Search This Blog

Tuesday, February 25, 2014

በአርማጭሆ የአንድነት ፓርቲ አባላት ከስራ ተባረሩ

-የፓርቲው አባላት በመንግስት ስራ ውስጥ ድርሻ አይኖራችሁም ተብለው መባረራቸውን የተባረሩ የፓርቲው አባላት ለኢሳት ገልጸዋል። አብዛኞቹ ለሱዳን እየተሰጠ ያለውን መሬት በተመለከተ ተቃውሞ በማሰማታቸው መባረራቸውን ገልጸዋል።
የምእራብ አርማጭሆ የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ የሆነው አቶ አንጋው ተገኝ፣ በድንበር ጉዳይ ጥያቄ በማንሳታቸው መባረራቸውን ገልጸዋል
ከተባረሩት የፓርቲው አባላት መካከል አወቀ ብርሃኑ፣ አባይ ዘውዱ ፣ አንጋው ተገኝ፣ አብርሃም ልጃለም እና አለልኝ አቡሃይ ይገኙበታል።

No comments:

Post a Comment