Search This Blog

Saturday, April 5, 2014

የኦሮሞ ህዝብ ትግል ከጭቁን የአማራ ህዝብ ጋር ሳይሆን ከገዢው መደብና ከቀድሞው ሥርዓት ነፋቂዎች ጋራ ነው

“ኢትዮጵያ ውስጥ የመገንጠል ጥያቄ ማንሳት ይቻላልን?” ለሚለው የአምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው ጽሁፍ መልስ


በአርዕስቱ ለመጥቀስ እንደሞከርኩኝ የኦሮሞ ህዝብ ትግል ከትውልድ ለትውልድ ሲተላለፍ የመጣው ከገዥዎችና ከረዳቶቻቸው የውጪ ኃይላት ጋር ነው። ይህ ህዝብ በነፍጥ አንጋቾች ቅኝ (አቅኝዎች) ሥር ከቀደቀበት ጊዜ አንስቶ አስከ ዛሬ ድረስ ትግሉን ያቁዋረጣበት ጊዜ የለም። ይህም የሆነበት ወቅት ብናስብ ሴሜቲኮች (ሓበሾች) ወደ ምስራቅ አፍሪካ ከመጡበት ጊዜ አንስቶ ነው። እነዚህ ህዝብ ወደ ምስራቅ አፍሪካ የመጡት በተለያየ ጊዜ ሲሆን፣ ሰበባቸውም የተላያየ ነው። ከመጡም በኃላ በኩሾች ንጉሥ (አባ ገዳ) “ኩሳ” በተባለ የሥልጣን ወይም የንግሥና ስም ስር በመተዳደር ነው። ቀስበቀ እየበረከቱ ሲሄዱ በተንኮልና በኃይል የነበረውን የኩሽ ህዝቦችን መስተዳድር ደምስሳው ሥልጣኑን ተቆጣጠሩ። የዛጉዌዎች ሥርወመንግስት መሃል ገብ እንጂ እስካሁን በሥልጣኑ ሲፈራረቁበት ቆዩ።
እስኪ አቶ አምሳሉ ገ/ኪዳን የጠቀሱልን “ታሪክ” እንመልከት።
“… ከጥንት ከመሠረት ጀምሮ የሚታወቁ ሀገራት አሉ እንደ ዓለም ታሪክና መንፈሳዊው ተረክ ስናይ ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ ከተመሠረቱ ህልው ከሆኑ ሦስት ሀገራት አንዷ ናት፡፡ በዚህ ዙሪያ የተለያዩ ተረኮች አሉ፡፡
አንደኛው ኢትዮጵያን የመሠረታት የአዳም ልጅ አሪ ወይም አራም ዓለም በተፈጠረ በ 970ዓመት ነው፡፡ የመጀመሪያ ንጉሷም እሱ ነው እስከ የጥፋት ወኃ ድረስ 21ነገሥታት ነግሠው ለ 1286 ዓመታት ኢትዮጵያን ገዝተዋል የሚል ተረክ ለብቻው አለ፡፡ ከጥፋት ውኃ በኋላም ኖኅ ዓለምን ለሦስቱ ልጆቹ ሲያከፋፍል አፍሪካ ለካም ደርሳው ነበርና ኢትዮጵያ ውስጥ ከነገሡት የነገደ ካም ነገሥታት የመጀመሪያው ካም ነው ብለው ከካም የሚጀምሩ አሉ፡፡ አይ አይደለም ከካም ሦስተኛ ትውልድ 2545 ዓመት ቅ.ል.ክ ከሰብታህ ነው የሚጀምረው ብለው ከሰብታህ የሚጀምሩም አሉ፡፡ በዚያም ሆነ በዚህ ሀገሪቱ ጥንታዊትና በሀገር ደረጃ በቀዳሚነት ከተጠሩ ሀገራት አንዷ ናት፡፡ በጥንት የዓለም ታሪክ መጻሕፍትም ሆነ በመንፈሳዊ መጻሕፍት ዛሬ አፍሪካ ብለን የምንጠራውን እንዳለ ኢትዮጵያ ነበር የሚሉት፡፡ በጥንቱ የአውሮፓዊያን የዓለም ካርታ ላይ አትላንቲክ ውቅያኖስን “የኢትዮጵያ ውቅያኖስ” ሲል ይጠራዋል፡፡ በሌላ በኩል ማሊ፣ ቻድ፣ ኒጀር ወደታችም ታንዛኒያ በሌሎች በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራትም ምንጫቸው ኢትዮጵያ እንደሆነ የሚናገሩ በርካታ ማኅበረሰቦች አሉ፡፡”
