ተቃውሞው ከፖሊስ ቁጥጥር ውጪ እየሆነ ነው። የሃረር መዘጋጃ በትን ህዝቡ ከቦ በድንጋይ እያናወጠው ነው።
ምንሊክ ሳልሳዊ ትላንትና ምሽት በሃረር ከተማ በተለምዶ መብራት ሃይል በሚባል የገበያ ቦታ ላይ የወያነ ተላላኪዎች በለኮሱት እሳት ለሁለተኛ ጊዘ የነጋደውን ንብረት ማውደሙን ተከትሎ ብሶት ያረገዝው ህዝቡ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞውን አሰምቷል።
ከሁለት አመት በፊት በዚሁ የገበያ ቦታ የወያን ተላላኪዎች በለኮሱት እሳት ከፍተኛ ንብረት መውደሙ የሚታወስ ሲሆን ትላንትና ምሽቱን በድጋሚ የእነዚሁ ተጎጂ ነጋደዎች የበፊት ቁስል ሳያገግም እና ንብረታቸውን ሰርተው ሳይተኩ በድጋሚ ቃጠሎው ተከስቷል።
የወያነው ተላላኪዎች እሳቱን እንዲለኩሱት ተደርጓል ሊባል የቻለበት ምክንያት ባለፉት ሶስት አመታት ነጋደዎቹ ከቦታው እንዲለቁ የተነገራቸው ሲሆን ከክልሉ ባላስልታናት ጋር በተነሳ አለመግባባት ባለስልጣናቱ እሳቱ እንዲለኮስ እና ንብረት እንዲወድም ያደረጉ መሆኑ ምንጮሹ ተናግረዋል።
በዛረው እለት በብሶት የተወጠረው የሃረር ህዝብ አደባባይ በመውጣት የወያነን መንግስት ያወገዘ ዚሆን ፖሊሶች ለተቃውሞ የወጣውን ህዝብ በማፈስ ወደ እስር በት የወሰዱ እና አከባቢውን በቶክስ በማናወጥ ከፍተኛ ሽብር ፈጥረዋል። እስካሁን የተጎዳ ሰው ይኑር አይኑር የወጡ መረጃዎች የሉም ።
No comments:
Post a Comment