ጥቂቶች የሚያደርጉት የፖለቲካ ዉሳኔ ዝምታ የመረጥነውን ቤታችንን አንኳኩቶ እኛን መንካቱ ፣ ማናጋቱ አይቀርም። ፖለቲካ የሚለዉ ቃል እንደ ጸያፍና አስፈሪ ቃል ነዉ በብዙ ኢትዮጵያዉያን ዘንድ የሚታየዉ። እንደዉም በተለምዶ ፖለቲካ ከኮረንቲ ጋር ይመሳሰላል። ነገር ግን፣ ይመስለናል እንጂ፣ ከፖለቲካ ነጻ የሆነ ሰዉ የለም። በአዎንታዊነት ሆነ በአሉታዊነት «ፖለቲካ አያገባንም» የሚሉ ዜጎችን ጨምሮ ፣ ምን ያህል የፖለቲካ ዉሳኔዎች፣ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ላይ እያደረሱ ያለዉን ተጽእኖ በስፋት ለማብራራት በርካታ ምሳሌዎችን መዘርዘር ይቻላል።
ከአራት ኪሎ የሚወሰኑት የፖለቲካ ዉሳኔዎች የማይነኩት ዜጋ አይኖርም። « ኦ ኦ ፖለቲካና ኮንረንቲ አንድ ናቸዉ. ! እኔ አያገባኝም » በሚል የፖለቲካ ፓርቲዎች ወይንም የሲቪክ ማህበራትን ተቀላቅለን ፖለቲካዊ አስተያየት ላለመስጠት ዝምታን ብንመርጥም፣ ሌሎች ጥቂቶች የሚያደርጉት የፖለቲካ ዉሳኔ፣ ወደድንም ጠላንም ቁጭ ብለን በተቀመጥንበት፣ ቤታችንን አንኳኩቶ እኛን መንካቱ ፣ ማናጋቱ አይቀርም።
ያለን አማራጭ ሶስት ነዉ።
የመጀመሪያዉ አማራጭ በፖለቲካዉ ምክንያት በቀጥታ፣ አሊያም ፖለቲካዉ በወለደዉ በኢኮኖዉ ችግር አገር ለቆ ተሰዶ መሄድ ነዉ። የቀናን ወደ አሜሪካና አዉሮፓ፣ ያልቀናን ደግሞ ወደ አረብ አገረ !!!!
ሁለተኛዉ አማራጭ ጥቂቶች በሚወስኑት የፖለቲካ ዉሳኔ ዉስጣችን እየደበነ፣ እየተቃጠለና እየተናደድን ማጉረምረምና ብሶታችንን ነጋ ጠባ ማዉራት ነዉ። ከጊዜ ወደ ጊዜ በንዴት ደም ብዛታችን እየጨመረ፣ ጸጉራችን እየሸበተ፣ ኑሮን ለመርሳት በየመሸታ ቤቱ ብርሌያችንን መጨበጥ
ሶስተኛዉ አማራጭ እጅግ ፈታኝ፣ ከራስ ጥቅም አልፎ ለሌላ ማሰብን የሚጠይቅ፣ በርግጥ ዘላቂነት ያለዉ መፍቴሄ እንዲመጣ የሚረዳ ፣ የሚያዋጣ አማራጭ ነዉ።
ዋናዉ የአገራችን ችግር የመልካም አስተዳደር፣ የእኩልነት፣ የፍትሕ እጦት፣ እንዲሁም የሙስና የዘረኝነት የጥላቻ መሳፋፋት ነዉ። በአጭሩ አባባል፣ የአገራችን ችግር የፖለቲካ ችግር ነዉ። የፖለቲካ ችግር የሚፈታዉ ደግሞ በፖለቲካ ትግል ነዉ። ይህን ተረድተን፣ የፖለቲካ ዉሳኔዎች አገርንና ሕዝብን በሚጥቀሙ መልኩ እንዲወሰኑ ለማድረግ የሰላማዊ የትጥቅ ብቻ የሆነዉን የፖለቲካ ትግል መቀላቀል የግድ አስፈላጊ ነዉ።
No comments:
Post a Comment