our struggle continues until we get our  freedom!!! ashenafi
ይህ ታሪክ ለመጸፍ የሞከረው ጳውሎስ ፓርሌ የተባለው ሊቅና ስለ ዓለም ታሪክ ከጂኦግራፊ ጋር በማዛመድ የጸፈው ሲሆን፣ ሓበሻው ደብተራ ዮሐንስ ወልደ ማሪያም ዘብሔረ ተጉለት በ1937 ዓ.ም ትርጉሙን በማዛባት ለራሳቸው እንዲመች አድርጎ የደብተራ (አለቃ) ታየ የተባሉትን “የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ” ብለው የጸፈውን ገልብጣው አስነበበን።
የአፍሪካ ህዝብ ታሪክ ደብተራዎቹ እንደሚጽፉት በሺህዎች (3ሺህ፣ 5ሺህ፣ 10ሺህ) ገለመሌ የሚገመት ሳይሆን አርኪሆሎጂስቶችና ስለ ፍጥረታት የሚያጠኑ ሳይንሲስቶች (ተማራማሪዎች) እንዳረጋገጡት በሚሊዮኖች ዓመታት የሚገመት ጊዜ ነው። ኢትዮጵያዊትዋ ሉሲ (ድንቅቱ) እናስታውሳት።
ወደ አቶ አምሳሉ ጽሁፍ ስንመለስ “ኢትዮጵያን የመሠረታት የአዳም ልጅ ኦሪ ወይም ኦራም ዓለም በተፈጠረ በ970ዓመት ነው፡፡” የሚለውን እናገኛለን። ይህ “ኦሪ ወይም ኦራም” ወይም የኦሮሞች ትውፍታ እንደሚለው ሆሪ ወይም ሆሮ ከሚለው ቃለት ጋር ይዛመዳል። በመሆኑም ኦሮሞች ከዚህ በመነሳት ኦሪ/ሆሪ፣ ኦራ/ሆራ፣ ኦሩ/ሆሩ በማለት የሰው ልጅ እንዴት እየተባዘ ኣሁን ደረጃ እንደ ደረሰ ይገልጸሉ። ስለሆነም ኦሮሞች (Horteen/umeen walaabu baate) ሆርቴን/ኡሜን ወላቡ ባቴ ይላሉ። በኦሮሞች አመለካከት ወላቡ ማለት ያለንበት መሬትን ጨምረው በአካባቢያችን ያለው ጠፈር/ህዋ ነው። ስለዚህ ኦሪ/ሆሪ የኦሮሞዎች ቀዳሚው አባት ነው። ኦሪትም የመጀመሪያ የአፍሪካኖች እምነት ነው። ኦሪት የኦሮሞዎች ቅድመ እምነትና አሁንም ቀሪ እሴቶች ያሉት ሲሆን፣ የሥልጣኔ መሰረትም ናቸው።
ይህን የአፍሪካን ህዝብ እምነት እንደ እራሱ ፈጠራ አድርጎ የወሰደው ከእሥራኤላዊ ነገድ የሌዊ ጎሣ የሆነው ሙሴ(ሙሳ) የተባለ ሰው ነው። እሱም ተወልዶ ያዳገው በግብጽ አገር በፈረኦኖች ቤተመንግሥት ውስጥ ነው። ሁሉን ነገር የተማራው እዚያው ነው። በኃላ አንድ ግብፃዊ ገድሎ ጉዳዩ ስለታወቃበት እዚያው ግብጽ ውስጥ ወደ ደቡብ አቅጣጫ ኮበለላ። እዚያ በሄደበትም ቦታ የዚህ አፍሪካዊ የሃይማኖት አባት የሆነውን ሄትሮ/ገትሮ የተባለ ቅዱስ ሰው አግኝቶ ቤተሰብ ውስጥ አባል በመሆን በጎቹን እየጠበቀና ሴት ልጆቹን አግብቶ ሲኖር ቆይቶ፣ እዚሁ ቦታ በእግዜብሔር ተራራ ላይ የኣምላክ መንፈስ ቀርቦት ወደ አገሩ ወደ ፓለስታይን እንዲሄድ አዘዛው። በእንዲህ ሁኔታ የነበረው የይሁዲ መህበረሰብ ከሙሴ ጋር ወደ ጵለስቲኖች ምድር ሄዱ። በመሆኑም የዚህ የቀደምት የሰው ዘር የሆነውን ታሪክ የራሳቸው በማድረግ ሥልጣኔውም እምነቱንም፣ የሰው ልጅ መገኛውንም ወደ መካከለኛው ምስራቅ ወሰዱት። ከዚህ በመነሳት ለአፍሪካዊው ህዝብ “ሃም/ኩሽ” የሚል በመስጠት በሃይማኖት መጽሐፍ ውስጥ እንዲመዘገብ አደረጉ። ይህንኑ የሃይማኖትና የህብሩ መጽሀፍ ደግሞ ግሪኮች በጊዜያቸው ወደ እራሳቸው ቁዋንቁዋ ሲገለብጡ “ኩሽ” የሚለውን “ኢትዮጵ” አሉ። እዚህ ላይ ተውላጣው ስም ይላያይ እንጂ የሁለቱ ትርጉም አንድ ሲሆን “ጥቁር ህዝብ” ማለት ነው።

