Search This Blog

Monday, March 31, 2014

የሌቦች ማምረቻ የሆነው የወያኔ መንግስት ጨረታ ሲጋለጥ

የመንግስት ባለስልጣናት የሙስና መንገዳቸውን ለማሳካት ሲሉ በመንግሥት ፖሊሲ፣ አሠራርና መመርያ ላይ ጫና እየፈጠሩ እንደሚመቻቸው ተደርጎ እንዲወጣ በማድረግ ላይ ናቸው ሲል ሙስና ኮሚሽን አማሯል።
ኢትየጵያ ውስጥ አሁን ያለው የሙስና መጠን ትናንትና ከነበረው እጥፍና ከእጥፍ በላይ አሻቅቧል፡፡ አሁን አገሪቷ ውስጥ ያለው የኑሮ ውድነት ወደላይ እንዲያሻቅብ ካደረጉት ምክንያቶች አንዱም የሙስና ጣርያ መንካት ነው፡፡ በዚህ ደረጃ ላይ አሳሳቢ መሆኑን መግለጽ ቀርቶ የእገሌን አገር ደረጃ አያክልም የሚለውን አባባል የኢትዮጵያ ሕዝብን እንደመናቅ ይቆጠራል፡፡በአሁኑ ወቅት ሙስና በኢትዮጵያ ውስጥ ተንሰራፍቷል፡፡ ባለጉዳይም ጉቦ ካልሰጠ ጉዳዩን እንደማያስጨርስ፤ ጉዳይ ፈጻሚም ገንዘብ ካላገኘ ጉዳይን ማስጨረስ የማይቻልበት ደረጃ መድረሱን በገሃድ በሚታይበት ደረጃ ላይ ነን፡፡ በቀበሌ፣ በወረዳ፣ በክፍለ ከተማ፣ በአዲስ አበባ መስተዳድር፣ በፖሊስ፣ በፍርድ ቤት፣ በአገር ውስጥ ገቢ፣ በጉምሩክ፣ በመንገድ ትራንስፖርት፣ በሆስፒታሎች፣ በኢሚግሬሽን፣ ወዘተ ጉዳይን ለማስጨረስ ጉቦ መስጠት የተለመደ ሆኗል፡፡
corrupted weyanee official Bereket simon with the father of corruption & their right hand man Shek Mohamed al amoudi
ጉቦ መስጠትም ሆነ መቀበል እንደ ብቃትና እንደ ሥልጡንነት እየታየ ነው፡፡ ጉቦ የማይቀበል የማይረባና የማይጠቅም ተብሎ የሚሰየምበት ደረጃ ላይ መድረሳችንን እያንዳንዱ ሰው በሚገባ ያውቀዋል፡፡ እንደዚህ በመሰለ አስፈሪ ሁኔታ ውስጥ ባለንበት ወቅት ሙስና ኢትዮጵያ ውስጥ አሳሳቢ ደረጃ ላይ አይደለም ሲባል ምን ማለት ነው? መረጃው የተገኘውስ ከየት ነው? ከተበዳይ ወይስ ከበዳይ?
ኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄዱ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ግዢዎች አነስተኛም ይሁኑ ትላልቅ የፕሮጀክት ጨረታዎች ያለኮሚሽን ክፍያ የተፈጸሙ ናቸው የሚል ጥናት ፍፁም ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም፡፡ ምንልክሳልሳዊበአሁኑ ወቅት በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ የሚካሄዱ ግዢዎችና ጨረታዎች ሕጋዊነትን ለማስያዝ ብቻ የሚካሄዱ ካልሆነ በስተቀር፣ አስቀድሞ ከታቀደውና ከታለመው ሰው ወይም ድርጅት ውጭ ማንም እንዲገባ በማይፈቀድበት ደረጃ ላይ መድረሳችንን የዋህ ሰው ሳይቀር በሚገባ የሚረዳበት ደረጃ ላይ እኮ ነን ያለነው፡፡ ግዢዎች ሲፈጸሙ ወይም ጨረታ በሚወጣበት ጊዜ የሚደረገውን ለአብነት እንይ፡፡

