Search This Blog

Tuesday, May 6, 2014

ሃሮማያ ድጋሚ ሁለት ያልፈነዱ ፈንጂዎች ተገኙ

ሃሮማይ ዩንቨርስቲ የሃረር ካምፓስ በፖሊሶች ድንገት ተወሮ ነበር።ተማሪዎች ታርደው ተገኝተዋል ማን አረዳቸው?
የሃረር ነጋዴዎች አዲስ እና ወያኔ የለቀቀው ብሶት ተከስቷል ይላሉ። ሓረር ውሃና መብራት ናፍቃለች።
ምንሊክ ሳልሳዊ ፦ ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ሰበብ የፈነዳው የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞ እስከዛሪ ድረስ ውጥረቱ እንደቀጠለ መሆኑ ይታወቃል ፡፤ የተቃውሞው ድባብ አሁንም አጥልቶባቸው ካሉ የምስራቅ ኢትዮጵያ ዩንቨርስቲዎች የሃሮማያ የድሬዳዋ እና የሃሮማያ ሃረር ካምፓስ ተጠቃሽ ናቸው።
በሃሮማያ ዩንቨርስቲ ባለፈው ሳምንት በኳስ ሜዳ ተሰብስበው በነበሩ ተማሪዎች ላይ በተወረወረ ቦምብ ተማሪዎች የሞቱ ሲሆን በርካቶች ቆስለው ሕክምና እየተከታተሉ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ ። ከዛም በተከታይ በዩንቨርስቲው ውስጥ ብሄርን መሰረት ያደረጉ ግጭቶች ተከስተው ተማሪዎች መገደላቸውን እና መቁሰላቸውን በአከባቢው እንዳይንቀሳቀሱ እየተደረገ መሆኑን ዘገባዎች ጠቁመዋል።
በትላንትናው እለት እና ዛሬ የደረሱን መረጃዎች እንደሚያሳዩት በሃሮማያ ዩንቨርስቲ ሃረር ካምፓስ ተቃውሞ ያሰሙ ተማሪዎች በፌዴራል ተከበው እንደተደበደቡ እና አሁንም ግቢው በፖሊስ ተወሮ እንደሚገኝ የሃረር ነዋሪዎች ገልጸዋል። የተወሰኑ ተማሪዎች ለሕይወታቸው በመፍራት ግቢውን በመልቀቅ በውጪ ቤት ተከራይተው መኖር መጀመራቸውን እንዲሁም በየቤተክርስቲያኑ ተጠልለው እንደሚገኙ ምንጮቹ አክለው ገልጸዋል።
በትላንትናው እለት ዋናው ግቢ ሃሮማያ ዩንቨርስቲ ተማሪዎችን በጠዋት ስብሰባ የጠራው የወያኒው መንግስት ስብሰባው ላይ ጠንከር ያሉ ጥያቄዎች ያቀረቡትን እና እየተካሄደ ያለውን ፍጅት የተቃወሙትን እንዲሁም በመማር ማስተማሩ ሂደት ላይ ወያኔ እየፈጠረ ያለውን ችግር የተናገሩትን እንዲሁም ተቃውሞ ያሰሙ ተማሪዎችን ያላወገዙትን በግልጽ ከስብሰባው እያወጡ የክልሉ ፖሊሶች እንደደበደቧቸው የአይን እማኞች ተናግረዋል።
ያለፈው ያቀነባበረው ፍንዳታ አልበቃ ያለው ወያኔ በድጋሚ ለማፈንዳት ያቀዳቸው ፈንጂዎች ከሽፈው መያዛቸውን ከቦታው የተገኙ መረጃዎች ሲያሳዩ ፈንጂውን ይዘዋል ተብለው የተገኙ ተማሪዎች የኦሮሞ ተወላጆች ያልሆኑና ከመሃል ሃገር የሄዱ ተማሪዎች እንደሆኑ ምንጮቹ ሲያረጋግጡ የተያዙት ሁለት አባላት በመሃል ሃገር የሕወሓት አባል ሆነው የተመዘገቡበት መታወቂያ የተገኘባቸው ሲሆን አማርኛ ትግሪኛ እና ኦሮምኛ እንደሚናገሩ ታውቋል።
እነዚሁ ተማሪዎች ከነፈጂያቸው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ወዲያው ወደ አዲስ አበባ ለምርመራ ተብሎ የተላኩ ሲሆን ሲንቀሳቀሱበት በነበረው አከባቢ ሁለት ተማሪዎች ታርደው መገኘታቸውን የክልሉ ፖሊስ አረጋግጧል። ፖሊስም ይሁን ተማሪውች ታርደው የተጣሉ ተማሪዎች ፈንጂ ይዘው ከተገኙት ጋር ግንኙነት ሊኖረው ይችላል በሚል ጥርጣሪያቸውን ቢገልጹም የአከባቢው ፖሊሶች ወደ አዲስ አበባ የላኳቸውን ተማሪዎች መልሰው ለማግነት አለመቻላቸው ሲታወቅ በኳስ ሜዳ የፈነዳው እና ለዜጎች ሞት እን ቁስለት ምክንያት የሆነው ቦምብ ያፈነዳው ማን እንደሆነ እስካሁንም ምርመራው አለመጀመሩ ታውቋል።
የሃረር ነጋዴዎች አዲስ እና ወያኔ የለቀቀው ብሶት ተከስቷል ይላሉ። ሓረር ውሃና መብራት ናፍቃለች።
=================================================
በሸዋ በር አከባቢ እና በመብራት ሃይል አከባቢ ባለፈው ሱቃቸው የተቃጠለባቸው ነጋዴዎች ለ እያንዳንዳቸው በቆርቆሮ የተከፋፈለ እና አንድ ሜትር በአንድ ተኩል የሆነች መደብ የተሰጣቸው ሲሆን ቀሪው መሬት ክልሉ ለኢንቨስተሮች በሚል ሰበብ በሙስና ለባለስልጣናት የግል ጥቅም ለማዋል በመራወጥ ላይ ነው ሲሉ ነጋዴዎች አማረዋል። እንደበፊቱ ያለን የንግድ ሱቅ እንዲመለስልን እና እንድንገነባ ይፈቀድለን የሚሉት ነጋዴዎች ከአንድ አልጋ የምታንስ የበሬ ግንባር በምታክል መደብ ላይ ምን ዘርግተን ልንሸጥ ነው ሲሉ ብሶታቸውን አሰምተዋል።
መጀመርያ ከነበሩት እና ከተቃጠሉት ሱቆች በተጨማሪ የተሰሩ 150 ሰፋፊ ሱቆች ለባለስጣናት ቤተሰቦች እና ዘመዶች እንዲሁም ለአዳዲስ የመሃል ሃገር የመጡ ሰዎች የተሰጡ ሲሆን ቀሪ መሬቶች ለኢንቨስተር በሚል ሰበብ ዘረፋ ሊካሄድባቸው መሆኑን ምንጮቹ ገልጸዋል። ለነጋዴው ወያኔ 50 ኪሎ ስንዴ እና ስኳር ከመስጠቱ ውጪ ምንም እርዳታ ያላደረገ ሲሆን የክልሉ ፕሬዝዳንት በነጋዴው ጉዳይ ላይ ምንም አይነት ነገር አልፈርምም በማለቱ ነጋዴው ከነቤተሰቡ እየተሰቃየ ይገኛል።