ቅድም እላይ እንደ ጠቀስኩኝ ቀዳሚው የሰው ዘር መገኛ ኤሲያ ሳይሆን አፍሪካ ውስጥ ነው። የኤደን ገነት የሚባለውም እዚሁ አፍሪካ ውስጥ ነው። ይህን እውነተኛ ታሪክ ለማጥፋት ይሁዲዎችም፣ አውሮጳዎችም አረቦችም ብዙ ጥረዋል። ብዙ ሰነዶችን፣ የእጅ ጥባባትን፣ ቅርሳቅርሶችን ደምስሳዋል. ግሪኮች ግብጽን ሲዪዙ 40,000 ከድንጋይና ከሌሎች ነገሮች የተሰሩ ሃውልቶችን አውድሞዋል። የሄሮግላፍክስ ጽሁፎችን ደምስሳዋል። በኃላ የመጡ ሮማዊያንም ተመሳሳይ ድርጊት ፈፅማዋል። እንድሁም በሃይማኖት ሰበብ በተነሳውና የክርስትናን እምነት ለማስፋፋት ሲባል “የኣህዘብ” የተባለውን የአምልኮና የታሪክ መጽሀፍትና ቅርሳቅርስ አውድማዋል። በተመሳሳይ ሁኔታ የእስልምና ሃይማኖት ወደ አፍሪካ ሲስፋፋ ቀደምቶቹ የውጪ ኃይላት ያደረጉትን ዓይነት ጭካኔ በተመላበት ድርጊት “የኣህዘብ” የተበለውን ሁሉ እና በክርስቲና ስም የተጀመረውንና መልሰው የመገንባትን ሥራ እንደገና ደምሰሳዋል።
ስለዚህ እስራኤሎችም ሆኑ ግሪኮች ለዚያው ለቀደምት የሰው ዘር ኦር/ኦራም አዲስ ስም ሰጡት እንጂ በውሃ የተደመሰሳ ህዝብ የለም። ምናልባት በዚያው በመካካለኛው ምሥራቅ የሉትን ህዝቦች በጎርፍና በተለያዩ ነገሮች፣ ለምሳሌ እንደ ጃፓኑ ሱናም, እንደሰሜን ኣሜሪካው ካተሪን አሪካን, ወይም አሪካን ጉስታቭ አይናት መዓት ወርዶባቸው ይሆናል። እንጂ አፍሪካዊው የኣምላክ ፍጡራን በውሃ ኣልጠፉም። የአፍሪካ ህዝብ ወደፊትም “8ኛው ሺህ” የጥፋት በትር ይመጣል በተባለውም ጊዜ አይጠፉም።
ወደ ታሪክ ስንመለስ ደግሞ የአርክዎሎጂና የመስክ የሳይንስ ጥናቶች እንድሚከተልው ያቀርቡታል።
“Ethiopians were the first men that ever lived, the only truly autochthonous race and the first to institute the worship of the God and the rites of sacrifice.”“The Cyclopedia of Biblical Literature says, “There is every reason to conclude that the separate colonies of priest craft spread from Meroe into Egypt; and the primeval monuments in Ethiopia strongly confirm the native traditions, reported by Diodorus Siculus, that the worship of Zeus-Anumon originated in Meroe, also the worship of Osiris.”
