡ በሌላ በኩል ማሊ፣ ቻድ፣ ኒጀር ወደታችም ታንዛኒያ በሌሎች በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራትም ምንጫቸው ኢትዮጵያ እንደሆነ የሚናገሩ በርካታ ማኅበረሰቦች አሉ፡፡”
our struggle continues until we get our  freedom!!! ashenafi
ይህ ታሪክ ለመጸፍ የሞከረው ጳውሎስ ፓርሌ የተባለው ሊቅና ስለ ዓለም ታሪክ ከጂኦግራፊ ጋር በማዛመድ የጸፈው ሲሆን፣ ሓበሻው ደብተራ ዮሐንስ ወልደ ማሪያም ዘብሔረ ተጉለት በ1937 ዓ.ም ትርጉሙን በማዛባት ለራሳቸው እንዲመች አድርጎ የደብተራ (አለቃ) ታየ የተባሉትን “የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ” ብለው የጸፈውን ገልብጣው አስነበበን።
የአፍሪካ ህዝብ ታሪክ ደብተራዎቹ እንደሚጽፉት በሺህዎች (3ሺህ፣ 5ሺህ፣ 10ሺህ) ገለመሌ የሚገመት ሳይሆን አርኪሆሎጂስቶችና ስለ ፍጥረታት የሚያጠኑ ሳይንሲስቶች (ተማራማሪዎች) እንዳረጋገጡት በሚሊዮኖች ዓመታት የሚገመት ጊዜ ነው። ኢትዮጵያዊትዋ ሉሲ (ድንቅቱ) እናስታውሳት።
ወደ አቶ አምሳሉ ጽሁፍ ስንመለስ “ኢትዮጵያን የመሠረታት የአዳም ልጅ ኦሪ ወይም ኦራም ዓለም በተፈጠረ በ970ዓመት ነው፡፡” የሚለውን እናገኛለን። ይህ “ኦሪ ወይም ኦራም” ወይም የኦሮሞች ትውፍታ እንደሚለው ሆሪ ወይም ሆሮ ከሚለው ቃለት ጋር ይዛመዳል። በመሆኑም ኦሮሞች ከዚህ በመነሳት ኦሪ/ሆሪ፣ ኦራ/ሆራ፣ ኦሩ/ሆሩ በማለት የሰው ልጅ እንዴት እየተባዘ ኣሁን ደረጃ እንደ ደረሰ ይገልጸሉ። ስለሆነም ኦሮሞች (Horteen/umeen walaabu baate) ሆርቴን/ኡሜን ወላቡ ባቴ ይላሉ። በኦሮሞች አመለካከት ወላቡ ማለት ያለንበት መሬትን ጨምረው በአካባቢያችን ያለው ጠፈር/ህዋ ነው። ስለዚህ ኦሪ/ሆሪ የኦሮሞዎች ቀዳሚው አባት ነው። ኦሪትም የመጀመሪያ የአፍሪካኖች እምነት ነው። ኦሪት የኦሮሞዎች ቅድመ እምነትና አሁንም ቀሪ እሴቶች ያሉት ሲሆን፣ የሥልጣኔ መሰረትም ናቸው።
ይህን የአፍሪካን ህዝብ እምነት እንደ እራሱ ፈጠራ አድርጎ የወሰደው ከእሥራኤላዊ ነገድ የሌዊ ጎሣ የሆነው ሙሴ(ሙሳ) የተባለ ሰው ነው። እሱም ተወልዶ ያዳገው በግብጽ አገር በፈረኦኖች ቤተመንግሥት ውስጥ ነው። ሁሉን ነገር የተማራው እዚያው ነው። በኃላ አንድ ግብፃዊ ገድሎ ጉዳዩ ስለታወቃበት እዚያው ግብጽ ውስጥ ወደ ደቡብ አቅጣጫ ኮበለላ። እዚያ በሄደበትም ቦታ የዚህ አፍሪካዊ የሃይማኖት አባት የሆነውን ሄትሮ/ገትሮ የተባለ ቅዱስ ሰው አግኝቶ ቤተሰብ ውስጥ አባል በመሆን በጎቹን እየጠበቀና ሴት ልጆቹን አግብቶ ሲኖር ቆይቶ፣ እዚሁ ቦታ በእግዜብሔር ተራራ ላይ የኣምላክ መንፈስ ቀርቦት ወደ አገሩ ወደ ፓለስታይን እንዲሄድ አዘዛው። በእንዲህ ሁኔታ የነበረው የይሁዲ መህበረሰብ ከሙሴ ጋር ወደ ጵለስቲኖች ምድር ሄዱ። በመሆኑም የዚህ የቀደምት የሰው ዘር የሆነውን ታሪክ የራሳቸው በማድረግ ሥልጣኔውም እምነቱንም፣ የሰው ልጅ መገኛውንም ወደ መካከለኛው ምስራቅ ወሰዱት። ከዚህ በመነሳት ለአፍሪካዊው ህዝብ “ሃም/ኩሽ” የሚል በመስጠት በሃይማኖት መጽሐፍ ውስጥ እንዲመዘገብ አደረጉ። ይህንኑ የሃይማኖትና የህብሩ መጽሀፍ ደግሞ ግሪኮች በጊዜያቸው ወደ እራሳቸው ቁዋንቁዋ ሲገለብጡ “ኩሽ” የሚለውን “ኢትዮጵ” አሉ። እዚህ ላይ ተውላጣው ስም ይላያይ እንጂ የሁለቱ ትርጉም አንድ ሲሆን “ጥቁር ህዝብ” ማለት ነው።