እጅግ የሚያስፈራው ደግሞ ሙስና ከመስፋፋቱም በላይ ሙስናን የሚዋጋና እውነታው ገሃድ እንዲሆን ጥረት የሚያደርግ ወገን ያለአግባብ እየተበደለ ነው፡፡ ሙሰኞች በያዙት የሕዝብና የመንግሥት ሥልጣን ሀቅን ለመቅበር የሚችሉትን ያህል ማድረግ የሚችሉበት ደረጃ ላይ ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ አገሪቷን እጅና እግሯን አስሮ ለጅብ እንደመስጠት ይቆጠራል፡፡
የጨረታ ዶክመንት ለሚፈለገው ድርጅት ወይም ሰው ከሳምንታት ወይም ወራት በፊት አስቀድሞ እንዲሰጥ ይደረጋል፡፡ የጨረታ ዶክመንቱ (ቴክኒካል ስፔስፊኬሽኑ) በአጫራቹ ድርጅት አማካይነት በተመረጡና በታመኑ ሰዎች እንዲሠራ ይደረጋል፡፡ ይህ በተለያዩ ከፍተኛ የመንግሥት ግዥ በሚፈጽሙ ተቋማት ውስጥ በግልጽ እንደሚደረግ ግልጽ ነው፡፡ ፀሐይ የሞቀውም ነው፡፡ ለጨረታ ወይም ለግዥው የተዘጋጀው ወይም የተመደበው ገንዘብ ለሚፈለገው ድርጅት ወይም ግለሰብ አስቀድሞ እንዲሰጥ ይደረጋል፡፡ ለጨረታ የተዘጋጀው ወይም የተመደበው ገንዘብ አስቀድሞ ለሚፈለገው ድርጅት ወይም ግለሰብ ከተሰጠ በኋላ፣ በሚያቀርበው ዋጋ ላይ ምንም ዓይነት ልዩነት ሳይኖረው ተፈላጊው ድርጅት ወይም ግለሰብ እንዲያቀርብ ተደርጎ ተመራጭ እንዲሆን ይደረጋል፡፡ ምንልክሳልሳዊበአንዳንድ ግዥዎች አሸናፊ እንዲሆን የሚፈለግ የተጫራች ድርጅት ስፔስፊኬሽን እንዳለ የጨረታ ዶክመንት ሆኖ እንደሚቀርብ በግልጽ በሚታወቅበት ደረጃ ላይ ነን፡፡
በአሁኑ ወቅት እየተካሄዱ ያሉ ግዥዎችና ጨረታዎች ከፍተኛ ሙስና እየተፈጸመባቸው የሚካሄዱ መሆኑ ቢታይም፣ ሕጋዊነትን ተከትለው እንደተፈጸሙ ስለሚቀመጡ (በወረቀት፣ በአካሄድና በአሠራር) እጅግ የረቀቁና ሥር እየሰደዱ የመጡ ሙስናዎችን ለማየት ግን አዳጋች አይደለም፡፡ ምንልክሳልሳዊአንድ ድርጅት ከሁለት በላይ የተለያዩ ስም የያዙ የድርጅት ስሞችን ይዞ በመቅረብ አንዱ አሸናፊ ሌሎች አጃቢዎች ሁነው እንደሚቀርቡ በግልጽ ይታወቃል፡፡ የጨረታ ጊዜዎችን እጅግ በማሳጠር አሸናፊ እንዲሆን ለሚፈለገው ድርጅት ወይም ግለሰብ ግን አስቀድሞ መረጃውን በመንገርና ተዘጋጅቶ እንዲቆይ በሚደረግ፣ የሌሎች ተጫራቾችን ጊዜ በማሳጠርና የዝግጅት ጊዜ እንዲያጡ በማድረግ የሚፈጸሙ ግዥዎችና ጨረታዎች ናቸው እየተካሄዱ ያሉት፡፡
አንዳንድ ቦታ ጨረታ በሚዘጋጅበት ወይም በሚካሄድበት ጊዜ ተጫራቾቹ በአጫራቹ ድርጅት ግለሰቦች ስም የሚጠሩበት አጋጣሚ እንዳለም በግልጽ የሚታወቅ ነው፡፡ ማን አሸነፈ ሲባል የአጫራቹ ግለሰብ ስም እየተጠራ እገሌ አሸነፈ ተብሎ በሚነገርበት ደረጃ ላይ እንዳለን ለማንም ባልተሰወረበት ሁኔታ ላይ ነን፡፡ እጅግ በጣም የሚገርመው ደግሞ ከጨረታ በኋላ አሸናፊው ድርጅት በፕሮጀክቶች ክትትልና በዕቃ ርክክብ ከሚፈለገው ደረጃና ብቃት በታች አፈጻጸም ያሳያል፡፡ ከሚፈለገው ዕቃ ውጭ አቅርቦቶች ሲካሄዱ ዝም እየተባለ የሚፈጸሙ የፕሮጀክቶች ግዥዎች ከበስተጀርባቸው ትልቅ ሙስና እንደሚካሄድባቸው ብዙዎች ያውቁታል፡፡ 
