Search This Blog

Thursday, March 6, 2014

የኦሮሚያ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አለማየሁ አቶምሳ በባንኮክ ታይላንድ በ45 አመታቸው አረፉ ።

የኦሮሚያ ፕረዚዳንት የነበሩት አቶ አለማየሁ አቶምሳ ሞተዋል የሚሉ ዘገባዎች ከትላንትና ምሽት ጀምሮ እየተሰራጩ ይገኛሉ። አቶ አለማየሁ በተመረእ ምግብ ምክንያት የጀመረቸው ልክፍት ጸንቶባቸው በባንኮክ ታይላድ ለህክምና ከሀዱበት ሆስፒታል አርፈዋል።

አቶ አለማየሁ አቶምሳ እንደማይተርፉ ታውቆ የመሞቻ ቀናቸውም እንደደረሰ ታውቁ ከተሾሙ ጀምሮ በስራቸው ገበታ ላይ እንደማይገኙ ከግምት ገብቶ ባለሉበት ባላቀረቡት የስልጣን መልቀቂያ እንዳቀረቡ ተደርጎ ከስልጣናቸው ሕወሓት ያሰናበታቸው ሲሆን በታይላንድ ባንኮክ ህክምናቸውን እየተከታተሉ ነበር።አቶ አለማየሁ አቶምሳ... በታይላንድ ባንኮክ በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ45 አመታቸው ነው ዛሬ ለሊት ሰባት ሰዓት ላይ ያረፉት።

አቶ አለማየሁ ከየካቲት 9 ቀን 2006 ጀምሮ በባንኮክ ህክምናቸውን ሲከታተሉ እንደቆዩ ነው ያገኘነው መረጃ የሚያመላክተው።በምስራቅ ወለጋ ቢሎ ቦሼ ወረዳ ከአባታቸው አቶ አቶምሳ ሚጃ እና ከእናታቸው ወይዘሮ አየለች ብሩ በ1961 ዓም ነው የተወለዱት አቶ አለማየሁ።

የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅህፈት ቤት ባወጣው መግለጫም፥ ላለፉት 24 ዓመታት የኦሮሞ ህዝብ እና መላው የአገሪቱ ህዝቦች ዛሬ ለደረሱበት የሰላም፣ የዴሞክራሲና የልማት ተጠቃሚነት እንዲበቁ በቁርጠኝነት የታገሉ ነባር ታጋይ ነበሩ ብሏል።በ1981 ዓመተ ምህረት የደርግን ስርዓት ለመገርሰስ ሲካሄድ የነበረውን የትጥቅ ትግል ተቀላቅለዋል።ከ1988 እስከ 1994 ድረስም የኦህዴድ ማዕከላዊ ፅህፈት ቤት እና የድርጅቱ የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ በመሆን አገልግለዋል።ከ2002 ዓመተ ምህረት ጀምሮ የኦህዴድ ሊቀመንበር ሆነው፥ ከ2003 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ደግሞ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር በመሆን ሰርተዋል።

No comments:

Post a Comment