ሃረር ውሃና መብራት ናፍቋታል የሚሉን ነዋሪዎች ብሶታችንን አደባባይ ይዘን የወጣን ቀን ክልሉ ያበቃለታል ሲሉ እየዛቱ ነው። ባለፉት ወራቶች በክልሉ የውሃና የመብራት እጦት ከመስፋፋቱም በላይ ከነበረበት በ እጥፍ ብሶ እየታየ መሆኑን ነዋሪዎቹ ጥርሳቸውን ነክሰው ይናገራሉ። አዲስ አበባ ባቡር እና መንገድ እየዘረጋን ነው የሚል ልማታዊ ሰበብ ይሰጣል እዚህ ሃረር ደሞ የምን ልማታዊ ሰበብ ሊሰጠን ነው እንዲህ በመብራት እና ውሃ እየበደሉን ያለው ሲሉ ምሬታቸውን ያሰማሉ፡፤ ለወደፊት ለሚመጣው ልማትታለኝ በሰማይ እንድንለማመድ እያበረታቱን ከሆነ ይነገርን ሲል ህዝቡ አቤት ብሏል። በቀን ውስጥ ለ 2 ወይንም 3 ሰአታት ያህል ባቻ በጸሎት የምትቆየው መብርራ አሁን ጭራሽ እየጠፋሽ ሲሆን ውሃ በሃረር ከታየች ሳምንት አልፏታል ሲሉ ነዋሪዎቹ ይገልጻሉ።
በመልካም አስተዳደር እጦት የምትሰቃየው ሃረር ከተማ እንዲሁም በዘረኝነት በፍትህ እጦት እና በመሰረታዊ አገልግሎት በአድሎዋዊ አሰራር በስፋት የተንሰራፋበት ባለስልጣናት ከነዘመዶቻቸው በዘረፋ እና ሙስና የተጨማለቁበት መሆኑን ህዝቡ ይናገራል። ይህንን አምባገነን መንግስት በጋራ በአንድነት ለመገርሰስ ብዙ መስራት ይጠበቅብናል

No comments:

Post a Comment