Search This Blog

Sunday, March 9, 2014

ለሩጫ ውድድር የወጡ ሰቶች ያሰሙትን ተቃውሞ ተከትሎ ወደ እስር በት ተጋዙ

የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ እና የድርጅት ጉዳይ ሃላፊው ከሴቶቹ ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ 
ዛሬ በተካሄደው የሴቶች 5ሺሜትር ሩጫ ላይ የሰማያዊ ፓርቲ የሰቶች ጉዳይ ባመቻቸው እድል የፓርቲው ሴቶች የሮጡ ሲሆን በሩጫውም ላይ የተለያዩ መፈክሮች ማለትም እርዮት ትፈታ እና ሌሎች ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥያቄዎች አሰምተዋል::

ከመነሻው የጀመረው የተቋውሞ ድምጽ እስከ ማብቂያው የቀጠለ ሲሆን ሩጫቸውን ጨርሰው ሊገቡ ሲሉ በፖሊሶች ተቆርጠው በአሁኑ ሰዐት ታስረው ይገኛሉ በሩጫው ወቅት ተቋውሞ ሲያሰሙ የሚያሳይ ቪድዮ እና ፎቶ እንደደረሰን ምንለቅ መሆኑን በትህትና እንገልጻለን::



የሰማያዊ ፓርቲ የሴቶች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሴት አባላት እና ከእናርሱ ጋር የነበሩ ሴቶች በዛሬው እለት በተካሄደው ሩጫ ላይ ተሳትፈው ሃሳባቸውን በመግለጽ ላይ አንዳሉ በሩጫው መጨረሻ ላይ በፖሊስ ታፍሰው ወዳልታወቀ ቦታ ተወስደዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአከባቢው የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ብርሃኑ እና የድርጅት ጉዳይ ሃላፊው አቶ ጌታነህ ሴቶቹ መታሰራቸው ምንም አግባብነት እና ህጋዊ መሰረት የለውም በማለታቸው ከሴቶቹ ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ አባል አቶ አቤል ኤፍሬም በአከባቢው ስለነበሩ ብቻ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ያሉበትን ለማጣራት የሰማያዊ ወጣት ክንፍ አባላት በእንቅስቃሴ ላይ መሆናችንን እያስታወቅን የደረስንበትን ይፋ የምናደርግ መሆኑን እናስታውቃለን፡
ትግሉን በእስራት እና በግድያ ማስቆም አይቻልም!!

No comments:

Post a Comment