Friday, April 4, 2014

ኢትዮጵያን የሚያሰጋት የሃይማኖት አክራሪነት ሳይሆን የፖለቲካ የበላይነት የፈጠረው ጽንፈኝነት እና አክራሪነት ነው

ሃይማኖት መንግሥታዊ ቅርጽ ይዞ እንዲወጣ ለማድረግ መሞከር አክራሪነት ነው፡፡ =====
«መጾም፣ መጸለይ፣ ሥርዓተ-አምልኮን መፈጸም ለሃይማኖቱ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እንጂ አክራሪነት ሊባል አይችልም፤»...የአክራሪ ክርስትና ወይንም እስልምና ቡድን መኖር የክርስትና እና እስልምና ተከታዮችን በሙሉ «አክራሪ» አስብሎ ሊያስፈርጃቸው አይችልም::አክራሪ ተብሎ የሚፈረጀው የሚራመዱ የፖለቲካ ጡዘቶች በሰዎች ላይ ሌላ እምነትን በመጫን በግዳጅ እና በሃይል ሊያስገድዱ ሲሞክሩ ይህ ማለት አህበሽን እና ተሃድሶን በጥንታውያኑ እስልምና እና ተዋህዶ ላይ በኢትዮጵያ እንደተሞከረው ማለት ነው::

አክራሪነት አሉታዊ ትርጉም ሲኖረው የራስን እምነትና አመለካከት በሌሎች ላይለመጫን መሞከር ነው፡፡ ሃይማኖት መንግሥታዊ ቅርጽ ይዞ እንዲወጣ ለማድረግ መሞከር ራሱ አክራሪነት ነው፡፡ አክራሪነት የፖሊቲካ ገጽታ ያለው ነው፡፡ ኾኖም ግን ሃይማኖትን ማጥበቅ አክራሪነት አይደለም፡፡ሃይማኖት ፍጹም እውነታን በፍጹም እምነት ስለሚቀበል ከሌሎች ግላዊ አስተሳሰቦች የተለየ ነው፡፡ የሃይማኖት መገለጫዎችን መጠቀም የዚያን ሃይማኖት ጥልቀት የሚያሳይ እንጂ እንደ ችግርም የሚወሰድ ወይም አክራሪነት ሊኾን አይችልም፡፡ «መጾም፣ መጸለይ፣ ሥርዓተአምልኮን መፈጸም ለሃይማኖቱ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እንጂ አክራሪነት ሊባልአይችልም፤» ይላሉ የዘርፉ ምሁራን፡፡
የአክራሪነትና የአጥባቂነት ፅንሰ ሐሶቦች በጥሩ ኹኔታ ተለይተው ተገልጸዋል፡፡ አንዳንድ ሰነዶች ወያኔም ለይስሙላ የገለበጣቸው ሰነዶቹ አክራሪነትንና አጥባቂነትን በአግባቡ ለይተውና ተንትነው ያስቀምጣሉ፡፡ በዚሁ መሠረትአጥባቂነትን፣ ‹‹የግል ሃይማኖትን ሃይማኖቱ በሚያዘው መሠረት ሳይንጠባጠብ ሁሉንም ትእዛዛት መፈጸም ነው፤» በማለት ሲፈታው አክራሪነትን ደግሞ፣ «ከራስ እምነት ወጥቶ ሌላውን መተንኮስና የሌሎችን ሃይማኖት መኖር አለማመንና አለመፍቀድወይም ሌሎቹን አስገድዶ የራስ እምነት ተከታዮች ለማድረግ መጣር ነው፤» ይላል፡፡ በተግባር ላይ አለመዋሉ እና በጣልቃ ገብነት መተርጎሙ ጉዳት አመጣ እንጂ::
ከዚህ ብያኔ ስንነሣ ክርስቲያንም ሆነ ሙስሊም ከርሱ ውጭ የኾኑትን የሌሎቹን መኖር የማይቀበልና ከግለሰቦቹ ፈቃድ ውጭ አስገዳጅ እስከኾነ ድረስ እርሱን አክራሪ ማለት ይቻላል፡፡መብትን መጠየቅ ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት መሸሽ አክራሪነት አይደለም:: በዚህ መልኩ አክራሪው ይህንኑ ድርጊት ሊፈጽም የተነሣውን ቡድን ብቻ እንጂ «አክራሪው ቡድን» የወጣበትን/የተገኘበትን ቤተ እምነት ሊወክል አይችልም፡፡ ስለዚህ በአለማቀፍ ደረጃ የአክራሪ ክርስትና እና እስልምና ቡድን መኖር የክርስትና እና እስልምና ተከታዮችን በሙሉ «አክራሪ» አስብሎ ሊያስፈርጃቸው አይችልም፤ ለሌላው ቤተ እምነትም እንዲሁ፡፡ ሃገሪቱን የሚያሰጋት የሃይማኖት አክራሪነት ሳይሆን የፖለቲካ የበላይነት የፈጠረው ጽንፈኝነት እና አክራሪነት ነው::

