Search This Blog

Friday, March 21, 2014

በኦሮሚያ ቡሌ ሆራ ዩንቨርስቲ ራሳቸውን የሚያጠፉ ተማሪዎች ቁጥር እየጨመረ ነው::

ትላንት ለሊቱን አንዲት የፕላንቴሽን ሳይንስ ተማሪ ሞታ ተገኝታለች
በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በጉጂ ኦሮሚያ ቡሌሆራ ከተማ በሚገኘው እና ቡሌ ሆራ ተብሎ በሚጠራው ዩንቨርስቲ ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች በሚደርስባቸው የአስተዳደር በደል እና በመማር ማስተማሩ ላይ በሚደረጉት ፖለቲካዊ ተጽእኖዎች
ራሳቸውን የሚያጠፉ ተማሪዎች እና ትምህርታቸውን ጥለው የሚወጡ ተማሪዎች መበራከታቸውን ከዩንቨርስቲው የደረሱን እገባዎች ያመለክታሉ::
በዩንቨርስቲው ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች በአሁን ጊዜ ወደ 3000 የሚጠጋ መሆኑን የነገሩን ምንጮች ከእለት ወደ ኢለት በብሶት የተማረሩ ተማሪዎች ራሳቸውን ማጥፋት የቀጠሉ ሲሆን በዚህ አመት ብቻ የአሬውን ጨምሮ አራት ተማሪዎች ራሳቸውን አጥፍተዋል:: እንዲሁም አንድ ተማሪ ከፎቅ ላይ ዘሎ በመውደቅ ራሱን ለማጥፋት ቢሞክርም ተርፏል::
ቁጥራቸው ከ500 በላይ የሆኑ ተማሪዎች በተለያየ ዩንቨርስቲው በሚፈጥረው የአስተዳደር እና የፖለቲካ ጉዳዩች ብስጭት ራሳቸውን በመሳት ወደ ቤተሰቦቻቸው ትምህርታቸውን አቅውርጠው ተመልሰዋል::በዛሬው እለት ደግሞ የፕላንቴሽን ሳይንስ የሁለተኛ አመት ተማሪ የሆነች ለሊቱን ሞታ መገኘቷን ታውቋል::

No comments:

Post a Comment