ሸዋ በር እና አከባቢው ስጋት ነጋደው ጭንቀት እንዳጠላበት ነው።"...አዘናግቶ ሊያጋየን ነው::"
የእሳት ማጥፊያ አዘጋጁ እሳት ሊነሳ ይችላል የሚለውን ወያኔያዊ ሽብር በነጋዴዎች ዘንድ ጥርጣሬ አጭሯል::
የእሳት ማጥፊያ አዘጋጁ እሳት ሊነሳ ይችላል የሚለውን ወያኔያዊ ሽብር በነጋዴዎች ዘንድ ጥርጣሬ አጭሯል::
በሃረር ለረዥም ጊዜ ታፍኖ የቆየው ብሶት ባለፈው ሰሞን የተነሳውን የእሳት ቃጠሎ ተከትሎ ሕዝቡ አደባባይ እስከመውጣት ደርሶ ነበር::የወያኔው መንግስት ካለፉት አመታቶች ጀምሮ በተለያየ ጊዜ የሃረር ነጋዴዎችን መደብሮች ሲያቃጥል እንደ ዋናው ምክንያት ተደርጎ የተወሰደው አከባቢው ለልማት ስለሚፈለግ ከቦታው ተነሱ የሚለው የቅድመ ማስጠንቀቂያ ነጋዴዎቹ በምትኩ ቦታ ይሰጠን የሚሉትን አስታኮ የሚመጣ ቃጠሎ መሆኑ እና ከቃጠሎ በፊት ወደ መደብሮች መጋዘን የሚገቡ ነዳጅ የተሞሉ ጀሪካኖች ሕዝቡ ጣቶቹን በወያኔ ላይ እንዲጠቁም አድርጎታል::
ወያኔ የሃረር ህዝብ ላይ ያደረሰውን ሰቆቃ እና በደል ለመሸፈን ሰላማዊ ሰልፍ በመጥራት ነገሮችን በሙሉ አሸባሪ ብሎ በሚጠራቸው በመላከክ ህዝቡን ለመሸወድ ቢሞክርም አልተሳካለትም:: በየመንገዱ ቢያፍስ ቢያባርር ቢደበድብ ቢያስር ስብሰባ ቢጠራ ያልተሳካለት ወያኔ ከዚህ በመቀጠል ምን ሊያመጣ እንደሚችል እስካሁን የታወቀ ነገር የለም:: ምናልባት ይላሉ የሸዋ በር እና አከባቢው ነጋዴዎች ስጋታችንን እና ጭንቀታችን መደብሮቻችንን እንዳያቃጥልብን ነው ሲሉ ሃሳባቸውን አካፍለውናል::
በውሃ እጥረት እና በሌሎች የአገልግሎት አቅርቦት የምትታመሰው ሃረር በሕወሓት ሰራሾች ደባ እየተደረገባት ያለው የሰብኣዊ መብት ገፈፋ እና በደል እየጨመረ እንዲ እየቀነሰ አለመሆኑ የሰሞኑ ምስክር ሂደት ምስክር ነው::በዚህ ሰሞን ከክልሉ ምክር ቤት እስከ ቀበሌ ካድሬዎች ስብሰባ ከሕዝቡ እስከ ነጋዴው ቢሰበሰብም በሰብሳቢዎች እና በተሰብሳቢው ሕዝብ መካከል አለመተማመን እንደነገሰ ተበትኗል:: በትላንትናው እለት በሸዋ በር አከባቢ ጀጎል ግንቡን አስታኮ ያሉ ባለመደብሮች ስብሰባ ተጠርተው እንዲሁም የእህል እና የቅመማ ቅመም ነጋዴዎች በስብሰባው ተጋብዘው የተገኙ እና በተሰብሳቢው እና በሰብሳቢዎች ሕወሓት ሰራሽ የከተማው ባለስልታናት መካከል ስጋት እና ሽንቀት ወጥሮት የተካሄደ እንደነበር ነጋዴዎቹ ጠቁመዋል::
