Search This Blog

Sunday, March 30, 2014

ፍትሕ ማግኘት ገጠመኝ ሙስና ደግሞ የአንቀጾች ሁሉ የበላይ አንቀጽ እየሆነ መጥቷል

የበደለ፣ የአገር ሀብት ያባከነ፣ ሕገ የረገጠ ግለሰብ ማጥፋቱ እየታወቀ ይቀጣል ወይስ አይቀጣም ለሚለው ጥያቄ ወሳኙ ማስረጃ መሆኑ እየቀረ ነው፡፡
የፖለቲካ ገጠመኝ ሆኗል፡፡ ይታሰራል የተባለው ሊሾም፣ ተጠያቂ ይሆናል የተባለው ጠያቂ የሚሆንበት ሁኔታ አለ፡፡
መልካም አስተዳደር በሕግና በመርህ ደረጃ መከበር አለበት ተብሎ የታወጀ፣ የተነገረ፣ የተለፈፈለት ነው፡፡ በተግባር ደግሞ አቤት ብዬ ሰሚ አገኛለሁ፣ ቅሬታ አቅርቤ ይፈታልኛል የሚል ዜጋ የለም!!!! በዚህ ዙሪያም ጉቦና ጥቅማ ጥቅም የበላይነት እየያዙ ነው፡፡ የአቅም ማነስ ችግር ትልቅ እንቅፋት ነው፡፡ ስብሰባዎችና ሥልጠናዎች የችግር መፍቻ መድረኮች መሆናቸው ቀርቶ መደበቂያ እየሆኑ ነው፡፡ ‹‹በስብሰባና በሥልጠና ምክንያት ኃላፊ የለም›› የሚል ማስታወቂያ መለጠፍ ነው የቀረው፡፡ ኃላፊ ቢሮው ገብቶ አቤቱታ አንብቦ ችግር መፍታት መርህና ግዴታው መሆኑ ቀርቶ የፖለቲካ ገጠመኝ እየሆነ ነው፡፡
የሕግ የበላይነት እንዲኖር፣ ሰብዓዊ መብት እንዲከበር፣ የፕሬስ ነፃነት እንዲረጋገጥ፣ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እውን እንዲሆን የሚያደርጉ ሕገ መንግሥትና ሕጎች አሉን ????????? ከድህነት የሚያላቅቅ፣ መካከለኛ ገቢ ወዳላት አገር የሚያሸጋግር፣ የቤት፣ የጤና፣ የትምህርት፣ የትራንስፖርት፣ ወዘተ ችግሮችን የሚፈታ ዕቅድም አለን ???????????
እነዚህ አሉ ማለት ግን ዲሞክራሲ ተረጋገጠ፣ ልማት እውን ሆነ ማለት አይደለም፡፡ በመርህ ደረጃ ተግባር ላይ ካዋልናቸው ይጠቅማሉ፡፡
ካላከበርናቸው፣ ከረገጥናቸውና ከጣልናቸው ደግሞ ገጠመኝ ይሆናሉ፡፡ ፍትሕ ገጠመኝ እየሆነ ነው፡፡ምንሊክሳልሳዊ የፍትሕ መጓደል በሚያሳስብ ሁኔታ እየታየ ነው፡፡ በፍትሕ አካላት ውስጥ በአቅምና በአመለካከት ድክመት አለ፡፡ የሥነ ምግባር ጉድለት በትልቁ እየታየ ነው፡፡ በጠበቆች፣ በዳኞችና በዓቃቢያነ ሕግ በኩል አሳሳቢ የሥነ ምግባርና የአቅም ችግር እየተስተዋለ ነው፡፡
በአጠቃላይ የፍትሕ አካላት መጠናከር እያሳዩ ከመጓዝ ይልቅ እየተልፈሰፈሱና እየተንገዳገዱ ናቸው፡፡ በዚህ ምክንያት ፍትሕ ማግኘት መርህ መሆኑ ቀርቶ ገጠመኝ እየሆነ ነው፡፡ ጉቦ የአንቀጾች ሁሉ የበላይ አንቀጽ እየሆነ መጥቷል፡፡ሰላማችን፣ ሉዓላዊነታችን፣ አንድነታችንና ህልውናችን በመርህ ደረጃ ዋስትና ያላቸው መሆናቸው ቀርቶ የፖለቲካ ገጠመኝ ሆነዋል፡፡ የአገር እና የህዝብ ህልውና ገጠመኝ በመሆኑ ወያነ ደግሞ የዛፍ ላይ እንቅልፍ ተኝቷል፡፡ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም በጋራ የዛፍ ላይ እንቅልፉን የሚለጥጠውን ወያነን በማውረድ ህዝባዊ የበላይነትን መቀናጀት የዜግነት ግደታችንን መወጣት አለብን::

No comments:

Post a Comment