Search This Blog

Monday, November 17, 2014

በኬንያ ስደተኞችን የማፈኑን ስራ የሚያስቀጥል የደህንነት ቡድን ናይሮቢ ገብቷል:

- በኬንያ ሰላም እያለች ራሷን የምታስተዋውቀው ገዳይ ሴት ተልእኮዋን አልተሳካላትም::
- በኬንያ የሚገኙ ስደተኞች በተጠንቀቅ እንዲቆሙ መረጃውን ያስተላልፉ::
በኬንያ የሚገኙ ስደተኞችን ለማፈን የሚረዳ የደህንነት ግብረሃይል ወደ ናይሮቢ መጓዙን ከኤምባሲው የደህንነት አታቼ ቅርብ የሆኑ ዲፕሎማቶች ያደረሱኝ መረጃ ይጠቁማል::አዲስ የተላከው ሃይል በናይሮቢ የከተመውን CID ብሎ ራሱን የሚጠራው የወያኔ የስለላ መዋቅር ጋር በመቀናጀት አስፈላጊ ናቸው የተባሉ ሰዎችን በማፈን ወደ ኢትዮጵያ በሰአታት ውስጥ ለመላክ የሚያስችለውን ስራዎች እንደሚሰራ ታውቋል::
የCID አባላት ታፍነው ይወሰዳሉ የተባሉትን አዋዋል ተከታትለው የጨረሱ ሲሆን እንዲሁም በቡድን የሚገናኙ ኢትዮጵያውያንን የሚገናኙበትን ጊዜ እና አከባቢ ጠብቀው ለማፈን ክትትል ላይ መሆናቸው ታውቋል:: ከኤምባሲው የደህንነት አታቼ ቢሮ የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው አዳዲስ ስደተኞች አንድ ላይ ሲሆኑ ለማፈስ ዝግጅት ጨርሰዋል ስልካቸውን እንዲቀይሩ እና ከሚያውኩት ሰው ውጪ ከማንም ጋር ናይሮቢ ውስጥ እንዳይደዋወሉ ሲል እየነጠሉ እንዳይወስዷቸው ሌሎቹ ያመልጡናል ብለው ስላሰቡ ለስራው የሚሆኑ ደህንነቶች ከኢትዮጵያ ገብተዋል ብሏል:: እንዲሁም አፈናው ስደተኞቹን በተዋወቁ አዛኝ መሳይ ቆነጃጅት ቀጠሮ ይፈጸማል የሚል ተጨማሪ መረጃ ተገኝቷል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ በናይሮቢ ስደተኞችን እያጠመደች በተመረዘ ምግብ የምትገለው እና ራሷን ሰላ እያለች የምትጠራው ቆንጆ የተሰማራችበት ተልእኮ እንዳልተሳካ ታውቋል::በኢትዮጵያ ኤምባሲ ውስጥ እንደ ዲፕሎማት የተመዘገበቸው እና ለአምባሳደሩና ለደህንነት አታቼው ቅርብ እንደሆነች የምትታወቀው እንዲሁን ከCID አባላት ጋር በጋራ እንደምትሰራ የተደረሰባት ይህች ግለሰብ ከዚህ ቀደም በሚሊዮን ሹሩቤ ላይ የተጠቀመችውን ቃላቶች ልረዳህ እችላለሁ የፈለከው አደርግልሃለሁ ከማለት ጀምሮ ማግባት እና መውለድ ስለምፈልግ ከእንዳተ አይነት እውቀት ካለው ሰው ጋር ...አንተን ለማኖርም ሆነ ለማዝናናት እችላለሁ ና ወደ ቤቴ ልውሰድህ ...ወዘተ የሚል የማጃጃያ ዘዴ እና ውድ ግብዣዎችን በማድረግ አንድን ወጣት ለማጥመድ ያደረገችው ሙከራ ሳይሳካላት እንደቀረ የኤምባሲው ምንጮች ጠቁመዋል::ግለሰቧ ቋሚ ስልክ ቁጥር የሌላት ሲሆን በምትፈለግበት ሰአት የማትገኝ ድንገት ደውላ ለግብዣ የምታመቻች ናት::እንዲሁም በደወለችው ቁጥር ተመልሶ ቢደወል ስልኩ ዝግ መሆኑን ምንጮቹ አክለው ገልጸዋል::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

No comments:

Post a Comment