ሌላው ሊቅ ደግሞ ስለ የሰው ልጅ መገኛና የሚጠቀምባቸው የጥንት መሣሪያዎችን ሲያመለክት እንዲህ ብለዋል።
“The oldest artifacts yet discovered come from the area of the river GONA in Ethiopia. … To the untutored eye a primitive stone axe from Gona looks little different from any pebble in the area
The latest evidence suggests that modern humans left Africa twice, first around 90,000 years ago, through Sinai into the Levant, an exodus which petered out.” (Peter Watson p. 23)
ስለ ጎና ወንዝ “the river GONA in Ethiopia” ከተነሣና ይህ ወንዝ ደግሞ ስሙ የኦሮሞ ስም መሆኑን ከብሔሩ ጎሣ አንዱ ሆኖ እናገኛለን። ምክንያቱም ኦሮሞ መሬቱንና ወንዞቹን በጎሣው ኣባቶች ስም ይሰይማልና። ስለዚህ ይህን በተመለከተ ፕሮፌሶር ኣስመሮም ለገሣ በኦሮሞች አካባቢ ባደረጋው የመስክ ጥናቱ ውስጥ እንደሚከተልው አስፍረዋል።
“The council of election of the Gona Moiety consists of men elected from the Qallu lineage of the Oditu clan. …The council, headed by the Qallu, constitutes the top leadership of the moiety.
The Qallu’s home is the repository of the most important collective symbols of the Gona moiety. Borana clan leaders gather every eight years for the Muda ritual. On that grand occasion the Qallu is presented with large numbers of cattle, and he gives his blessing to all the clans and any individual who comes to pay homage to him.” (Asmerom Legesse 1964)
የመስክ ተመራማሪዎች ስለ ኩሽ ህዝቦች የእምነት መሰረት ሲያትቱ እንደሚከተለው ያቀርቡታል።
“The primitive worship of the Ethiopians was pure. They worshipped one Supreme Being. Their rulers were priest-kings and at death were deified. As the ages ensued this intended itself in ancestor worship, which was original with the Cushite race. It flourishes on the African continent today. Ancestor worship spread over all the countries which the Cushites conquered.
Modern research is leading us to Khufu, the belief that culture was spread in Egypt from the south, especially from Meroe. The country was first ruled over by contemporary kings, who were at war with each other. At last the common difficulties in harnessing the Nile united them under Menes 5500 years BC. For a thousand years the capital remained at Memphis. This was the old kingdom, the period of the pyramid builders.” (Wonderful Eth. of anc. Em. P.77)
ሌላው ስለ ኩሽ ህዝቦች መስፋፋት የሚገልጽ ሰነድ ደግሞ እንዲህ ይላል።
In Africa the Ethiopian, the Egyptian, The Libyans, the Canaanites’ and Phoenicians were all descendants of Ham. They were a black or dark colored race and the pioneers of our civilization. They were emphatically the monument builders on the plains of Shinar and the valley of the Nile from Meroe to Memphis.
“In those primitive days, the central seat of Ethiopia was not the Meroe of our day, which is very ancient but a kingdom that preceded it by many ages, that was Called Meru.”
Lenormant spoke of the first men of the ancient world as “Men of Meru.”
እዚህ ላይ መጥቀስ የሚያስፈልግ ጉዳይ መሩ“Men of Meru.” የሚለው ቃል ከኦሮሞ ቃላቶች አንዱና ተመሳሳይ ትርጉም መኖሩን ያመለክታል።
በመቀጠል ስለ ኩሽ ህዝቦች ሥልጣኔና የአስትሮኖሚ እውቀት የሚያትት ሰነድ ደግሞ በዚህ ሁኔታ ተቀምጣዋል።
“The ancient kingdom of Meroe was upper Nubia and was divided into agriculture and grazing lands.
In the oldest recorded traditions, Cushite colonies were established in the Valley of Nile, Barabra and Chaladea.” These beginning must have been not later than 7000 or 8000 BC or perhaps earlier. The Greeks also said that Egyptian derived their civilization and religion from Ethiopia. The highly developed Merodic inscription are not forwarded in Egypt north of the first cataract or in Nubia south of Soba.
