Search This Blog

Wednesday, February 19, 2014

ሰበር ዜና አንድነትና መኢአድ የጠሩት የተቃውሞ ሰልፍ ብአዴንን አሳስቦታል “ስራ አጥ” ያላቸውን ወጣቶችን ዛሬ ሲያሳፍስ ውሏል

 የባጃጅ አሽከርካሪዎችም ሰልፉን እንዳይቀሰቅሱና እንዳይሳተፉ ማስጠንቀቂያ ደርሷቸዋል

አንድነት ፓርቲ ከመኢአድ ጋር በመሆን የጠራውና በመጪው ዕሁድ የካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ም ብአዴንን በመቃውሞ በሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ብአዴንን እንዳሳሰበውና በባህር ዳር ከተማ “ስራ አጥ” ያላቸውን ወጣቶችን ዛሬ ሲያሳፍስ መዋሉን ለክልሉ መንግስት ቅርበት ያላቸው የፍኖተ ነፃነት ምንጮች አጋለጡ፡፡
የፍኖተ ነፃነት ምንቾች እንዳጋለጡት በብአዴን ከፍተኛ ሹማምንት ትዕዛዝ በባህርዳር ከተማ ያሉ “ስራ አጥ” ወጣቶች ዛሬ ሲታፈሱ ውለዋል፡፡ አፈሳው በመንገድ ላይ ንግድ የተሰማሩና ኑሯቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ዜጎችንንም የጨመረ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን የብአዴን ካድሬዎች የባህር ዳር ከተማ የባጃጅ አሽከርካሪዎችንም በመሰብሰብ ሰልፉን እንዳይቀሰቅሱና  በተቃውሞ ሰልፉ ላይም እንዳይሳተፉ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋቸዋል፡፡
የባህር ዳር የባጃጅ አሽከርካሪዎች አንድነት ፓርቲ በሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ በባህርዳር ባደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ በራሳቸው ተነሳሽነት ቅስቀሳ ሲያሰርጉ እንደነበር ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment