Search This Blog

Monday, March 3, 2014

የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በአቶ አለምነው መኮንን ንግግር ላይ መግለጫ ሳያወጣ ተጠናቀቀ

ስብሰባውን በባህርዳር ከተማ ሲያካሂድ የሰነበተው የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ የንቅናቄው የጽህፈት ቤት ሀላፊ የአማራውን ህዝብ የዘለፉበትን ንግግር ያስተባብላል ተብሎ ቢጠበቅም፣ ምንም ሳይል ቀርቷል። ንቅናቄው ” ህዝቡ በተቃዋሚዎችና ተባባሪዎቻቸው የሚነዙ አሉባልታዎችን ወደ ጎን በማለት ከብአዴን ጎን ጎን እንዲሰለፍ” የሚል መግለጫ በማውጣት ስብሰባውን አጠናቋል። በጉዳዩ ላይ አስተያየቱን የጠየቅነው አንድ የብአዴን አባል፣ አቶ አለምነው ቀድሞውንም የተናገረው  የብአዴንን አቋም መሆኑን አውስቶ ንቅናቄው ከገባበት አጣብቂኝ ለመውጣት ለይምሰልም ቢሆን፣ የጸጸት ድምጹን በማሰማት ህዝቡን ለማረጋጋት ይደፍር ይሆናል የሚል እምነት ነበረኝ፣ አሁን እንደምናየው ግን ብአዴን እንደ ህወሃት ሁሉ ህዝብ ምን ያመጣል” በሚል ንቀት መጓዝን መርጧል ” ብሎአል። አቶ አለምነው መኮንን በአማራው ህዝብ ላይ የተናገሩትን አስጸያፊ ስድብ በመቃወም በባህርዳር በርካታ ህዝብ በተገኘበት የተቃውሞ ሰልፍ መካሄዱ ይታወሳል።
በሌላ በኩል ደግሞ በመተማ አካባቢ የሚኖሩ አንዳንድ ሰዎች ለግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል ወጣቱን ታመላልሳላችሁ በሚል ተይዘው አሰቃቂ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ለኢሳት ገልጸዋል። እነዚሁ የአካባቢው ተወላጅ ያልሆኑ የደህንነት ሃይሎች፣ የሚጠረጥሩዋቸውን ሰዎች እየያዙ ” ለግንቦት7 ሰዎችን ወደ ኤርትራ የሚያመላልሱ ሰዎችን ታውቃላችሁ፣ አውጡ በማለት በማሰቃየት ላይ መሆናቸውን ኢሳት ያነጋገራቸው ሰዎች ገልጸዋል። አንድ የአካባቢው ነዋሪ፣ በደረሰበት ከፍተኛ ድበደባ ቆሞ ለመሄድ አለመቻሉንና የሰሜን ጎንደር የአንድነት ፓርቲ ተወካዮች ተባብረው መጠነኛ እርዳታ እንዳደረጉለት ተናግሯል።

የደሴ ሕዝብ በኢሕኣዴግ የግዳጅ መዋጮ ተማሯል::በደሴ ወንጀል በመበርከቱ የሰአት እላፊ ገደብ ተጥሏል::

በከተማዋ ፌዴራል ፖሊሶች በምሽት ወታደራዊ ልምምድ ያደርጋሉ::
የደሴ ሕዝብ ከመለስ ፋውንዴሽን ጋር በተያያዘ ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ ይፈለግበታል::

      ከደሴ የሚደርሱኝ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት በሕወሓት አዛዥነት በብኣዴን ሰብሳቢነት የመለስ ዜናዊን አመራር አካዳሚ ሕንጻን ለመገንባት የመለስ ፋውንዴሽን ከህዝቡ ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚጠበቅበት እና ለግንባታው የግዴታ አስታውጾ እንዲያደርግ እያስገደዱት መሆኑን እና ሕዝቡም ከኑሮ ውድነት ጎን ለጎን ከአፉ ላይ ሊጎርሰውን ያዘጋጀውን በጉልበተኞች እየተነጠቀ መሆኑን በማማረር አቤቱታውን ማሰማቱን የደሴ የለውጥ ሃዋርያ ወጣቶች አንድነት ለምንሊክ ሳልሳዊ በላከው መረጃ ገልጽዋል::