The Greeks looked to old Ethiopia and called the upper Nile the common cradle of mankind. Toward the rich luxuriance of this region they look for the “Garden of Eden.” From these people of the upper Nile arose the oldest tradition and rites and from them sprang the first colonies and arts of antiquity. They brought to development astronomy and the other science, which have come down to us.
የኩሽ ህዝቦችን አስትሮኖሚ እውቀትና, በስናፈለክ ላይ የተመሰረተ የጊዜ ቀመርን እንዴት እንደፈጠሩና ሲጠቀሙበት ቆይተው ለዓለም ህዝብም እንዴት እንደተስፋፋና በሃይማኖት አማካይነት ለሓበሻ-ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እንደተሰጠና፣ እስካሁንም የግዕዝ ተብሎ የግላቸው እንዳደረጉ ማስተዋል ይቻላል።
ዘንድሮ በግዕዝ 2006 ነው የሚባለው ቀድሞ የኩሾች የነበረና በኃል ኢጣሊያዊው ጁሊዮስ (ጁሊያኖ) የተባለው ሰው የቀመረው ነው።ይህም ቀመር እስከ 1580 እ.አ.አ ሁሉም ዓለም ይጠቀምበት ነበር።
ይህ የኩሽ ህዝቦች የስናፈለክ ጥበብ ከጥንት ጀምሮ ከኦሮሞ ህዝብ እንደልተለየና በአሁኑ ጊዜ በቦራና ኦሮሞዎችና በመእካላዊ ኦሮሚያም በአሁኑ ጊዜ በሥራ ለይ መኖሩና አያንቱዎች የቀኑና የኣመቱን የስራ ክንውን የሚያራሚዱበት ጨረቃንና ክዋክብትን በማገናዘብ የቀን መቁጠሪያውን ሲጠቀሙበት እናያለን። ይህ የጥንት የአስትሮኖሚ ኣጠቃቀም በኦሮሞች ዘንድ መኖሩ፣ ይህ ህዝብ የምስራቅ አፍሪካ ነበር ህዝብ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው። ስለዚህ ሓበሾች ቀይ ባህርን አቁርጠው ከመጡ በኃላ እዚሁ አገኙት እንጂ ይዘው የመጡት ነገር የለም። ሁሉን ነገር በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በኩል ከእስኪንዲሪያ ተለከላቸው። ፍትሃ ነገሥቱና ክብረ ነገስቱም ከግብጽ መጥቶ ከአርብኛ ወደ ግዕዝ ተተርጉሞ ነው።
“The ancient Egyptians divided the year into twelve lunar months, of thirty days each, with five additional days at the end, which were considered very unlucky. This calculation was achieved on purely practical grounds, being the average amount of time between successive arrivals of the Nile flood at Heliopolis (the most impotent event in Egyptian life). The Egyptians soon noticed that, in fact, the actual year is slightly longer, 365 ¼ days, and made the adjustment. They also noticed that the rising of the Nile Occurred just as the last star appeared on the horizon, the Dog Star Sothic (Sirius as we would say). This ‘heliacal rising’ became the fixed point of the so called ‘Sothic calendar, and was more regular, and more accurate, than the flooding of the Nile.
Astronomical calculations have shown that the first day of the two calendars- the pre-Sothic and the Sothic agreed in 2773 BC, and scholars have concluded that this must have been when the Sothic calendar was introduced. So for the Egyptian, whether they knew it or not, the year 0 was in fact 2773.”
ሌላው ስለ ፊደላት በተመለከተ የሁሉ የዓለም ህዝቦች በኣሁኑ ጊዜ የሚጠቀሙት መሰረቱ የኩሾች የሆነውን ነው። ቻይናና የሩቅ ምስራቅ ህዝቦች በስተቀር። የሂንድ እራሱ መሰራቱ የኩሾች ከሜት የተባለው ነው።
ይህ አሁን እየጸፍንበት ያለው የግዕዝ ፊደል የተባለው ግማሹ የፌንቃዊያን ግማሹ ደግሞ ከግሪክ ቁጥሮችና ከግብጽ ፊደሎች የተወሰደ ነው። ይህንንም ያደረጉት “ከሰተ ብርሃን ወይም ቀዳማዊ አቡነሰላማ” እና አብሮ የመጡ የግሪክና የግብጽ ሊቃውንቶች ናቸው። ከዚህ ቀጥሎ ያለውን ሰንጠረዥ ይመልከቱ.