Thursday, April 3, 2014

Why Europeans should care about Ethiopia’s repression of journalists

With European elections looming and a host of crises here at home dominating the political debate, there is the risk that challenges abroad – including Ethiopia’s disturbing treatment of journalists – will be swept under the carpet. It is vitally important that the currentParliament and Commission not let that happen as their mandates wind down, writes Alison Bethel McKenzie.
When nominations for the European Parliament’s Sakharov Prize for Freedom of Thought were announced last autumn, it was heartening to see that two imprisoned journalists in one of Africa’s most oppressed countries had made the list with the support of more than 40 lawmakers.
We Need Freedom of Press in Ethiopia!!!!    Ashenafi
Although the award ultimately went to the Pakistani education activist Malala Yousafzai, the nomination of Ethiopian journalists Reeyot Alemu and Eskinder Nega marked important recognition of the appalling conditions that these brave people have faced since they were convicted on terrorism charges in 2011.
Yet today, there seems to be no end to the Ethiopian government’s assault on independent journalism. In February, an Addis Ababa court sentenced Somali journalist Mohamed Aweys Mudey to 27 years in prison for allegedly having information about a Somali al-Shabab terrorist cell operating inside Ethiopia. Several colleagues of Alemu and Nega are already serving sentences under anti-terror law.
Two Swedish journalists know all too well the consequences of being a journalist in Ethiopia, Africa’s second largest country and a leading recipient of EU aid. In December 2011, reporter Martin Schibbye and photographer Johan Persson were sentenced to 11 years in prison for “rendering support to terrorism” by interviewing people in the conflict-prone Ogaden region. Luckily for them, concerted international campaigns and diplomatic pressure helped win their freedom a year later.

Tuesday, April 1, 2014

ማህበረ ቅዱሳን ላይ የፖለቲካ ብትር መምዘዝ ለምን አስፈለገ?

በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስር በሚገኘው እና የተለያዩ አርኪ እና ስኬታማ ጉዞዎችን በማድረግ ታላቅ ስራ በሰራው በማህበረ ቅዱሳን ላይ ወያኔ የፖለቲካ ብትሩን በመምዘዝ ሊያወድመው መሆኑን ይህንን ሰሞን አበይት ከተባሉ ጉዳዮች አንዱ ሲሆን ይህንን ተከትሎ የወያኔ ካድሬዎች እና በሃይማኖቱ ውስጥ የተሰገሰጉ ቡችሎች ጸረ-ማህበረ ቅዱሳን ዘመቻቸውን ተያይዘውታል።

ለዘመናት በሰላማዊነታቸው ወደር ያልተገኘላቸውን የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ወኪሎች ባልተገኙበት ባልዋሉበት ባላሰቡት ባልደገሱት በአክራሪነት እና በአሸባሪነት በመፈረጅ እንዲሁም ህዝበ ሙስሊሙን በመግደል እና በማሰር በማንገላታት ላይ የተሰማራው ወያኔ የሽብርተኝነት ፍረጃ ካርታውን ወደ ተዋህዶ እምነት በማዞር ማህበረ ቅዱሳንን አሸባሪ በማለት ለስልጣኑ የሚያሰጉ መሆናቸውን በመደስኮር ላይ ይገኛል።

