Search This Blog

Sunday, November 9, 2014

አቶ በረከት ስምዖን ያስገቡትን የስልጣን ጥያቄ ሕወሓቶች እንዳልተቀበሉት ተነገረ; “እለቃለሁ የሚል ከሆነ ሃብቱ መመርመር አለበት” ተብሏል

በውሳኔው የማይስማማ ከሆነ በሱና በቤተሰቡ በወዳጆቹ ስም የተመዘገበው ሃብት እንዲጣራ ተብሏል::
-ሳያገግሙ ስብሰባ እንዲመራ እና ሚዲያ ላይ እንዲቀርብ ታዟል::
የብአዲን/ኢሕአዲግ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት አቶ በረከት ስምኦን ያቀረቡት የስልጣን መልቀቂያ ለጊዜው በሚል ውድቅ መደረጉን ሆኖም በቅርቡ መልስ ይሰጥበታል ሲሉ የሕወሓት ባለስልጣናት መመለሳቸውን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::
Bereket Simon weeping with his wife over Meles Zenawi's death
አብዛኛውን ጊዜ ራሳቸውን ከቤት በማስቀመጥ እና በማዝናናት ያሳልፋሉ የተባሉት አቶ በረከት ስምኦን በልባቸው ላይ በተገጠመላቸው አርቴፊሻል መሳሪያ በጤንነታቸው ላይ ከባድ እክል እንደፈጠረባቸው እና ከወራት በፊት ሳኡድ አረቢያ ታክመው ቢመጡም ሊሻላቸው እንዳልቻለ እንዲሁም ባለፈው ሳምንት በድጋሚ ቢሄዱም ሆስፒታሉ ተስፋ እንዳስቆረጣቸው ሲታወቅ ከሕክምና መልስ ወደ ቢሯቸው የገቡት በጣት የሚቆጠር ቀናት እንደሆነ ታውቋል::
ይህን ሰሞን ስብሰባ መምራት አለብህ በሚዲያ መታየት አለብህ የሚል ግዳጅ ከሕወሓት ባለስልጣናት ወርዶላቸው የተደናበሩት አቶ በረከት ማገገም እንኳን ሳይችሉ በስራ መደራረብ እንዲሞቱ እየተደረገ ነው ሲሉ ከቤተሰባቸው አንዱ የሆኑት ሲናገሩ ተሰምቷል::አቶ በረከት በከፍተኛ ህመም ውስጥ እንዳሉ ሲታወቅ የሕወሓት ባለስልጣኖች የአዜብን ቡድን እንደመቱት ወዲያው በረከትንም ከጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ አሽቀንጥረው ካሳንቺስ አዲስ ቢሮ እንደሰጡት ሲታወቅ መገፋቱ እያንገበገበው በሽታውን እንዳባባሰበት ታውቋል::

No comments:

Post a Comment