Kemetic alphabet of Ancient Egypt/Kemet and the Upper Nile Valley of Ancient Africa. The Greek alphabet, the script of English today, is based on the Kemetic alphabet of Ancient Egypt/Kemet and the Upper Nile Valley of Ancient Africa. Ancient Egyptians called their words MDW NTR, or ‘Metu Netter,” which means divine speech. The Greeks called it, ‘hieroglyphics”- a Greek word. The etymology of hieroglyphics is sacred (hieros) carvings (glyph). The Oromos (the Kemet of modern age) called it Qubee.
የግዕዝ ፊደላት እንዴት እንደተፈጠሩና እንደተበወዙ የሚያሰይ ሰነድ ከተች የተመለከተውን ይመስላል።
በተያያዘ ሁኔታ የቤተክህነት የተባሉት ቁጥሮችም የግሪኮች ነው። “ጽርኣዊያን” ማለት ግሪካዊያን ማለት ነው። እንዲሁም “ቅብጣዊያን” ማለት ግብጻዊያን ማለት ነው። ስለዚህ ታሪክ ለባለታሪክ እውነትነትና ተረትነት አንድ ቀን ሀቁ ፍንትው ብሎ እንደሚወጣ መገንዘቡ አስፈላጊ ነው። በዚሁ ሰበብ ለማስገንዘብ የምፈልገው ነገር ኦሮሞች የላቲን ፊደል ለቁዋንቁቸው (ለኩሽ ቤተሰብ በሙሉ) አመቺ መሆኑን ተረድተው መጠቀም ሲጀምሩ የሓበሾች ጩሀት አያድርስ ነበር። ምንድር ነው ታዲያ እነሱስ ከፌንቃዊያን፣ ከግሪካዊያንና ከግብጻዊያን ፊደሎች የተውጣቱ ፊደሎችን ወስደው የራሳቸው አድርገው፣ ለቁንዋቁቸው እንዲመች አድርገው በቅደም ተከተል በውዛው ተጠቅመውባታል። ስለዚህ የኦሮም ህዝብም የፈለገውን የመዋስ፣ የመውሰድና የመጠቀም ሙሉ መብት አለው። ይህም መብት እራሱ የሚመርጠው እንጂ ሌሎች አውቅልሃለሁ በሚሉት ጮሌዎች የሚመረጥለት አይደለም። ይህ ምርጫውም እነርሱ እንደሚሉት “ጥቁር ፈረንጅነት” ሳይሆን የፊደሎቹ አፈጣጠር በቅድሚያ በኩሾች ቤተሰብ ነውና። ኦሮሞም የዚሁ ቤተሰብ አባል ነውና።
ሌላው ከኣቶ አምሳሉ ጽሁፍ ለማየት የሞከርኩት እንደሚከተለው የተገለጸውን ነው። እንዲህ ይላል።
“ከዚህ ባሻገር ስላሉ ነገሮች ስናወራ በሀገራችን በርካታ ብሔረሰቦች የሚያቀርቡት ቅሬታ አለ፡፡ በማንነታችን እንድናፍር እንድንሸማቀቅ እንደረግ ነበር፣ እንደ ዜጋ አንታይም ነበር የሚለው ቅሬታ ወይም በደል አልነበረም አልተፈጸመም ማለት አይቻልም ነገር ግን ምክንያታዊ እንደነበር ልንገነዘብ ይገባል፡፡ በአርግጥ ዛሬ ላይ ሆነን ስናየው ፍጹም አግባብነት የሌለው ሆኖ አናገኘዋልን፡፡ ነገር ግን ይህ ከጥንት ጀምሮ የነበረ ጥቃት እንዴት ሊፈጠር ቻለ? የሚለው ጉዳይ መጤን መመርመር ያለበት ጉዳይ ይመስለኛል፡፡ ያለ ምክንያት የሚፈጸም ምንም ነገር የለምና አንዴትና ለምን የመገለል እንደ ዜጋ ያለመቆጠር ጥቃት ሊደርስባቸው ቻለ ለሚለው ቅሬታ የኦሮሞን ብሔረሰብ በተመለከተ ወደ 16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወደ ኋላ፤ የትግሬን ብሔረሰብ በተመለከተ ወደ አምስተኛው መቶ ክፍለ 44ዘመንና አምስት መቶ ዓመታት ከዚያ ወደኋላ በመመለስ በዚያ ወቅት የነበረውን ሁኔታ ብናየው የዚህ በደል መንስኤ ምን እንደሆነ እንረዳለን፡፡”
በዚህ አንቀጽ እንደተመለከተው የኦሮሞን ህንዝብ የኃላ መጤ እንግዳ አድርጎ የማቅረብ ሁኔታ ይንጸባረቃል። እራሱ አፍሪካ የኩሽ/ሓም ህዝቦች ምድር ነው እያለ፣ ከኃላ ከኣረብ ሃገር የመጠውን የቤት ባለቤት ሲያደርጋው ምን ይባላል ጃል?