መረጃዎቹ እንደጠቆሙት የገንዘብ አሰባሰቡ ሂደት በሁሉም ክፍለከተሞች ባሉ የወያኔ ካቢኔዎች ሲሆን እያንዳንዱ የካቢኔ አባል በግል እንዲሰበስብ የገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ የተሰጠው ሲሆን ከፍተኛ ገንዘብ ለሰበሰበ ሽልማት ስለሚሰጠው የሚል ቅል ስለተገባላቸው የስልታን እና የደሞዝ እድገት ለማግኘት እና ታማኝነታቸውን ለማረጋገጥ በሽፍን ድጋፍ ሕዝቡን በግዳጅ እና በማስፈራራት በዛቻ ገንዘብ እንዲያዋጣ እያደረጉት ሲሆን ይህንን በተመለከተ ሕዝቡ በቤቱ አሊያም በስብሰባ ካልተገኘ በቅጣት ሁሉ መልክ ተጨማሪ እንዲከፍል ይደረጋል የሉት የምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች ሕዝቡ በሚሄድበት መስሪያቤት አሊያም ስብሰባ ቀደም ብሎ የከፈለ ሰው ደረሰኙን ካልያዘ ጉዳዩን ለማስፈጸም በድጋሚ እንዲከፍል የሚደረግ ሲሆን እረስቸዋለሁ ሄጄ ላምጣ የሚል ነገር ተቀባይነት የለውም::

እንዲሁም በደሴ የብኣዴን ጽ/ቤት ሃላፊነት ተጨማሪ ለመለስ ፋውንዴሽን በሚል በግዳጅ ገንዘብ እየተሰበሰበ ሲሆን የጽ/ቤቱ ሃላፊ የሆኑት አቶ ጌታዊ ይርጋ (የቀድሞ የኮምቦልቻ ከተማ ከንቲባ) ከዚህ ቀደም በሙስና ታስረው የነበሩ እና ከህግ ውጪ ለፖለቲካው አስፈላጊ ሆነው በመገኘታቸው በትእዛዝ ከተፈቱ በኋላ ሲቭል ሰርቭስ ኮሌጅ ተልከው ሰልጥነው በደሴ የብኣዲን ጽ/ቤት ሃላፊ ሆነው ከተመደቡ ጀምሮ በግዳጅ ከእጅ ወደ አፍ የሚኖረውን በኑሮ ውድነት የተማረረውን ህዝብ እያስገደዱ የመንግስት ሰራተኛውን ከደሞዙ ላይ 30% እንዲቆረጥ ውሳኔ በመስጠት እንዲሁም በየቤቱ የብኣዴን ካድሬዎች እየዞሩ ከቀበሌ ሰዎች ጋር በመሆን ሕዝቡ 100 ብር እንዲከፍል በበደል ላይ በደል እየፈጸሙበት ይገኛል:: እንዲሁም ባለሃብቱን እያስገደዱት ያሌለን ገንዘብ እንዲተፋ ወጥረው ይዘውታል ሲሉ ለምንሊክ ሳልሳዊ መረጃውን ልከዋል::


====================================
በሌላ ዜና በደዜ ከተማ ዙሪያ ጨለማን ተገን አድርገው የሰዎች ግድያ እና ዝርፊያ ወንጀሎች ከበፊቱ በበለጠ በመበርከቱ የከተማው ፖሊስ መምሪያ ማንኛውም የከተማው ነዋሪ ከምሽቱ አራት ሰአት በኋላ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርግ የሰአት እላፊ ገደብ መጣሉን የከተማው ነዋሪዎች ጠቁመዋል።


ባለፉት ሁለት ቀናት በመላው አገሪቱ የተካሄዱትን ፍተሻዎች በተመሳሰለ መልኩ የሞባይል ቤቶች እና የኢንተርኔት ካፌዎችን እንዲሁም የመረጣቸውን ብሎም የጠረጠራቸውን ግለሰቦች በድንገት ፍተሻ በማካሄድ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሞባይሎች ላፕቶፖች ዲስክቶፖች ኮምፒተሮች እና የሚሞሪ ካርዶች ሰብስቦ የወሰደው የደሴ ፖሊስ ሰአት እላፊውን ጥሶ የተገኘ ነዋሪ በጸጥታ ሃይሎች ለሚወሰድበት ማንኛውም እርምጃ መንግስት ተጠያቂ እንደማይሆን ገልጿል::

ከዚሁ ጋር በተያያዘ መረጃ የደሴ ከተማ በፌዴራል ፖሊስ ወታደራዊ ልምምድ ተወጥራ እንደምታመሽ ታውቋል:; ቁጥራቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ የፌዴራል ፖሊሶች ከምሽቱ 3 30 ጀምሮ ወታደራዊ ልምምድ ለማድረግ በዋናው የከተማዋ መንገዶች በመጠቀም ላይ ሲሆኑ በህዝቡ ላይ ሽብር እየነዙ መሆኑን ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ነግረውታል::ይህንን እያደረጉ ያሉት የከተማውን ነዋሪ ለማስፈራራት እና ለማሸበር እየጣሩ እና በሃርቡ አከባቢ የሚንቀሳቀሱ የፌዴራል ፖሊሶች ለሊቱን በወታደራዊ ልምምድቸው ጊዜ ስለሚጮሁ ህዝቡን ከስራ ቤቱ ገብቶ እንዳያርፍ እንቅልፍ እየነሱት ሲሆን ምን ያክል መንግስት ጭንቀት ላይ እንዳለ ያሳያል ሲሉ መረጃውን የላኩት ነዋሪዎች ገልጸዋል::መረጃውን ላቀበላችሁኝ የደሴ ወጣቶች አመሰግናለሁ።

መንግስታዊ ውሸት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውድቀት ትልቅ ሚና ተጫውቷል:

ሕወሓት/ኢሕኣዴግ መራሹ መንግስት የያዘውን ስልጣን ለመቀራመት አሰፍስፈው በጥላቻ ፖለቲካ ለሚዳክሩት ሁሉ ሊሰለጥኑ እንደሚገባ ልንነግራቸው ይገባል::ካልሆነ እንደኢሕኣዴግ ያሉ የሃያላኑ ስልጡን ማፊያዎችን መጣል ከባድ ይሆናል::ጥያቄው የለውጥ ጥያቄ ነው ::ኢሕኣዴግ መስማት ከቻለ ጥያቄው ይህ ነው :: የፖለቲካ ተሃድሶ እንዳልን ሁሉ የኢኮኖሚ ተሃድሶም ያስፈልገናል::ያለውን የኢኮኖሚ እደምታ ለመገምገም ሳይሆን መጪው ጊዜ በለውጥ የታጀበ የኢኮኖሚ ፖሊሲ እንዲኖረን ለማሳሰብ ነው:: ባለፊት አመታት እያልን እንደፈረደብን ማላዘን ሳይሆን መጪውን ጊዜያት ማሰብ ካለብን ለዚህ የባከነ ትውልድ እረፍት እንሰጠዋለን::

የሕወሓት የንግድ ድርጅቶች ህዝብን ማእከል ያደረገ ድህነት እንዲፈጠር አድርገዋል::ሃገርን ለኪስራ ዳርገዋል::የሕወሓት ድርጅቶች በሞኖፖል የተቆጣጠሩ እና ፖለቲካው የሚያሽከረክራቸው የንግድ ድርጅቶች ለሃገር እድገት ጋሬጣ ከመሆናቸውም በተጨማሪ ለሙስና መስፋፋት ለስልጣን መባለግ እንዲሁም ለድህነት መንሴ ሆነው ተገኝተዋል::እነዚህ ድርጅቶች በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ነጋዴዎችን ከገበያ አባረዋል::አክስረዋል በመቶሺህ የሚቆጠሩ ዜጎችን ከሃገር አሰድደዋል::በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ከመንግስት አዘርፈዋል ዘርፈዋል:; በትሪሊኦኖች የሚቆጠር ገቢን መንግስትን አሳጥተውታል::ህዝብን ማእከል ያደረገ ድህነት እንዲፈጠር አድርገዋል::ሃገርን ለኪስራ ዳርገዋል::በተጭበረበር ፖለቲካ ላይ የተገነባ ኢኮኖሚ ዋጋቢስ ነው::

