Search This Blog

Thursday, February 8, 2024

ማምታታት እና በመሬት ላይ ያለውን ተጨባጭ እውነታ መካድ እያየን ያለነውን ማለቂያ የሌለው ጦርነት፣ ረሃብና ሰቆቃ ያስከተለ የኢትዮጵያ መንግስታት ባህል።

 ማምታታት እና በመሬት ላይ ያለውን ተጨባጭ እውነታ መካድ እያየን ያለነውን ማለቂያ የሌለው ጦርነት፣ ረሃብና ሰቆቃ ያስከተለ የኢትዮጵያ መንግስታት ባህል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር መግለጫ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል በአስመራ ተደርሶ የነበረውን ስምምነት ያፈረሰው ዶር ኣብይ ኣህመድ ዋና መሪ የሆኑበት የኢትዮጵያ መንግስት ነው።የኢቲዮጵያን መንግስት በመወከል ፕሬዘዳንት ለማ መገርሳና ዶር ወርቅነህ ገበየሁ እና በኦነግ መካከል ነሃሴ 2018 ዓም በኣስመራ ከስምምነት ተደረሰ። በዚህ ስምምነት መሰረት በኦሮሞ ህዝብ የነጻነት ትግል፣ በኦነግ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት የጦርነት ግንኙነት መሆኑን በጋራ ተስማምተዋል። ይህ የጦርነቱ ግንኙነት አብቅቶ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ በማካሄድ ላይ ከስምምነት ተደርሷል። ለዚህም ቀዳሚው የኢትዮጵያ መንግስት የደህንነት ሃይሎችን ጨምሮ የታጠቁ ሃይሎች ጉዳይ መሆን በሚገባቸው ላይ በስፋት ተነጋግረው ስምምነት ላይ ተደርሷል ።
የኢትዮጵያ መንግስት የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት እና ቡድን ሳያደሉ የሀገሪቱን ህገ መንግስት እና ህግጋት በማክበር ሁሉንም ብእኩልነት እንዲያገለግሉ፣ በኦነግ ስር ተደራጅቶ የሚገኘው ሰራዊት (የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት) በተመለከተ ኦነግ ወደ ሃገር ቤት ሲገባ አብረው የጋራ ኮሚቴ (Joint Committee) ኣቋቁመው ዓለም አቀፍ ህጎችን እና ደንቦችን በተከተለ ሁኔታ የታጠቁ ሃይሎች የሚዋሀዱበትን ስርዓት ተከትሎ እንዲፈጽም፣ ኦነግም ሆነ ሌሎች ፖለቲካ ፓርቲዎች በሃገሪቷ ውስጥ በሰላማዊ መንገድ በመንቀሳቀስ ያመኑበትን የፖለቲካ ፕሮግራም ያለኣንዳች እገዳና እንቅፋት የሚያካሄዱበት ላይ ቃል ተግብቶ ከስስምምነት ላይ ተደረሰ።
ከዚሁ ጋር የሚተሳሰረው እ.ኤ.አ. በ1992ዓም ኦነግን በሴራ ከፖለቲካው መድረክ ተገፍቶ ሲወጣ በመላው ሃገሪቱ የነበሩትና የተዘጉ ፅህፈት ቤቶቹ ጉላሌ የሚገኘውን የኦነግ ዋና መሥሪያ ቤትን ጨምሮ እንዲመለሱለት፣ እንዲሁም በ1996ዓም የተዘጋው የኦሮሞ መረዳጃ ማህበር ጽ/ቤቶችና የተዘረፉት ንብረቶቹ እንዲመለሱ በሚል ላይ ተስማሙ። እነዚህ እና ሌሎች ከእነዚህ ጋር በተያያዙ ሁሉም ነጥቦች ስምምነት ላይ ተደረሰ። ኦነግ ከገባ በኋላ የሆነው እና ኦነግ ላይ የተፈጸመውን ክህደት መላው ህዝብ ሙሉውን መረጃ እንዳለው እናምናለን። በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ላይ ኦነግ ከአስመራ ተነስቶ ሃገር ቤት ከመግባቱ በፊት የማያቋርጥ ውጊያ መካሄድ ቀጠለ።
የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትን በሁለት ሳምንታት ውስጥ እናጸዳለን በሚል በጄኔራል ብርሃኑ ጁላ እና በፕሬዝዳንት ለማ መገርሳ የተሰጠውን አዋጅ ሁሉም ሰው ያስታውሰዋል። ይህንን ለማረም እና በስምምነታችን መስረት ለመቋጨት በድርጅታችን እና በአባ ገዳዎች በኩል የተደረገው ሙከራም ሰፊ ቢሆንም እንዴት ኣንደከሸፉ ሁሉም ያስታውሳል ብለን እናምናለን። ኦነግ እንዳይንቀሳቀስ ተከለከለ። በሃግሪቱ በበርካታ ቦታዎች የከፈታቸው ጽህፈት ቤቶች በጦር ሃይል እና በፖሊስ ተዘግተው፤ ንብረት ተዘረፈ። ጉለሌ ከሚገኘው ዋናው መስሪያ ቤት ከፍተኛ የድርጅቱ አመራሮችን ጨምሮ ሁሉም በፊንፊኔ ፖሊስ ሃይል እንዲወጡ ተደርገው እስከዛሬም ድረስ ማንም ሰው እንዳይገባ ፖሊስ ጽ/ቤቱ ፊት ለፊት ተቀምጦ ይጠብቃል።
የኦነግ አመራሮች እና የፖለቲካ ኦፊሰሮችና ባለስልጣናት ከመላው ኦሮሚያ ያልታሰሩበት የሉም። ይህን ጉዳይ እና ያለውን እውነታ በምርጫ ቦርድ የተቋቋመው ኮሚቴ ጉዳዩን መርምሮ ሪፖርቱን ለፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እና ለሀገሪቱ ፓርላማ የዲሞክራሲ ኮሚቴ ሪፖርት አስገብቷል።
የኦነግ ቢሮዎች አሁንም ዝግ ሲሆኑ ንብረቱም እንደተዘረፈ ነው። መላው ህዝብ እንዲሚያውቀው የኦነግ ኣመራሮች ከአራት አመታት በላይ በእስር ቤት ያለፍርድ ቤት እውቅና እየተሰቃዩ ናቸው። የፖለቲካው መድረክ ለሁሉም እንዲጠብ ተደርጎ ተንቀሳቅሶ መስራት ስለማይቻል ችግር ውስጥ ተገብቷል። በመላው ሃገሪቷ ውስጥ የተሰማሩት የብልጽግና ጦር፥ ፓርቲ ፖሊስ፣ እና ሚሊሻ ሃይሎች ዜጎችን በፈለጉበት ቦታ መግደል፣ መደብደብ፣ መዝረፍ እና ቤቶቻቸው ማቃጠልን የእለት ተእለት ስራቸው አድርገውታል።
ይህንን እውነታ በመካድ ነው እንግዲህ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር አቢይ አህመድ ትናንት ጥር 06 ቀን 2024 ዓም ለሃገሪቷ ፓርላማ “ኦነግ ስራውን በሰላማዊ መንገድ እያካሄደ ነው፤ የፈረሰ ስምምነት የለም ወዘተ.” በማለት የተናገሩት። ከፓርቲው እራሳቸውን ያገለሉና ብልጽግና የሾማውቸው ግለሰቦች ካልሆኑ በስተቀር፣ ከብልጽግና መንግስት ጋር ሥልጣን ተጋርተው በስራ ላይ ያሉ የኦነግ ኣመራሮች የሉም።
የኢትዮጵያ መንግስታት የፖለቲካ ማምታታት ውጤት ኢትዮጵያን ለጦርነት፣ ረሃብ፣ ድህነት፣ መፈናቀል እና ውድመት የዳረገ እንደሆነ የአገሪቱ እና የመሪዎቿ ታሪክ ይገልጻል። ኣሁንም ይኸው መቀጠሉ ደግሞ የኣሁኑን ትውልድ ያጋጠመ የከፋ አሳዛኝ እውነታ ነው። ከዚህ እንዴት እንወጣለን ይሚለው ከዚህ ትውልድ ፊት የታጋረጠ ፈተና መሆኑን ሁሉም ተረድቶ መቀበል አለበት።
ድል ​​ለሰፊው ህዝብ!
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር
የካቲት 7 ቀን 2024 ዓም
ፊንፊኔ

No comments:

Post a Comment