Search This Blog

Tuesday, April 15, 2014

ከ2007 ምርጫ በፊት ነባር የብአዴን ባለስልጣናትን እና ካድሬዎችን ማንጠባጠቡ ቀጥሏል::

ኦሕዴድ ከ5000 በላይ ካድሬዎችን በልማት እንቅፋትነት ሰበብ ሊያባርር ነው::
  
ሕወሓት በምርጫ 2007 ኢሕኣዴግ ላይ እንከን ይፈጥሩ ይሆናል ለማሸነፍም ይሁን ለማጭበርበር እንቅፋት ይሆናሉ ያላቸውን የብኣዴን ባለስልጣናትን እና ካድሬዎችን በማጣባጠብ የጀመረውን ጉዞ መቀጠሉ ሲታወቅ ኦሕዴድ በበኩሉ ከተለያዩ የዲያስፖራ የፖለቲካ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ጋር ግንኙነት አላቸው የበላይ የወረደ ትእዛዝ ሊፈጽሙ አልቻሉም ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ሰንሰለት ሰርተዋል የተባሉትን አባላቱን በልማት እንቅፋትነት ሰበብ ጸረ ልማት ታፔላ ተለጥፎላቸው ሊሰናበቱ መሆኑ ታውቋል::
What a shame on dictatorial government like weyanee having an election without the opposition parties!  Shame on You TPLF/weyane!   Ashenafi

የአገዛዝ እድሜውን ለማስረዘም የማይቧጥጠው ነገር ያሌለው ሕወሓት በኢሕኣዴግ ድርጅቶች መካከል የተስፋፋው የውስጥ ሰላም ማጣት እና አለመተማመን ስላሰጋው በመጀመሪያ በብኣዴን ውስጥ ያሉትን እና ያሰጋሉ የተባሉ ባለልጣናትን እና ካድሬዎች ማስወገድ ስለሆነ ይህንኑ ስራውን በወያኔ ሚዲያ ላይ ባሰማራቸው ሰዎች ላይ እንደሚጀምር ታውቋል:: ባለፈው ወር የኢዜአ ባለስልጣን የሆነውን የብኣዴኑን አቶ ታደሰን ከቦታው በማንሳት በፊት ወደነበረበት ቦታው አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ እንደሚመለስ ቢነገረውም እስካሁን ስራ ቦታው ላይ ካለመመደቡም በላይ በሱ ቦታ በእውቀት አልባነት የሚታወቀው አቶ መብራቱ ኪሮስ ከሕወሓት መቀመጡ ታውቋል:: እንዲሁም በተለያየ የስልጣን እርከን ላይ የነበሩ 22 የብኣዴን ሰዎች በእረፍ ስም እቤታቸው እንዲቆዩ የተደረጉ ሲሆን ካድሬዎችም እንዲሁ እረፍት እንዲወስዱ ፎርም እየተዘጋጀ መሆኑ ታውቋል::ከእረፍት ከመመለሳቸው በፊት ለእያንዳንዱ በግል አርፎ እንዲቀመጥ ማስጠንቀቂያ የሚሰጥ የደህነንት አካል መዘጋጀቱን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል::

ብኣዴንን አዳክሞ በአማርኛ ተናጋሪ ሌሎች ብሄሮች በተሻሻለ መልኩ ለመተካት በሕወሓት በኩል እየተሸረበ ያለው ሴራ በውስጡ ሰርገው በመግባት ድርጅቱ እንዲነቅዝ አድርገዋል ያላቸውን አባላቱን ሁሉ ነቅሰው በማውጣት በብልሃት መዋጥ የሚሉ ስልቶች በቀሪው ካድሬዎች ዘንድ ጥያቄዎችን አጭሯል:: 

No comments:

Post a Comment