በአገራችን ያሉ ባለሥልጣናት ስለሥልጣን ምንነት ትክክለኛ ዕውቀት ስለሌላቸው ይህ ነው የማይባል ኪሳራ እያደረሱ ይገኛሉ፡፡ የመንግሥት ባለሥልጣናት ሲሾሙ ልዩ ትኩረት የሚሰጡት በሥልጣን አማካይነት ስለሚገኘው ቤት፣ መኪና፣ ክብር፣ ገንዘብና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች ነው፡፡ ነገር ግን ምንሊክ ሳልሳዊ ከፈረሱ ጋሪው ቀደመ እንደሚሉት፣ በሥልጣን ውስጥ ካለው ኃላፊነት ይልቅ ሰለጥቅማ ጥቅሞቹ ማሰብ መዘዙ ኋላ ለራስም መትረፉ አይቀርም፡፡ሥልጣን አንድን ነገር ለመግዛት የሚያገለግል ኃይል ቢሆንም፣ ትክክለኛው ትርጓሜው ግን ተገቢ የሆነ ተፅዕኖን በማሳደር ነገሮችን በሥርዓት ለማስጓዝ የሚጠቅም ዘዴ ነው፡፡ ታዲያ ዛሬ የምናነሳው ጉዳይ በአገራችን በርካቶች ሥልጣንን የሚጠቀሙት ከምን አንፃር መሆኑን ለመፈተሽ ነው፡፡ በርካቶች የሥልጣንን ትክክለኛ ትርጓሜ ካለማወቅ የተነሳ በአገር እንዲሁም በሕዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ ነው፡፡ በመሆኑም ይህ ጉዳይ በጊዜው ሃይ ካልተባለ፣ ለባሰ ችግር ማጋለጡ አይቀሬ መሆኑ ሊታሰብበት ይገባል፡፡
weyanee official took power not only for the sake of their dictatorial government rather to build their wealth. Ashenafi |
የኢሕአዴግ ሰዎች ሥልጣንን የሚፈልጉት በሥልጣን ውስጥ ያሉ ጥቅሞችን ለማግኘት ካላቸው ክፉኛ መሻት ነው እንጂ፣ በእውነት ሥልጣንን በሚገባ ተረድተውት ነው ለማለት ያስቸግራል፡፡ ምንም እንኳን ሥልጣን ይዞ የሚያመጣቸው በርካታ ጥቅሞች ቢኖሩትም፣ ዋነኛ ዓላማው ከዚያ የዘለለ ነው፡፡ ሕዝብ የመንግሥት ባለሥልጣናትን መርጦ ሲሾም፣ የሾማቸው ባለሥልጣናት ባላቸው ዕውቀትና የሥራ ብቃት፣ መልካም አስተዳደርና ፍትሕን ያሰፍኑልኛል የሚል ብርቱ እምነት አለው፡፡ምንሊክ ሳልሳዊለዚህም ነው እንደ ኮንትራት የሆነውን ድምፅ ሰጥቶ በምላሹ ለሰው ልጆች አስፈላጊና መሠረታዊ የሆኑትን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ሥርዓቶች በተገቢው መንገድ እንዲመሩለት የሚጠብቀው፡፡ ስለዚህም አንድ ባለሥልጣን ሕዝቡ ከእሱ የሚጠብቀውን ማሟላት ምርጫው ሳይሆን ግዴታው መሆኑን ሊገነዘብ ግድ ይለዋል፡፡
አንድ ባለሥልጣን በሥልጣኑ ሊቆይ የሚችልበት ብቸኛው መንገድ የመረጠውን ሕዝብ ሲያገለግል መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ ማንም ባለሥልጣን ሕዝብን በኃይል መግዛት እንደማይችል በዓለማችን ያሉ ክስተቶች መቃኘት ብቻ ይበቃል፡፡ ስለዚህ የትኛውም ባለሥልጣን ስኬቱ የሚለካው ለሕዝቡ በሚሰጠው አገልግሎት እንጂ ባለው ኃይል አይደለም፡፡ ዛሬ ስለሥልጣን ስናወራ በሥልጣን ላይ ያለ ማንኛውንም ባለሥልጣንን ቢመለከትም፣ ነገር ግን ከሁሉ በበለጠ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ይመለከታል፡፡ ምክንያቱም እነሱ ባላቸው ሥልጣን በበርካቶች ላይ ተፅዕኖ ስለሚያሳድሩ ነው፡፡ ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ የመንግሥት ሥልጣንን እንደመያዙ መጠን ይህንን ጉዳይ በሚገባ ሊያጤነው ይገባል፡፡ ድርጅቱ የመንግሥት ባለሥልጣን አድርጐ የሚያቀርባቸው ግለሰቦች በሁሉም አቅጣጫ ሕዝብን የማገልገል ብቃት ያላቸው ሊሆኑ ይገባል፡፡
No comments:
Post a Comment