በመጀመሪያ ደረጃ የኦሮሞ ህዝብ ጸሐፊው እንደሚለው “ብሔረሰብ” ሳይሆን ትልቅ ብሔር ነው። በአፍሪካ ከሚገኙት ብሔሮች በመጀመሪያ ረድፍ ላይና ቁዋንቁዋውም ከአውሳና ዙሉ ቀጥሎ በሶስተኛነት ደረጃ ላይ ይገኛል።
በሌላ በኩል እኔ ይህን የማየው ግለሰቡ ከደብተራዎች ድርሰት አዙሪት ውስጥ የገበና መውጣትም መንገዱ የጠፈው ይመስላል። የኦሮሞ ህዝብ የምስራቅ አፍሪካ ነባር ህዝብና የሁሉም የምስራቅ ኣፍሪካ ህዝቦች መሰረትና ቀዳሚ አባት ነው። በሰሜናዊ ምስራቅ አፍሪካ ከኑቢያ (ኑቢያ) ወይም ሜሮዌ ወይም መረዋ አንስቶ እስከ ህንድ ውቅያኖስ ተንሰረፍቶ እየኖራ እያለ ከኣረቢያ የመጡ ሴሜቲኮች (ሓበሾች) ወደ ደቡብ ገፉት። ግፍያና ዘረፋ ሲበዛበት ወደኃላ ተመልሶ በማጥቃት የተወሰደበትን መሬቱና ነጸነቱን የተነጠቀው ቀሪ ማህበረ ሰቡን ነጻ እያወጣ ወደ ራሱ ቀላቀላቸው። ይህ የሆነው የአውሮጳ ዘመናዊ መሣሪያ መጥቶ እስከ ገላገላቸው ጊዜ ድረስ ነው።
ስለዚህ የኦሮሞ ህዝብ የተነጠቀውን ነጻነቱን፣ ሉዓላዊነቱን ለመመለስ ከማንም ፈቃድ አይጠይቅም። የኦሮሞ ህዝብ ትግል ከጭቁን የአማራ አርሶ አደር ጋር ሳይሆን በነፍጥ ኃይል ከወራራው የነፍጣኛና የነፍጣኛ ስርዓት ናፋቂዎች ጋር ነው። የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ የነጻነት ጥያቄ ነው። የኦሮሞ ነጻነት ግንባርም ዓላማ ስሙ እንደምናግረን ለኦሮሞ ህዝብ ነጻነት ነው እንጂ ስለ ኢትዮጵያ መገነጣጣል ያነሳበት ጊዜ ያለ ኣይመስለኝም። ምክንያቱም ትልቅ ህዝብ ወዴት ነው የሚገነጠለው። ቅርንጫፎች እንደአማራ ሳይንት, እንደትግራይ እንደኦጋደን ጋምቤላ ያሉ የኢምፓየሪቱ ዳርዳር የሉ ሊገነጠሉ ይችላሉ። የኦሮሞ ህዝብ በለበት ቦታ ላይ ነጻነትና የአገሩ ሙሉ ባለቤትነት መሆንን ነው የሚፈልገው። ይህንን ደግሞ ከማንም በችሮታ ለመግኛት አይጠብቅም። የማንንም አውቅልሃለሁን የፖላቲካ ሥራ አይፈልግም። የራሱን እድል እራሱ ይወስናል።

No comments:

Post a Comment