Search This Blog

Friday, October 17, 2014

የአሜሪካ መንግስት የሽብር መረጃ የሚጠቁመው ሕወሓትን ወይንስ አልሸባብን ?

- ሕወሓት አልሸባብን ሽፋን አድርጎ ፍንዳታ ለመፈጸም እንዳቀደ መረጃዎች ያሳያሉ።
- አሜሪካ ብሄራዊ ጥቅሟን ላለማጣት ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ስራዎች እየሰራች ነው።
- አልሸባብ ላይ ማሳበብ ለምን አስፈለገ ?
በምስራቅ አፍሪካ ይንቀሳቀሳሉ ከሚባሉት የአሸባሪ ቡድኖች ስሙ በዋነኛነት የሚጠቀሰው አልሸባብ በቡድን ደረጃ የታጠቀ ሲሆ በመንግስታዊ ሽብርተኝነት ስሙ ተመዝግቦ የሚገኘው የሕወሓት ቡድንም ሌላኛው ነው። እንዲሁም ሻእቢያ በግርግር መሃል ለመሹለክለክ ቢፈልግም ሊቀናችው ካልቻሉ ግን በምክር እና ጥቆማ እንደ አልሸባብ ካሉ የሽብር ድርጅቶች ጀርባ ሲንቀሳቀስ ከመታየቱም አልፎ አሰልጣኞችን እስከ ሶማሊያ መላክ የደረሰ ድርጅት ነው።
የአሜሪካን መንግስት በምስራቅ አፍሪካ ስላሉ ድርጅቶች በቂ መረጃ ያለው ሲሆን ዋናው አትኩሮት አልሸባብን አድርጎ ይንቀሳቀስ እንጂ በአልሸባብ ጀርባ እና ሽፋን የሽብር ወንጀል የሚፈጽሙ ድርጅቶች በተለይ በኢትዮጵያ ሕወሓት እና ሻእቢያ መሆናቸውን በቂ መረጃ አለው። የአሜሪካ መንግስት ይህን ሰሞን ዜጎቹ በኢትዮጵያ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ በተለይ ቦሌ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ አልሸባብ ጥቃት ሊያደርስ ይችላል የሚል ስጋት እንዳለው የሚገልጽ ዲፕሎማሲያዊ መረጃ ለዜጎቹ መበተኑ እሙን ነው።
በዋሽንግተን ዲሲ የወያኔ ኤምባሲ ውስጥ የተከሰተው ወያኔን ያዋረደ እና እንደ መንግስት ያሳፈረ ድርጊት ከተከሰተ እና የጦር መሳሪያ ስም ለመጥራት በሚፈራበት ከተማ ዋሽንግተን ላይ የቶክስ እሩምታ የለቀቀው የሕወሓት የሽብር ሰው ተይዞ ወደ ኢትዮጵያ መሰናበቱን አሊያም መጠረዙን አስታኮ የዲፕሎማሲ ሽንፈት የደረሰበት ወያኔ በአሜሪካ ድርጊት ካለመደሰቱን በላይ በተኳሹ ላይ ክስ እንደሚመሰረት ሲያውቅ እርር ድብን በማለቱ በአሜሪካ ጥቅሞች አሊያም ዜጎች ላይ አልሸባብን ሽፋን አድርጎ በቀል ሊወስድ ይችላል የሚል እደምታ ከመጠርጠሩም ሌላ አሜሪካ ስጋቷን አስታካ ጥንቃቄ እንዲወሰድ መረጃዎችን በትናለች።
ሕወሓት የበቀል ድርጅት እንደሆነ የምታውቀው አሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ መንገዶችን ተጠቅማ በሕወሓት የሚመጣውን የበቀል ብትር ለማስቀረት ስትል የአልሸባብን ስም ጠርታ መንቃቷን ተናግራለች።ሕወሓት በምስራቅ አፍሪካ እና መካከለኛ ምስራቅ ላይ ክፍተኛ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ወንጀሎችን እንደሚሰራ አሜሪካ የተጣራ መረጃ አላት።ከምስራቅ አፍሪካ ተንቀሳቅሶ እስከ ኢራቅ ኩርድ ድረስ ህገወጥ የመሳሪያ የሰዎች እንዲሁም የሰዎች አከላት ዝውውር በሕወሓት እንደሚፈጸም አሜሪካ በቂ መረጃዎች እንዲሁም አሸባሪ ከሚባሉ እንደ አልቃይዳ አልሸባብ እና ኬኬኬ የመሳሰሉ ድርጅቶች ጋር ሕገወጥ ግንኙነት እንዳለው አስረግጣ ታውቃለች።
የአሜሪካ መንግስት አንድ ጠንካራ ተቃዋሚ ኢትዮጵያ ውስጥ ማምጣት እንዳልቻለ እና ህዝብን አቅፎ የሚያሳምን መሪ አለመፈጠሩ የሕወሓትን የሃይል ሚዛን እንዳሳደገው በዲፕሎማቶቿ አማካኝነት በተደጋጋሚ ተናግራለች።የፖለቲካ ተንታኞችን ይህንን አስረግጠው ተንፍሰውታል። የሕወሓት የሃይል ሚዛን ለመጣል የሚችል ታማኝ ፖለቲከኛ በምስራቅ አፍሪካ ኢትዮጵያ ውስጥ መፍጠር አለመቻሉ የሽብር መንግስት የመስፋፋት አዝማሚያው እያደገ እንደሄደ ፖለቲከኞች አፋቸውን ሞልተው እየተናገሩ ነው።
አሜሪካ በምስራቅ አፍሪካ ያላትን ብሄራዊ ጥቅም ላለማበላሸት እንዲሁም አስተማማኝ የሆነ ሃይል ለብሄራዊ ጥቅሟ በምስራቅ አፍሪካ አለመኖሩ ሕወሓት ላይ ሙጭጭ እንድትል አድርጓታል። አሜሪካ በሕወሓት ላይ ልታደራጅ ያቀደችው በኢትዮጵያውያን የሚመራ አልሸባብ እና ቦኮ ሃራማ መሰል የአሸባሪ ድርጅትም ከኢትዮጵያውያን መልካም ትብብር በማጣቷ መደናቀፉ በቅርብ ርቀት ላይ በአሜሪካ ውጪ ጉዳይ ቢሮ የተደረጉ ውይይቶች ምስክሮች ናቸው።

No comments:

Post a Comment