Search This Blog

Tuesday, April 1, 2014

ማህበረ ቅዱሳን ላይ የፖለቲካ ብትር መምዘዝ ለምን አስፈለገ?

በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስር በሚገኘው እና የተለያዩ አርኪ እና ስኬታማ ጉዞዎችን በማድረግ ታላቅ ስራ በሰራው በማህበረ ቅዱሳን ላይ ወያኔ የፖለቲካ ብትሩን በመምዘዝ ሊያወድመው መሆኑን ይህንን ሰሞን አበይት ከተባሉ ጉዳዮች አንዱ ሲሆን ይህንን ተከትሎ የወያኔ ካድሬዎች እና በሃይማኖቱ ውስጥ የተሰገሰጉ ቡችሎች ጸረ-ማህበረ ቅዱሳን ዘመቻቸውን ተያይዘውታል።

ለዘመናት በሰላማዊነታቸው ወደር ያልተገኘላቸውን የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ወኪሎች ባልተገኙበት ባልዋሉበት ባላሰቡት ባልደገሱት በአክራሪነት እና በአሸባሪነት በመፈረጅ እንዲሁም ህዝበ ሙስሊሙን በመግደል እና በማሰር በማንገላታት ላይ የተሰማራው ወያኔ የሽብርተኝነት ፍረጃ ካርታውን ወደ ተዋህዶ እምነት በማዞር ማህበረ ቅዱሳንን አሸባሪ በማለት ለስልጣኑ የሚያሰጉ መሆናቸውን በመደስኮር ላይ ይገኛል።

ለተነሳለት የከፋፍለህ ግዛ እና የጎሳ ፖለቲካ ፖሊሲ አልመች ብሎ የተገኘውን ሁሉ አሸባሪ አክራሪ በማለት ማህበረ ቅዱሳንንም ባልዋለበት የማክረር እና የማሸበር ድርጊት በመወንጀል ተግባር ላይ መሰማራቱ የጀመረውን ኢትዮጵያን ከፋፍሎ በጎሳ ቡድንተኝነት እያናከሱ በስልጣን ለመኖር ያሴረውን ሴራ እንደሚያከሽፍበት በከባዱ እንቅፋት ሆኖ ስላገኘው ነው።

የኢትዮጵያ ሙስሊሞችም ይሁኑ የተዋሕዶ አማኞች መሰረታቸውን ጎሳ ሳይሆን ኢትዮጵያ የሚል እደምታ መኖሩ እና በብሄር የተከፋፈለ አካሄድ አለመከተላቸው የወያኔ ስጋት ሆኖበታል። በመስኪዶችም ሆነ በቤተክርስቲያን ደረጃ ቀበሌያዊ የጎሳ ጥየቃ እና ምደባ አለመኖሩ ያንገበገበው ወያኔ የኢትዮጵያ አንድነትን የሚሰብኩ እና በህዝቦች መካከል ፍቅርን የሚያሰርጹ ሆኖ ስላሰበው ብቻ መፍረስ መደርመስ መሪዎቹን መታሰር እንዳለባቸው ግብሩ ይመሰክራል።

በሙስሊምም ይሁን በተዋህዶ አማኞች ቀኖና ውስጥ ቀለም ዘር ጎሳ የመለያየት ትምህርት አለመኖሩ የሃይማኖቱን ምሁራን የአንድነት የፍቅር እና የሰላም ተምሳሌት እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። ይህ ደሞ ለወያኔ የከፋፍለህ ግዛ የጎሳ ፖለቲካ የማይመቸው ስለሆነ ማህበረ ቅዱሳንን በ97 ምርጫ ወቅት ለወያኔ መሸነፍ አንዱ ተጠያቂ አድርጎ በሰነዱ ወንጅሎታል። ስለዚህ አምነቶቹን እና አማኞቹን ለመከፋፈል የሚችለው እንደ ማህበረ ቅዱሳን ያሉትን እና እንደ ሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን በአክራሪነት በአሸባሪነት በመወንጀል ማፈራረስ ከዚያም ማሰር ማንገላታት ስራዬ ብሎ ታያይዞታል።

ያሰማራቸውም ቡችሎቹ ለመጪው ምርጫ ስጋት ያሳድራል ስለተባሉ ብቻ በጭፍን ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ በጅምላ የሚያካሂዱትን ጥላቻ በማህበረ ቅዱሳንም ላይ ጀምረውታል። የኢትዮጵያን አንድነት በጠበቀ መልኩ ለመጪው ትውልድ ያስተላልፋሉ ታሪኬን ያበላሹብኛል ያላቸውን ሁሉ እየገዘገዘ መጣል የለመደው ወያነ በማህበረ ቅዱሳንም ላይ የጀመረው ግሬደራዊ የጥላቻ ዝቆሽ ከዚሁ ጋር የተያያዘ ነው።
እንደ ኢትዮጵያውያኑ ሙስሊሞች እና የተዋህዶ አማኞች ሁሉ ነገ ባለተራ የሆኑት የፕሮቴስታት አማኞችም ከወዲሁ ስጋት አድሮባቸዋል፡፤ በጎሳ ስም የተከፋፈለ የበተክርስቲያን እና የመስኪድ ስያሜ የተመኘው ወያኔ ይህንን ለማሳካት ደፋ ቀና በማለት ላይ ስለሆነ ኢትዮጵያውይንን በጋራ ሃይማኖት ሳንለይ ይህንን የእምነት ጸር የሆነ የሰይጣን ተልእኮ በመያዝ ሃይማኖቶችን ሊያደፈርስ የሚፈልገውን ሕወሓት/ኢሕአዴግ የተሰኘውን የሽብር እና በፖለቲካዊ አክራሪነት የአንድነት የፍቅር የሰላም ፀር የሆነውን ቡድን ወደ ከርሰ ማቃብሩ ልንከተው ይገባል ። 

 ድል ለኢትዮጵያውያን!!!

No comments:

Post a Comment