ለዚህ ትልቅ ማሳያ ሊሆኑ የሚችሉ በመንገድ ግንባታ፣ በትላልቅ ግድቦች ግንባታ፣ በውኃ ሥራዎች፣ በቴሌኮም ፕሮጀክቶች፣ በቤቶች ግንባታና ማጠናቀቂያ ላይ ችግሮች ጎልተው እንደሚታዩ በእጅጉ ይታወቃል፡፡ እንደ ምሳሌ ለማቅረብ ከኤርፖርት እስከ መስቀል አደባባይ እየተሠራ ያለው መንገድ ቀደም ብሎ ለሌላ ድርጅት ተሰጥቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ኋላ ግን ተቀይሮ ለሲአርቢሲ ተሰጥቷል፡፡ የመጀመርያው ተጫራችና አሸናፊ ድርጅት አቅም ሲመዘን እንኳን በዚህ ትልቅና አስቸጋሪ መንገድ እንዲሳተፍ በገጠር መንገድም ለማሳተፍ የሚያስችል ብቃት እንደሌለው ግልጽ ነበር፡፡ ታዲያ ይህ ድርጅት አሸናፊ እንዲሆን ተመርጦ የነበረው አላስፈላጊ ግንኙነት በመመሥረቱ ነበር፡፡ የዚህ ዓይነት መሰል ገጠመኞች ደግሞ እጅግ በጣም ብዙ ናቸው፡፡ ባንኮች ብድርና የውጭ ምንዛሪ ለመስጠት በግልጽ ኮሚሽን በሚቀበሉበት አገር ላይ ሙስና ኢትዮጵያ ውስጥ አሳሳቢ ደረጃ አይደለም እንዴት ይባላል?
የፀረ ሙስና ኮሚሽን አንዳንድ ሰዎች አሳሳቢ የሚባል የሙስና መረጃ ሲያገኙ፣ በተለይ ከሀብታም ነጋዴዎች ጋር የሚያያዝ ከሆነ ቀድመው ችግሩን ለማወቅና ለመፍታት ከሚጥሩ ይልቅ ለግልግል በሚሯሯጡበት አገር ላይ እያለን፣ ሙስና ኢትዮጵያ ውስጥ ዝቅተኛ ነው እንዴት ይባላል? በአሁኑ ወቅት ከከፍተኛ እስከ ዝቅተኛ የመንግሥት አመራሮች ድረስ በሀብታም ተፅዕኖ ሥር በወደቁበት፣ ጉቦ በመቀበል የአገራቸውን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፈው በሚሰጡበት፣ ሀቅን በገንዘብ በሚለውጡበት፣ በጠራራ ፀሐይ ብሉ ሌብልና ቪኤስኦፒ በካርቶን በሚጫንበት፣ የሰው ሕይወት በገንዘብ አደጋ ላይ በሚወድቅበት፣ ዓይን ያወጡ ሙሰኞች በሰፊው ሕዝብ ፊት ደረታቸውን ነፍተው ጉራቸውን በሚነፉበትና ኃይላቸውን የሚያሳዩበት ወቅት መሆናችን እየታወቀ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሙስና አሳሳቢ ደረጃ ላይ አይደለም እንዴት ይባላል?
ትናንትና ለሀቅ፣ ለዲሞክራሲና ለአገራቸው ብልጽግና ሲሉ የወጣትነት ዕድሜያቸውን በረሃ የወጡ ወንድሞቻቸውን፣ እህቶቻቸውንና ጓደኞቻቸውን ቀብረው እዚህ ደረጃ ላይ የደረሱ ጀግኖች በሙስና ተነክረው ሀብታም ሥር በተንበረከኩበት ወቅት፣ የተለያዩ ድርጅቶች ቅጥረኛ በሆኑበት ወቅት፣ አሠራርና መመርያዎችን ጥሰው በኔትወርክ በተሳሰሩበት ወቅት፣ እርስ በራሳቸው እሳትና ጭድ ሁነው በማይተማመኑበት ወቅት፣ ለሕዝብ ህልውና ዋስትና በታጣበት ወቅት፣ሙስና ኢትዮጵያ ውስጥ ሊያሳስብ አይገባም ተብሎ እንዴት ይነገራል?
ከምንም ጊዜ በላይ እጅግ አሳሳቢ፣ ከአሳሳቢነቱ በላይም ጊዜ የማይሰጠውና ወረርሽኝ በሆነበት ደረጃ ላይ ነው ያለነው፡፡ አንዳንድ ቦታ ላይም ሙሰኞች የሙስና መንገዳቸውን ለማሳካት ሲሉ በመንግሥት ፖሊሲ፣ አሠራርና መመርያ ላይ ጫና እየፈጠሩ እንደሚመቻቸው ተደርጎ እንዲወጣ በማድረግ ላይ እንደሆኑ ወሬዎች በሚናፈሱበት ደረጃ ላይ ነው ያለነው፡፡ አንዳንዱ ቅንጣት ጥፋት የሌለው ይመስል ከራባቱን አስሮ ‹‹ሙስናን እንዋጋ›› የሚለው ከበስተጀርባው ትልቅ ጥፋት ተሸክሞ ነው፡፡
እጅግ የሚያስፈራው ደግሞ ሙስና ከመስፋፋቱም በላይ ሙስናን የሚዋጋና እውነታው ገሃድ እንዲሆን ጥረት የሚያደርግ ወገን ያለአግባብ እየተበደለ ነው፡፡ ሙሰኞች በያዙት የሕዝብና የመንግሥት ሥልጣን ሀቅን ለመቅበር የሚችሉትን ያህል ማድረግ የሚችሉበት ደረጃ ላይ ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ አገሪቷን እጅና እግሯን አስሮ ለጅብ እንደመስጠት ይቆጠራል፡፡

No comments:

Post a Comment