ሕወሓት/ኢሕኣዴግ መራሹ መንግስት የያዘውን ስልጣን ለመቀራመት አሰፍስፈው በጥላቻ ፖለቲካ ለሚዳክሩት ሁሉ ሊሰለጥኑ እንደሚገባ ልንነግራቸው ይገባል::ካልሆነ እንደኢሕኣዴግ ያሉ የሃያላኑ ስልጡን ማፊያዎችን መጣል ከባድ ይሆናል::የሃገራችንን ኢኮኖሚ የመሰረቱት ከብሄራዊ ጥቅማቸው አኳያ ቅጥኛ የሆኑ ኢኮኖሚስቶችን አስርጎ በማስገባት ላለፉት 35 አመታት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በተጭበረበረ ፖለቲካ ላይ እንዲመሰረት አድርገውን ለኪሳራ አሳልፈው ሰተውናል::ህዝቦች ባልተጠና እና በቶሎቶሎ በተዘጋጀ የኢኮኖሚ ፖሊቺ እየተመሩ የሄዱበት ጉዙ እልህ አስጨራሽ ብቻ ሳይሆን ከስኬት ይልቅ ለኑሮ ኪሳራ ዳርጓቸዋል::ይህ ደሞ ሃገሪቱን እመራዋለሁ ከሚለው መደብ የተፈጠረ ዝብርቅርቆሽ ነው::

መንግስታዊ ውሸት በራሱ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውድቀት ትልቅ ሚና ተጫውቷል:: የመንግስት መገናኘ ብዙሃን በተለመደ መልኩ ውሸት ሲደጋገም እውነት ይሆናል በሚል ፈሊጥ ህዝባን እያታለሉ የልተፈጠረ እና ያልተደረገ ነገር እየደሰኮሩ ሃገርን ለኪሳራ መዳረጋቸው የአደባባይ ሃቅ ነው::ይህ ውሸት ደሞ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ያመጣው ተጽእኖ ቀላል የሚባል አይደለም ::
በተጨማሪ ሃገር በባዶ ካዝና እየተመራ ባለበት በዚህ ወቅት ከውጪው አለም የተለያዩ ብድሮችን በማምጣት 3 መጪ ትውልድ ሊከፍለው በማይችለው እዳ ውስጥ ሃገሪቷ እንድትነከር አድርገዋል::የመጣውን ብድር ህዝቦች ከድህነት እንዲላቀቁ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ለሃገር የኢኮኖሚ ዋልታዎች ማደግ ከማዋል ይልቅ መንገድ እና ህንጻ በመስራት ገንዘቦችን ወደ ድንጋይ እንዲለወጡ መደረጉ ያለው አስተዳደር የአገዛዝ ብልሹነት እና የመልካም አስተዳደር እጦት ያመለክታል:: ይህ ደሞ ኢኮኖሚያችን በተጭበረበረ ፖለቲካ ላይ እንደተገነባ ያመለክታል::

