Search This Blog

Monday, February 10, 2014

10 ፓርቲዎች ውህደትና ግንባር ለመፍጠር ለምርጫ ቦርድ ጥያቄ አቀረቡ




አስር የተቃዋሚ ፓርቲዎች ውህደትና ግንባር ለመፍጠር ለምርጫ ቦርድ ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን፤ ምርጫ ቦርድም ጥያቄያቸውን መርምሮ በቅርቡ ውሳኔ እንደሚሰጥ አስታወቀ፡፡
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) እና ብርሃን ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ (ብአዴፓ) “አንድነት በሚል ስያሜ የውህደት ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ የመላው ኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (መኢዴፓ)፣ የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ)፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ (ኢብአፓ)፣ ሶዶ ጐርደና ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ሶጐሕዴድ)፣ ኦሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ኅብረት (ኦሕዴኅ)፣ ከምባታ ሕዝብ ኮንግረስ (ከሕኮ) እና ጌዲኦ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት/ ጌሕዴድ/ በበኩላቸው “ትብብር ለዴሞክራሲያዊነት ኢትዮጵያ (ትብብር)” በሚል ስያሜ የቅንጅት ጥያቄ ማቅረባቸው ታውቋል፡፡ 
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ይስማ ጅሩ ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፤ ቦርዱ የቀረቡትን የውህደትና የቅንጅት ጥያቄዎች በህጉ መሠረት መርምሮ ያልተሟሉ ጉዳዮች እንዲሟሉ በማድረግ እውቅና ይሰጣል፡፡ 
በአሁኑ ወቅት በቦርዱ ተመዝግበው በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ 75 የፖለቲካ ፓርቲዎች ሲኖሩ ሃያ አራቱ አገር አቀፍ፣ ሃምሳ አንዱ ደግሞ ክልላዊ ፓርቲ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ 

No comments:

Post a Comment