የሸዋ በር አከባቢ ነጋዴዎች ባለፈው በመብራት ሃይል እና በሲጃራ ተራ አከባቢ የደረሰውን የእሳት ቃጠሎ ከተመለከቱ በኋላ ነግ በኔን በማሰብ ንብረታቸውን ከአከባቢው በማሸሽ ስጋታቸውን በተግባር ለወያኔ ሰራሽ አካላቱ ያሳዩ ሲሆን ይህንን የተመለከተው መንግስታዊ አካል ነኝ ያለ ክፍል ነጋዴው እቃውን ከማውጣት ከመንግስት ጋር በጠረጰዛ ዙሪያ እንሰብሰብ እቃችሁን አታሽሹ ቢልም ነጋዴዎቹ አዘናግቶ ሊያጋየን ነው በሚል እቃቸውን ወደቤታቸው ጭነው ወስደዋል::
ንብረታችን ቤታችን እንዳለ ስብሰባ እንቀመጣለን ብለው የቆረጡት ነጋዴዎች በተጠሩበት ስብሰባ በመሄድ ዋና ዋና የተባሉ ነጥቦችን አንስተዋል::ከተነሱት ነጥቦች በእሁድ ቀን ማንም ሰው በገበያ ቦታዎች ውስጥ መገኘት እንደማይኖርበት;እሁድ ቀን ጠቅላላ መደብሮች ዝግ መሆን እንዳለባቸው:የዘበኞች ቁጥር መጨመር እንዳለበት:ወዛደሮች መታወቂያ እና ባጅ ሊኖረው እንደሚገባ እና መቆጣጠር አስፈላጊ መሆኑን:በንግዱ አከባቢ ዳር ዳሩን የመኪና መንገድ ላይ ያሉ በረንዳዎች እና መደቦች መጽዳት እንዳለበት በገበያ ውስጥ እሳት ማጥፊያዎች እና የውሃ ታንከሮች እንዲዘጋጁ ተወያይተውባቸዋል:; በዚህም መሰረት ነጋዴዎቹ የመተማመን መንፈስ ባይታይባቸውም ወኪሎቻቸውን መርጠው ስራውን ሊሰሩ የተስማሙ ሲሆን እስከዛሬ ያልታሰበ የእሳት ማጥፊያ እና የውሃ ታንከር አዘጋጁ እሳት ሊነሳ ይችላል የሚለውን ወያኔያዊ ሽብር በጥርጣሬ ተመልክተውታል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከታች በአስተያየት መስጫ ውስጥ የምትመለከቱት ምስል ከሶስት አመት በፊት ቦታው ለኢንቨስትመት ይፈለጋል ተነሱ የተባሉ ነጋዴዎች ምትክ ቦታ ይሰጠን እያሉ ሲከራከሩ የወያነ ሰራሽ የክልሉ ባለስልጣናት በድንገት የነጋዴዎችን መደብሮች ያቃተሉት ቦታ ሲሆን ይህ ቦታ ወደ መብራት ሃይል ሂደው ባለፈው ሱቆቻቸው የተቃተሉባቸው ነጋዴዎች ቦታ የነበረ ነው:: መንግስታዊ እሳት እየተከተለን ነው የሚሉ የመብራት ሃይል መደብር ባለቤቶች እና ተጎጂዎች ከ3 አመት በፊት የተቃጠለባቸው ቦታ ሕንጻ ለማሰራት ለአንድ ኢንቨስተር ተሰቶት ጥናት ተካሂዶ ቦታው ለኮንስትራክሽን አመቺ እንዳልሆነ እና አከባቢው ውሃ የሞላበት እና ሕንሳ ሊያሰራ የማይችል አፈሩም ለሕንሳ ግንባታ ተስማሚ እንዳልሆነ ይህ ቦታ ላይ ህንጻ ለማስገንባት ከፍተኛ ወጪ እና ዲዛይን የሚጠይቅ በመሆኑ ቦታው በዚህ ምክንያታዊ ጉዳዮች ለ3 አመት ያህል በምስሉ እንደምታዮት ታጥሮ የነበረ ሲሆን በአሁን ሰአት የተቃጠለው የሲጃራ ተራ እና የመብራት ሃይል ከቃጠሎ የተረፉ ቆርቆሮዎች እና ሌሎች ማቴሪያሎች መከመሪያ እየሆነ ነው::
No comments:
Post a Comment