Sunday, March 2, 2014

ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ለችግሮቻችን የመፍትሄው ቁልፍ

የሃገራቸው ነገር ሲነሳ የሚከነክናቸው ወገኖቻችን ኢትዮጵያ ላለባት ችግር መፍት ሄው ምንድነው? እያሉ ኣጥብቀው ሲጠይቁ ይደመጣል። መፍትሄውም ብቻ ሳይሆን ችግሩ ማለትም እውነተኛው ችግር የት ላይ ነው ያለው? ብለውም ኣጥብቀው ሲደመሙ ይታያል። በዛሬዋ ኣጭር ጽህፌ በነዚህ መራራ ጥያቄዎች ዙሪያ ቁንጥል ኣሳብ ለማቀበል ኣስቢያለሁ።
በርግጥም ሁላችን  ኢትዮጵያዊያን የሆንን ችግሩ ምንድነው? ብለን ከጠየቅን ኣንዳንዶች ሊገረሙብን ይችላሉ። የችግሩ ተካፋይ ሆነን ሳለ፣ እየተጉላላን ያለነው እኛው ሆነን ሳለ፣  እንደገና መልሰን  የሃገራችን ችግር የት ጋር ነው? ብለን ስንጠይቅ የምናወጋቸው ሰዎች ምናልባትም ግራ ሊጋቡ ቢችሉ ኣይደንቅም። ነገር ግን መጠየቃችን ትክክል ነው።
በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ ትንቢተ ዳንዔል ላይ ኣንድ ናቡከደነጾር የተባለ ንጉስ ኣንድ ጊዜ ጠቢባንን  ጠርቶ የህልም ፍቺ ይጠይቃል። ጥበበኞቹም ህልሙን ንገረንና ፍቺውን እንነግርሃለን ሲሉት ህልሙ ጠፍቶብኛል ስለዚህ ህልሙንም ፍቺውንም ውለዱ ብሎ ጉድ እንዳፈላ እናነባለን።
እኛ ኢትዮጵያዊያን የዋናው ችግር ተጽእኖዎች የየእለት ኑሮኣችንን ሲያምሱት ብናይም ዋናውን የችግሩን ምንጭ መፈለጋችን ግን ኣሁንም ትክክል ነው።
የሃገራችንን ዋና ችግር የት ጋር ነው ብለን ኣጥብቀን ከጠየቅን በርግጥ የስርዓት ችግር ነው ወይ? ስርዓት በማጣታችን ነው ወይ የከፋ ችግር ላይ የወደቅነው? ብለን እንጠይቃለን።  በዚህ ኣገባብ ስርዓት ስንል የኣይዲዮሎጂውን ጉዳይ ሳይሆን ፍትህና ተጠያቂነት፣ ግልጽነትና የህዝብ የበላይነት የሚንሸራሸርበት ሲስተም ተዘርግቷል ወይ ብሎ የመጠየቅ ያህል ነው።  ስለ ስርዓት ስናነሳ ደግሞ በዋናነት የሚታየው ህገ- መንግስታዊ ስርዓቱ ነው። ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱ ምን ያህል ለዜጎች ይጨነቃል፣ ምን ያህል ለፍትህና ለነጻነት ለህዝቦች ጥቅም መንሸራሸሪያ ይህናል? ብለን እንድንጠይቅ ያደርገናል። በዚህ ረገድ በርግጥ መሻሻል ያለባቸው ጉዳዮች ቢኖሩም በዋናነት ግን ችግራችን የስርዓት ችግር ሆኖ ኣናይም። ለኣብነት የ1955ቱን ህገ መንግስት ስናይ የፕሬስ ነጻነትን ይሰጣል፣ እኩል የህግ ከለላ ይሰጣል፣ የመሰብሰብ፣ ሰልፍ የማድረግ መብትን ሁሉ ይሰጣል። የደርጉም ቢሆን ለዜጎች የሚጨነቅ ኣይነት ነው።

የዩናይትድ እስቴስ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በኢትዮያ ዉስጥ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳለ በዘንድሮዉ አመታዊ ሪፖርቱ ይፋ አደረገ