ለተነሳለት የከፋፍለህ ግዛ እና የጎሳ ፖለቲካ ፖሊሲ አልመች ብሎ የተገኘውን ሁሉ አሸባሪ አክራሪ በማለት ማህበረ ቅዱሳንንም ባልዋለበት የማክረር እና የማሸበር ድርጊት በመወንጀል ተግባር ላይ መሰማራቱ የጀመረውን ኢትዮጵያን ከፋፍሎ በጎሳ ቡድንተኝነት እያናከሱ በስልጣን ለመኖር ያሴረውን ሴራ እንደሚያከሽፍበት በከባዱ እንቅፋት ሆኖ ስላገኘው ነው።

የኢትዮጵያ ሙስሊሞችም ይሁኑ የተዋሕዶ አማኞች መሰረታቸውን ጎሳ ሳይሆን ኢትዮጵያ የሚል እደምታ መኖሩ እና በብሄር የተከፋፈለ አካሄድ አለመከተላቸው የወያኔ ስጋት ሆኖበታል። በመስኪዶችም ሆነ በቤተክርስቲያን ደረጃ ቀበሌያዊ የጎሳ ጥየቃ እና ምደባ አለመኖሩ ያንገበገበው ወያኔ የኢትዮጵያ አንድነትን የሚሰብኩ እና በህዝቦች መካከል ፍቅርን የሚያሰርጹ ሆኖ ስላሰበው ብቻ መፍረስ መደርመስ መሪዎቹን መታሰር እንዳለባቸው ግብሩ ይመሰክራል።

በሙስሊምም ይሁን በተዋህዶ አማኞች ቀኖና ውስጥ ቀለም ዘር ጎሳ የመለያየት ትምህርት አለመኖሩ የሃይማኖቱን ምሁራን የአንድነት የፍቅር እና የሰላም ተምሳሌት እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። ይህ ደሞ ለወያኔ የከፋፍለህ ግዛ የጎሳ ፖለቲካ የማይመቸው ስለሆነ ማህበረ ቅዱሳንን በ97 ምርጫ ወቅት ለወያኔ መሸነፍ አንዱ ተጠያቂ አድርጎ በሰነዱ ወንጅሎታል። ስለዚህ አምነቶቹን እና አማኞቹን ለመከፋፈል የሚችለው እንደ ማህበረ ቅዱሳን ያሉትን እና እንደ ሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን በአክራሪነት በአሸባሪነት በመወንጀል ማፈራረስ ከዚያም ማሰር ማንገላታት ስራዬ ብሎ ታያይዞታል።

ያሰማራቸውም ቡችሎቹ ለመጪው ምርጫ ስጋት ያሳድራል ስለተባሉ ብቻ በጭፍን ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ በጅምላ የሚያካሂዱትን ጥላቻ በማህበረ ቅዱሳንም ላይ ጀምረውታል። የኢትዮጵያን አንድነት በጠበቀ መልኩ ለመጪው ትውልድ ያስተላልፋሉ ታሪኬን ያበላሹብኛል ያላቸውን ሁሉ እየገዘገዘ መጣል የለመደው ወያነ በማህበረ ቅዱሳንም ላይ የጀመረው ግሬደራዊ የጥላቻ ዝቆሽ ከዚሁ ጋር የተያያዘ ነው።
እንደ ኢትዮጵያውያኑ ሙስሊሞች እና የተዋህዶ አማኞች ሁሉ ነገ ባለተራ የሆኑት የፕሮቴስታት አማኞችም ከወዲሁ ስጋት አድሮባቸዋል፡፤ በጎሳ ስም የተከፋፈለ የበተክርስቲያን እና የመስኪድ ስያሜ የተመኘው ወያኔ ይህንን ለማሳካት ደፋ ቀና በማለት ላይ ስለሆነ ኢትዮጵያውይንን በጋራ ሃይማኖት ሳንለይ ይህንን የእምነት ጸር የሆነ የሰይጣን ተልእኮ በመያዝ ሃይማኖቶችን ሊያደፈርስ የሚፈልገውን ሕወሓት/ኢሕአዴግ የተሰኘውን የሽብር እና በፖለቲካዊ አክራሪነት የአንድነት የፍቅር የሰላም ፀር የሆነውን ቡድን ወደ ከርሰ ማቃብሩ ልንከተው ይገባል ። 

 ድል ለኢትዮጵያውያን!!!