Search This Blog

Tuesday, February 17, 2015

“We Will Not Allow Tigrean Buildings and Factories on the Graves of Oromo Farmers.” – OFC Editorial Takes Decisive Position to #StopAbayTsehaye

ማስተር ፕላኑ፦ ለህዝቡ የሚያስፈልገውን የሚያውቀው ከህዝቡ አብራክ የወጣ፣ ከህዝቡ ጋር የኖረ፣ የተማረው የኦሮሞ ወጣት ምሁራን እንጂ [አቶ አባይ ጸሃዬ] አይደልም፡፡
በቅርቡ ሚሚ ስብሃቱ ማስተር ፕላኑን በሚመለከት፣ “የኦሮሚያ ፊንፊኔ ዙሪያ አርሶ አደሮች መሬትን እንደ ርስት መቁጠር ማቆም አለባቸው” ብላ ነበር፡፡
እኛ ደግሞ የምለው ለኦሮሞ አርሶ አደር ለዘመናት የኖሩበትና ወልደው የከበሩበት መሬት ስርታቸው ካልሆነ በአንድ ሌሊት የሚገነቡ የፊንፊኔ ፎቆች የማንም ርስት ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ከተደረደሩት ሰማይ ጠቀስ ፎቆች ይልቅ ለኛ ለኦሮሞ ልጆች የኦሮሞ አርሶ አደር ጎጆ ትልቅ ቁም ነገር አላት፡፡ እኛ የኦሮሞን መሬትን የምናየው እንደ የሚዳሰስ ሃብት ብቻ አይደልም፡፡ የማይዳሰስ ሃብት የኦሮሞ ባህልና አብዳር አብሮት አለ፡፡ ስለዚህ በኦሮሞ መሬት ላይ የሚደረግ ወረራ የማይዳሰሱ ባህላዊ ሃብቶቻችንም ላይ የተቃጡ ናቸው፡፡
እኛ የአርሶ አደር ልጆች ከዚሁ ጎጆ ወጥተን ነው ተምረን እዚህ የደረስነው፡፡ ስለዚህ የኦሮሞ ጎጆ ቤቶች ሲደፈሩ ዝም ብለን የምናይበት ሞራል የለንም፡፡
ልማት ካስፈለገ ቅድሚያ መልማት ያለበት፣ ሀብት ማፍራት ያለበት አርሶ አደሩ ነው፡፡ በአርሶ አደሮቻችን መቃብር ላይ ግን ፋብሪካና ፎቅ እንዲገነባ አንፈቅድም፡፡
የኦሮሞ አርሶ አደሮች እድል አልተሰጣቸውም እንጂ የተባለውንም ፎቅና ፋብሪካ መገንባት አያቅታቸውም፡፡ ምነው ሸገርን ፎቅ በፎቅ ያደረጉት እኮ አንዳንዶቹ ስማቸውን መጻፍ የማይችሉ አይደሉም እንዴ? እድል ስለተሰጣቸው ግን አደረጉት፡፡
እስቲ በሞቴ የአዲስ አበባ መስተዳድር ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ገብቶ በአርሶ አደሮች ማሳ ውስጥ ባለ 30 ሜትር ስፋት ያለውን ምን የመሰሉ አስፋልቶችን በአራቱም ማዕዘናት እየገነባ ያለው በክልሉ ጥያቄ ነው? ለአርሶ አደሮች ጥቅም ብሎ ነው? ገንዘብ ከተረፈው ለክልሉ መንግስት ለምን ፈሰስ አያደርግም? በመሰረቱ በፈደራል ስርዓቱ ህግ መሰረት አንድ ክልል ወይም ሌላ አካል የክልሉ መስተዳድር ሳያውቅ ወይም ሳይፈቅድ የትኛውም ሉዓለዊ ክልል ውስጥ ገብቶ ልማትም ሆነ ምንም መስራት አይችልም፡፡
ማስተር ፕላኑንም ሆነ የነበረውን የመሬት ወረራ ፊት አውራሪ ሆነ እየመረ ያለው የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ነው፡፡ እስቲ በማን ጥያቄ ነው በሉዓላዊ ክልል ውስጥ ገብቶ በአርሶ አደር ማሳ ውስጥ በመጋለብ መንገድ እየሰረ ያለው?
አርሶ አደሮች እኮ መጡብን እንጂ መጡልን ብሎ አያውቁም፡፡ደርግ የትግራይ አርሶ አደሮችን በታንክ ስያስበረግጋቸው ነበር፡፡
እነዚህ ደግሞ አሁን የኦሮሞ አርሶ አደሮችን በዶዘር እያስበረገጉ ነው፡፡ ታንክ ወደ ዶዘር ተቀየረ እንጂ ጦርነቱ ከአርሶ አደሮች ላይ አልቆመም፡፡ ልማት በአከባቢው ህዝብ ነው እንጂ እንደ ሸቀጥ ከሌላ ቦታ አይመጣም፡፡
ከዚህ ቀደም የማስተር ፕላኑ ተዋናይ የነበሩት አቶ ኩማ ደመክሳ፣ የፊንፊኔ ዙሪያ አርሶ አደር 600 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ ካለው የኦሮሞ አርሶ አደር ያነሰ ኑሮ እየኖረ እንደሆነ የኦህዴድን የ24 ዓመታት የውድቀት ጉዞ ነግረውን ነበር፡፡ አሁን የኦሮሞ አርሶ አደር ልጆች ተምሯል፣ ህዝቡ እንዴት እንደሚለማ፣አከባቢው እንዴት እንደሚለወጥ፣ ለህዝቡ ምን እንደሚያፈልግ ከማንም በላይ ጠንቅቀው ያውቃሉና የማንንም ጣልቃ ገቢነት አይፈልጉም፡፡ ለህዝቡ
የሚያፈልገውን የሚያውቀው ከህዝቡ አብራክ የወጣ፣ ከህዝቡ ጋር የኖረ፣ የተማረው የኦሮሞ ወጣት ምሁራን እንጂ [አቶ አባይ ጸሃዬ] አይደልም፡፡
source http://finfinnetribune.com/Gadaa/2015/02/we-will-not-allow-tigrean-buildings-and-factories-on-the-graves-of-oromo-farmers-ofc-editorial-takes-decisive-position-to-stopabaytsehaye/

No comments:

Post a Comment