ዋሽንግተን ዲሲ፤ የካቲት 20/2006 (ቢቢኤን) ፦ የዩናይትድ እስቴስ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት (State Department) ባወጣዉ የዘንድሮ የሰዓዊ መብት ሪፖርት ላይ የኢትዮጵያ መንግስት ያከናዉናቸዋል ያለዉን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በመዘርዘር ሰፋ ባለ መልኩ አቅርቦታል።
ቀድም ሲል ኢትዮጵያ ዉስጥ በ2003 በተደረገዉ ምርጫ፤ በሟቹና በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስቴር መለስ ዜናዊ ይመራ የነበርዉ ኢ.ህ.አዴ.ግ ከ547 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ 545 መቀመጫዎች አሸንፏል መባሉን ሪፖርቱ እያመላከተ የምርጫ ጣቢያዎች በመንግስት ሐይላት ቁጥጥር ስር እንደነበሩና አለምአቀፍ ታዛቢዎች ስራቸዉን በተገቢዉ መልኩ እንዳያከናዉኑ ገደብ እንደነበረባቸዉ ይገፃል።John Forbes Kerry current United States Secretary of State.
በአገሪቱ ዉስጥ ባለዉ ከፍተኛ የመብት ረገጣ ሳቢያ ዜጎች የመሰብሰብ፣የመደራጀት፣የመናገር መብትን በገሃድ እንደሚነፈጉ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ያስደረግቸዉን ጥናቶች ተመርኩዞ ያብራራል። እነዚህን የዲሞክራሲ እሴቶችን ለመተግበር የሚሞክሩም ይታሰራሉ፣ይንገላታሉ፣ይዋከባሉ፣ዛቻ ይደርስባቸዋል፣ ክብራቸዉ ተነክቶ እንዲሸማቀቁምይደረጋሉ በማለት ሪፖርቱ ያትታል።እርዳታን የሚያስተባብሩ፣ እርዳታን ለጋሽ የሆኑ ድርጅቶች፣ ማህበራዊና ትርፍ አልባ የሆኑ ተቋማት (NGO) የግብረ-ሰናይ ተልእኮ አቸዉን እንዳይፈጽሙ የኢትዮጵያ መንግስት እንደሚከለክል፤ በሰዎች ላይ ህገ ወጥ የሆነ ግድያ እንደሚፈጽም፣ዜጎች ግርፋት-ድብደባ እንደሚደርስባቸዉ፣ ወጥ የሆኑ የማሰቃያ ተግባራት በመንግስት ሐይላት እንደሚፈጽምና በአገሪቱ እስርቤት የሚገኙ ታሳሪዎችን ህይወት ለአደጋ የሚያጋልጹ አሳቃቂ ተግባራትም እንዳሉም በሪፖርቱ ላይ ተገልጿል።

Saturday, March 1, 2014

“ምኒልክነትን የጠየቀው” የአድዋ ድል!





“ … ወታደር ባለመሆኔ የጦርነቱን ውሎ ማተት አያምርብኝም፡፡ ያም ሆኖ የአድዋ ድል ዛሬ ብርቅ በሆኑብን ሁለት እሴቶች ረድኤት የተገኘ ይመስለኛል፡፡ እኒህ ሁለት እሴቶች መተባበርና መደማመጥ ናቸው፡፡ ጣልያኖቹ በጊዜው ወደ ጦርነት ሲገቡ ተስፋቸውን የጣሉት በመድፍና በጠመንጃቸው ሳይሆን ኢትዮጵያውያን ዝነኛ በነበሩበት የውስጥ መቆራቆስ ላይ ነው፡፡ የትግራይ ቅልጥም ሲመታ ሸዋ ያነክሳል ብለው አላሰቡም፡፡ በርግጥም በክፍለ ሀገሮች ውስጥ የተለያዩ ሽኩቻዎች ነበሩ፡፡ እኒህን ሽኩቻዎች አስረስቶ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ ለአንድ አላማ ማሠለፍ ምኒልክነትን ይጠይቃል፡፡
“መደማመጥ ያልሁትን ላሳይ፡፡ አባ ዳኘው ከዛሬው የይስሙላ ፓርላማችን በተሻለ ሁኔታ ለልዩነቶች ቦታ የሚሰጥ ተንቀሳቃሽ ምክር ቤት በጦርነቱ ወቅት መፍጠር ችለዋል፡፡ ፀሐፌ ትእዛዝ ገብረሥላሴ በውጊያው ዋዜማ የነበረውን ሁኔታ እንዲህ ይገልፁታል
‘… አፄ ሚኒልክም በበነጋው ሰራዊቱን የቀኙን በቀኝ፣ የግራውን በግራ አሰልፈው ነጋሪትዋን እያስመቱ ወደሱ ተጓዙ፡፡ ኢጣሊያኖችም ዘበኛው ሲመጣ ባዩ ጊዜ ተመልሰው ወደ እርዳቸው ገብተው ተኙ፡፡

Demonstration in Support of the Co-pilo Hailemedhin Abera Tegegn in Osl...